በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

ከፋ ዞን

በደቡብ ክልል ከፋ ዞን ዴቻ ወረዳ ከ20 ሺህ በላይ የከምባታና ጠምባሮ አርሶአደሮች በማንነታችን ጥቃት ደርሶብናል በማለት እየተፈናቀሉ ናቸው፡፡

በደቡብ ክልል ከፋ ዞን ዴቻ ወረዳ ከ20 ሺህ በላይ የከምባታና ጠምባሮ አርሶአደሮች በማንነታችን ጥቃት ደርሶብናል በማለት እየተፈናቀሉ ናቸው፡፡

አርሶአደሮቹ የተፈናቀሉት ከሶስት ሳምንት በፊት በወረዳው ከ30 በላይ ሲቪሎች በታጠቁ ግለሰቦች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን ተከትሎ ነው ተብሏል፡፡

ጉዳያችንን ለክልሉ መንግሥት ብናሳውቅም ችላ ተብለናል ሲሉ አርሶአደቹ ተናግረዋል። አሁን ለችግር መጋለጣቸውንም ለቪኦኤ አስረድተዋል፡፡

የከምባታ ጠንባሮ ዞን በበኩሉ የተፈናቀሉ ዜጎች በስቃይ ላይ መሆናቸውን ገልጦ መፍትሔ እየተፈለገ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የከምባታና ጠምባሮ አርሶአደሮች
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:01 0:00

ሰሞኑን የኦሮሞ አባ ገዳዎች ፣ የሲንቄ እናቶች እና ወጣቶች በአዲስ አበባ የኦሮሞ ባህል ማዕከል ጉባኤ አካሄደዋል፣ ውሳኔም አስተላልፈዋል፡፡

ሰሞኑን የኦሮሞ አባ ገዳዎች፣ የሲንቄ እናቶች እና ወጣቶች በአዲስ አበባ የኦሮሞ ባህል ማዕከል ጉባኤ አካሄደዋል፣ ውሳኔም አስተላልፈዋል፡፡

በኦሮሞ ስም የሚቀሳቀሱ ሁሉቱም ፓርቲዎች ማለትም ኦዴፓ እና ኦነግ ውጊያ ማቆም አለባቸው ይላል ውሳኔያቸው ።

አባ ገገዳዎች በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ቦታዎች አለመረጋጋት አለመኖሩና ሰላም መጥፋቱ በተደጋጋሚ እየታየ ስለሆነ ክልሉ ሥጋት ውስጥ ወድቋል ብለዋል።

በክልሉ አስተማማኝ ሰላም እንዲኖር ፓርቲዎች ልዩነታቸውን አጥበው ችግሮችን በውይይት መፍታት እንዳለባቸው ሲሉም አሳሰበዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ለኦሮሚያ ሰላም የፓርቲዎች ኃላፊነት
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:21 0:00

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG