በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

ኮሚሽነር ዝግ አለ ገበየሁ

ሁለቱ የቀድሞ የብአዴንና የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች በቁጥጥር ሥር የዋሉት በጥረት ኮርፕሬት ፈፅመዋል ተብለው በተጠረጠሩበት የኃብት ብክነት ወንጀል ነው።

ሁለቱ የቀድሞ የብአዴንና የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች በቁጥጥር ሥር የዋሉት በጥረት ኮርፕሬት ፈፅመዋል ተብለው በተጠረጠሩበት የኃብት ብክነት ወንጀል ነው።
አቶ ታደሰ ካሳ በጥረት ኮርፕሬት በዋና ሥራ አስፈፃሚነት አቶ በረከት ስምኦን ደግሞ የጥረት ኮርፕሬት የቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ለበርካታ ዓመታት ሰርተዋል። ሁለቱ የቀድሞ ከፍተኛ አመራሮች ዛሬ አዲስ አበባ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ነው የተያዙት።
ይህንን ተከትሎ የአማራ ክልል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል። አቶ በረከትና አቶ ታደሰ ዛሬ ጠዋት ባህር ዳር ከተማ የገቡ ሲሆን በጊዜያዊ ማረፊያ ቤት ውስጥ እንደሚገኙ ኮሚሽነር ዝግ አለ ገበየሁ ተናግረዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የአቶ በረከት ስምኦን እና አቶ ታደሰ ካሳ በቁጥጥር ሥር መዋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:50 0:00

አቶ በረከት ስሞኦን

የአቶ በረከት ስሞኦን በቁጥጥር ሥር መዋል እስከአሁን በመንግሥት ከተወሰዱ የበላይነትን ከማረጋገጥ ደረጃዎች ከፍተኛው መሆኑን የፖለቲካ ምሁራንና የፓርቲ መሪዎች ተናግረዋል፡፡

የአቶ በረከት ስሞኦን በቁጥጥር ሥር መዋል እስከአሁን በመንግሥት ከተወሰዱ የበላይነትን ከማረጋገጥ ደረጃዎች ከፍተኛው መሆኑን የፖለቲካ ምሁራንና የፓርቲ መሪዎች ተናግረዋል፡፡

አቶ በረከት በሙስና በሰብዓዊ መብት ጥሰት ተጠርጥረው እስካሁን በቁጥጥር ሥር ከዋሉት ሰዎች ከፍ ያለ ሥልጣን የነበራቸው ናቸው ብለዋል እነዚህ አስተያየት ሰጭዎች፡፡

የህግ የበላይነትን ለማስከበር እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎች ወጥነት ሊኖራቸው እንደሚገባ ግን አሳስበዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

በአቶ በረከት ስሞኦን በቁጥጥር ሥር መዋል - የፖለቲካ ምሁራንና የፓርቲ መሪዎች አስተያየት
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:01 0:00

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG