በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው

ከ319 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት በመንግሥት ላይ አድርሰዋል ባላቸው ስምንት ግለሰቦች ላይ የኢትዮጵያ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ክሥ መሠረተ።

ከ319 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት በመንግሥት ላይ አድርሰዋል ባላቸው ስምንት ግለሰቦች ላይ የኢትዮጵያ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ክሥ መሠረተ።

በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድም 15ኛ ወንጀል ችሎት የክሥ ዶሴ ዛሬ የተከፈተባቸው የብረታ ብረትና ኢንጂኔሪንግ ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ሜጄር ጄነራል ክንፈ ዳኘው፣ ብሪጋዲየር ጄነራል ጠና ቁርንዲ፣ ኮሎኔል ደሴ ዘለቀ፣ ኮሎኔል ጌትነት ጉድያ፣ ኮሎኔል ጎይቶም ከበደ፣ አቶ ቸርነት ዳና፣ እሌኒ ብርሃን እና ሮመዳን ሙሳ መሆናቸውን የሃገር ውስጥ የዜና አውታር የሆነው ፋና ብሮድካስቲንግ ዘግቧል።

ተከሣሾቹ የተመሠረቱባቸው ሥልጣንን ያለአግባብ በመጠቀም ፈፅመዋቸዋል የተባሉ ሰባት የሙስና ወንጀል ክሦች ሲሆኑ ሦስቱ ተከሣሾች ዛሬ ችሎት ፊት በአካል እንደልቀረቡም ዘገባው ጠቁሟል።

ተከሳሾች መቃዋሚያቸውን ለማቅረብ ተለዋጭ ቀጠሮ እንዲሰጣቸው የጠየቁ ሲሆን አቃቤ ህግም ማስረጃዎቼ ናቸው ብሎ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ያቀረባቸው ሰነዶች ወደ አማርኛ ተተርጉመው በ10 ቀናት ውስጥ እንዲቀርቡ ችሎቱ አዝዞ ጉዳዩን ለጥር 17 / 2011 ዓ.ም መቅጠሩን ይኸው የፋና ዘገባ አመልክቷል።

ባህር ዳር

ምዕራብ ጎንደር ውስጥ በገንዳ ውኃ የተፈፀመውን ግድያ የሚያጣራ ቡድን ወደ አካባቢው እንደሚልኩ የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዚዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው አስታወቁ።

ምዕራብ ጎንደር ውስጥ በገንዳ ውኃ የተፈፀመውን ግድያ የሚያጣራ ቡድን ወደ አካባቢው እንደሚልኩ የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዚዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው አስታወቁ።

ርዕሰ-መስተዳድሩ ዛሬ ሰጥተውታል ያለውን መግለጫ ጠቅሶ ፋና ባሠራጨው ዘገባ የአንድ የኮንስትራክሽን ድርጅት መኪኖችን አጅበው ሲንቀሳቀሱ ከነበሩ የመከላከያ አባላት ጋር በተፈጠረው ግጭት በጉዳዩ ውስጥ ያልነበሩ ሰዎች ጭምር መገደላቸውን መጠቆማቸውን አመልክቷል።

በምዕራብ ጎንደር አካባቢ የእርስ በእርስ መገዳደል እየቀጠለ መሆኑን የተናገሩት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የክልሉ መንግሥት በአካባቢው ሰላም የማስከበር ኃላፊነቱን ለመወጣት ሕጋዊና ጠንካራ እርምጃ ለመውሰድ እንደሚንቀሳቀስ ማስታወቃቸውን ጠቁሟል።

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG