በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

በወላይታና በሲዳማ ብሄር መካከል እርቀ ሰላም የማውረድ እንቅስቃሴ ቀጥሏል፡፡

በወላይታና በሲዳማ ብሄር መካከል እርቀ ሰላም የማውረድ እንቅስቃሴ ቀጥሏል፡፡

ትናንት የወላይታ አገር ሸማግሌዎች በግጭቱ የተጎዱ የሲዳማ ተወላጆችን ሃዋሳ መጥተው በባህላዊ ሥርዓት ያፅናኑ ሲሆን የሲዳማ ሸማግሌዎችም ወላይታ ሶዶ በመሄድ ጠይቀዋል፡፡

በቀጣይም እርቀ ሰላም የማውረድና የይቅርታ ሥርዓት ከህዝብና ከወጣቶች ጋርም ይፈፀማል ተብሏል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ

በወላይታና በሲዳማ መካከል እርቀ ሰላም የማውረድ እንቅስቃሴ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:09 0:00

ካርቱም የሚገኘው የደቡብ ሱዳን ኤምበሲ እንዳስታወቀው፣ ሱዳን ውስጥ እየተካሄደ ባለው ተቃውሞ፣ አራት ደቡብ ሱዳናውያን ተገደሉ።

ካርቱም የሚገኘው የደቡብ ሱዳን ኤምበሲ እንዳስታወቀው፣ ሱዳን ውስጥ እየተካሄደ ባለው ተቃውሞ፣ አራት ደቡብ ሱዳናውያን ተገደሉ።

ከቪኦኤው ስውዝ ሱዳን ኢን ፎከስ ፕሮግራም ጋር ቃለ ምልስልስ ያደረጉት፣ በካርቱም የደቡብ ሱዳን አምባሳደር ሜያመ ድዩተ እንደተናገሩት፣ ሁለት ወንዶችና ሁለት ሴቶች ደቡብ ሱዳናውያን የተገደሉት፣ የሱዳን የፀጥታ ኃይል፣ ሱዳን ዋና ከተማ ላይ የተቃውሞ ሠልፍ በአካሄዱ ሰዎች ላይ በከፈተው ተኩስ ነው።

ሱዳን ውስጥ የሚገኘውና የደቡብ ሱዳናውያንን ደኅንነት የሚከታተለው የኤምበሲው አጣሪ ኮሚቴ በሰጠው መግለጫ አራቱ ሰዎች ሰላማዊ ሰልፉን እየተመለከቱ እንጂ በሰልፉ ተሳታፊዎች አልነበሩም ብሏል።

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG