በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

የኦሮሞ አባ ገዳዎች ህብረት

የኦሮሞ አባ ገዳዎች ኅብረት ያዘጋጀው የእርቀ-ሰላም መድረክ ዛሬ አዲስ አበባ ላይ ተካሂዷል።

የኦሮሞ አባ ገዳዎች ኅብረት ያዘጋጀው የእርቀ-ሰላም መድረክ ዛሬ አዲስ አበባ ላይ ተካሂዷል።

በመድረኩ ላይም የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኦዲፒ) እና የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) መሪዎችን ጨምሮ ሌሎች በኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተሣትፈዋል።

በመድረኩ ላይ የተገኙት የኦሮሞ አባ ገዳዎች ኅብረት ሰብሳቢ አባ ገዳ በየነ ሰንበቶ፥ “ሃገራችንን የምንጠብቀው እኛ ነን፤ የሃገራችን ጉዳይ የፖለቲካ ፓርቲዎች አይደለም፤ የእኛ ጉዳይ ነው፤ የሃገራችን ሰላም ጉዳይ ሁላችንንም ያገባናል” ብለዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የኦሮሞ አባ ገዳዎች ኅብረት የእርቀ-ሰላም መድረክ በአዲስ አበባ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:09 0:00

የጠ/ሚ ዐብይ አሕመድ የአውሮፓ ጉብኝት

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ርዕሰ-ሊቃነ-ጳጳሳት ዘካቶሊካዊያን አቡነ ፍራሲዝን

አውሮፓ ጉብኝት ላይ የሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ርዕሰ-ሊቃነ-ጳጳሳት ዘካቶሊካዊያን አቡነ ፍራሲዝን ቫቲካን ላይ አግኝተው አነጋግረዋል።

አውሮፓ ጉብኝት ላይ የሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ርዕሰ-ሊቃነ-ጳጳሳት ዘካቶሊካዊያን አቡነ ፍራሲዝን ቫቲካን ላይ አግኝተው አነጋግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዳቮስ ላይ እየተካሄደ ባለው ዓመታዊው የዓለም የምጣኔኃብት ጉባዔ ላይ ለመገኘት ስዊትዘርላንድ ገብተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስት አብይ በጣልያን ቆይታቸው ወቅት ከሃገሪቱ መሪዎች በተጨማሪ የዓለም የምግብና የግብርና ድርጅት /ፋኦ/ን፣ የዓለም የምግብ መርኃግብር WFPንና የግብርና ልማት ዓለምአቀፍ ድርጅቱን - ኢፋድን ጨምሮ መቀመጫቸው ሮም ከሆነ ዓለምአቀፍ ድርጅቶች ኃላፊዎች ጋር ተገናኝተው መወያየታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፅሕፈት ቤት ቃል አቀባይ ቢልለኔ ስዩም ገልፀዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የጠ/ሚ ዐብይ አሕመድ የአውሮፓ ጉብኝት
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:11 0:00

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG