በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት መሥርያ ቤት በከፊል ከተዘጋ 11ኛ ቀኑን ይዟል። ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ከሜክሲኮ ጋር በሚያዋስነው ድንበር ግንብ ለመሥራት የሚያስፈልግ ገንዘብ እንዲመደብ ያቀረቡት ጥያቄ የምክር ቤት አባላት አልተቀበሉትም።

የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት መሥርያ ቤት በከፊል ከተዘጋ 11ኛ ቀኑን ይዟል። ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ከሜክሲኮ ጋር በሚያዋስነው ድንበር ግንብ ለመሥራት የሚያስፈልግ ገንዘብ እንዲመደብ ያቀረቡት ጥያቄ የምክር ቤት አባላት አልተቀበሉትም።

የህግ መመርያ ምክር ቤት አባላት በመጪው ሀሙስ ሥራ ሲጀምሩ የብዙሃነት ቦታ ስለሚኖራቸው ለ11 ቀናት ያህል ተዘግቶ የቆየውን የመንግሥት ሥራ ክፍል ለመክፈት የሚያስችል የባጀት ዕቅድ እናወጣለን ይላሉ።

ዲሞክራቶቹ የምክር ቤት አባላት የሚያሳልፉት የባጀት ዕቅድ የትረምፕ የድንበር ግንብን አያካትትም። ትረምፕ ባስተላለፉት የአዲስ ዓመት መልዕክት፤ በዲሞክራቶች ዕቅደ ሃስብ ላይ ተሳልቀዋል።

ዶ/ር ሂሩት ወልደማሪያም

ከአንድ ዩኒቨርስቲ በስተቀር በሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት እንደቀጠለ መሆኑን የሳይንስና ከፍተኛ የትምህርት ሚኒስትር አስታወቁ፡፡

ከአንድ ዩኒቨርስቲ በስተቀር በሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት እንደቀጠለ መሆኑን የሳይንስና ከፍተኛ የትምህርት ሚኒስትር አስታወቁ፡፡

በአንዳንድ ዩኒቨርስቲዎች ያጋጠመው የፀጥታ መታወክም ለውጡን የማይደግፉ ኃይሎች የፈጠሩት የችግር ነፀብራቅ መሆኑን ሚኒስትሯ ዶ/ር ሂሩት ወልደማርያም ለጋዜጠኞች አብራርተዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመማር ማስተማር ሂደት
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:45 0:00

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG