በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

የሱዳን መንግሥት በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ እያካሄደ ነው ያለውን ከመጠን ያለፈ የኃይል እርምጃ እንዲያቆም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ከሚሽነር ሚሼል ባሸሌ ጠየቁ።

የሱዳን መንግሥት በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ እያካሄደ ነው ያለውን ከመጠን ያለፈ የኃይል እርምጃ እንዲያቆም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ከሚሽነር ሚሼል ባሸሌ ጠየቁ።

ሱዳን ውስጥ ከተከሰተው የነዳጅ እጥረትና የይበ ዋጋ ድንገት መናር ጋር ተያይዞ የተቀሰቀሰው የሕዝብ ቁጣና ሰልፍ ወደ አንድ ወር እየሆነው ነው።

ይህ ቁጣ ወደ ፖለቲካ እንቅስቃሴነት አድጎ ተቃዋሚዎቹ አሁን እያነሱ ያሉት ጥያቄ ላለፍት ሰላሣ ዓመታት የገዙት ፕሬዚዳንት ኦማር ሃሰን አልበሽር ሥልጣን እንዲለቅቁና እጅግ ነቅዟል የሚሉት መንግሥታቸው እንዲቀየር ነው።

በሌላ በኩል ግን መንግሥቱ እየሰጠ ያለው ምላሽ ሁኔታዎቹን ከማባባስ አልፎ የፈየደው ቁም ነገር የለም ሲሉ የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ቃል አቀባይ ራቪና ሻምዳሳኒ የድርጅቱን ቅሬታ አመልክተዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ሱዳን የሰብዓዊ መብቶች ማሳሰቢያ እየደረሣት ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:55 0:00

የኢህሃዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስብሰባ

የኢህሃዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ እየተካሄደ ባለው ለውጥና በሕግ የበላይነት መከበር ላይ እየተወያዩ መሆኑ ተገለጠ፡፡

የኢህሃዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ እየተካሄደ ባለው ለውጥና በሕግ የበላይነት መከበር ላይ እየተወያዩ መሆኑ ተገለጠ፡፡

ከ36ቱ የኢህሃዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት አንዱና በግንባሩ ጽ/ቤት የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪል ማኅበራትና የአጋር ድርጅቶች አስተባባሪ አቶ ፈቃዱ ተሰማ ማምሻውን ለአሜሪካ ድምፅ እንዳስረዱት በተጠቀሱት ርዕሶችና በተያዙ ጉዳዮች ላይ ነፃና ግልፅ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የኢህሃዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስብሰባ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:37 0:00

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG