በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

የሐረር ከተማ የውኃ ችግር በከፊል እየተቃለለ መሆኑ እየተሰማ ነው።

የሐረር ከተማ የውኃ ችግር በከፊል እየተቃለለ መሆኑ እየተሰማ ነው።

ከከተማዪ የውኃ ምንጮች አንዱ የሆነው የኤረር ግድብ አቅርቦት በአካባቢው ነዋሪዎች ተቋርጦ መቆየቱ ተዘግቧል።

ነዋሪዎቹ የአካባቢው የከርሠ-ምድር ውኃ እየተመናመነ ስለሆነ ለእርሻ የሚሆን ውኃ እንዲለቀቅላቸው፣ እንዲሁም ለግድቡና ለውኃ ጣቢያው መሥሪያ ቦታ ሲባል ከይዞታዎቻቸው እንዲነሱ የተደረጉ ሰዎች ቀደም ሲል የተከፈላቸው ካሣ እንዲሻሻልላቸው መጠየቃቸው ተገልጿል።

ክልሉ በነዋሪዎቹ ጥያቄዎች ተስማምቶ ውኃው መለቀቅ መጀመሩን የክልሉ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ባለሥልጣን ሥራ አስኪያጅ አቶ ተወለዳ አብዶሽ አመልክተዋል፡፡

ከነዋሪዎቹ ጋር የተደረሰውን ስምምነት ተግባራዊ ማድረግ ለመፍትኄው ዘላቂነት አስፈላጊ መሆኑን የክልሉ የፍትህና የፀጥታ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ አህመድ ዩሱፍ ተናግረዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የሐረር ከተማ የውኃ ችግር
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:24 0:00

ፎቶ ፋይል

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር /ኦነግ/ መሪዎችና አባሎቼ እየታሠሩ ናቸው ሲል አቤቱታ አሰማ።

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር /ኦነግ/ መሪዎችና አባሎቼ እየታሠሩ ናቸው ሲል አቤቱታ አሰማ።

ኦነግ ይህንን የገለፀው “የኢትዮጵያ መንግሥት በኦሮሞ ነፃነት ግንባር አመራር አካላትና አባላቱ ላይ የሚያካሂደውን ዛቻና እሥራት በአስቸኳይ ያቁም ሲል ከትናንት በስተያ፤ ቅዳሜ ባወጣው መግለጫ ነው።

መንግሥት ባለፈው ሣምንት ባወጣው መግለጫ “ታጥቀውና ሳይታጠቁ የሚንቀሳቀሱ 835 ግለሰቦችን ቁጥጥር ሥር አውያለሁ” ማለቱ ይታወሳል ።

የኦነግን የቅዳሜውን መግለጫ አስመልክቶ ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን፣ ከመከላከያ ሚኒስቴርና ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ለማጣራት ያደረገው ጥረት አለመሣካቱን ተገልፆል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ኦነግ መሪዎችና አባሎቼ እየታሠሩ ናቸው አለ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:24 0:00

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG