በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

ጠ/ሚ ዐብይ አሕመድ

ኢትዮጵያዊያን ሃገራቸውን ለመለወጥ ያገኙትን ዕድል እንዲጠቀሙበት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ጥሪ አቅርበዋል።

ኢትዮጵያዊያን ሃገራቸውን ለመለወጥ ያገኙትን ዕድል እንዲጠቀሙበት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ጥሪ አቅርበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ አየተከበረ ስላለው የገና በዓል ባስተላለፉት በፅሁፍ ባወጡት መልዕክት ስለሰላም፣ ስለመከባበር፣ ስለሥራና ብልፅግና ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከትናንት በስተያ ቅዳሜ ከመምህራን ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት “መታሠርና መገረፍ የለመድን ሰዎች ያንን ሲተው የደከምን ከመሰለን ስተናል” ብለዋል።

በአንዳንድ የኦሮምያ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ ታጣቂ ኃይሎችን በተመለከተም ተናግረዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ

የጠ/ር ዐብይ አሕመድ የገና በዓል መልዕክት
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:08 0:00

የዩናይትድ ስቴትስ ከፊል የመንግሥት ሥር ከተዘጋ ዛሬ 17ኛ ቀኑን ይዟል።

የዩናይትድ ስቴትስ ከፊል የመንግሥት ሥር ከተዘጋ ዛሬ 17ኛ ቀኑን ይዟል። ፕሬዚዳንት ዶናል ድትረምፕ ከሜርክሲኮ ጋር በሚዋሰነው ድንበር ላይ ግንብ ለመገንባት የሚያስፈልግ ባጀት እንዲመደብ በሚለው አቋማቸው ጸንተዋል። የህግ መወሰኛ ምክር ቤት ዲሞክራቶች ደግሞ የተዘጉት መሥሪያ ቤቶች እንዲከፈቱ ሊረዳ በሚችል ዕቅደ-ሃሳብ ላይ ድምፅ ለመስጠት እየተዘጋጁ ናቸው።

አዲስ የሥራ ሳምንት በተጀመበት በዛሬው ዕለት በብዙ መቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የመንግሥት ሥራተኞችሥራ መግባት አይችሉም። ሌሎች በብዙ መቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የመንግሥት ሠራተኞች ደግሞ የሚከፈላቸው መቼ እንደሆነ ባይውቁም በሥራ ገበታቸው ተገኝተው እየሰሩ ናቸው።

የህግ መምርያ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ የተዘጉት መሥሪያ ቤቶች እንዲካፈቱ በነፍስ ወከፍ መሥሪያ ቤቶች ባጀት ላይ ድምፅ እንዲሰጥበት አደርጋለሁ ብለዋል። ቅድሚያ የሚሰጣቸው የገንዘብ ሚኒስቴርና የሀገር ውስጥ ገቢ አገልግሎት እንደሚሆኑ ገልፀዋል።

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG