በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድን ለመደገፍ የተደረገው ሰልፍ

የደረሰውን አደጋ በተመለከተ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር አሚር አማንንና የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ዘይኑ ስለ ፍንዳታው ማብራሪያ ሰጥተውናል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ የጀመሩትን ለውጥ ለማበረታት በተጠራው በዛሬ ሰልፍ ላይ በእጅ ቦንብ የሰው ሕይወት መጥፋቱና 156 ሰዎች መቁሰላቸውን ዐንድ ሰው ደግሞ መሞቱን ባለሥልጣናቱ አስታውቀዋል።

የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር አሚር አማንንና የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ዘይኑ ጽዮን ግርማ አነጋግራቸዋለች።

“በጥንቃቄና በባለሞያ መከበር አለበት”- ኮሚሽነር ዘይኑ ጀማል
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:32 0:00

መስቀል አደባባይ

የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ ዛሬ ከቦንብ ጥቃት አመለጡ፣ 132 ዜጎች ቆስለዋል፡፡ ሌላ አንድ መሞታቸውን ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ ዛሬ ከቦንብ ጥቃት አመለጡ፣ 132 ዜጎች ቆስለዋል፡፡ ሌላ አንድ መሞታቸውን ተገልጿል፡፡ ለጠ/ሚኒስትሩ ድጋፍ ለመስጠት የተጠራውና በሚሊዮኖች የሚቆጠር ሕዝብ የተገኘበት ሰልፍም በአሳዛኝ ሁኔታ ተጠናቋል፡፡

ከዚህ የቦንብ ጥቃት በፊትና በኋላ አስተያያታቸውን የሰጡ የሰልፉ ተሳታፊዎች ግን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ የጀመሩት የለውጥ ጉዞ አይቀለበስም ብለዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ያህል ቁጥር ያለው ሕዝብ በገዛ ፈቃዱ አደባባይ የወጣላቸው የመጀመሪያ የኢትዮጵያ መሪ ናቸው፡፡

አሁን በደረሰን ዜና የአዲስ አበባ ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነርን ጨምሮ ዘጠኝ የፌደራልና የአዲስ አበባ ፖሊስ አመራሮችን አባላት ክፍተት አሳይተዋል፡፡ በሚል ቀጥTር ሥር አውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው መሆኑን የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈር ቤት ኃላፊ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሸዴ ማምሻውን ላይ ገልፀዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር አብይ አሕመድ ዛሬ ከቦንብ ጥቃት አመለጡ
please wait

No media source currently available

0:00 0:13:59 0:00

የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ ከቦንብ ጥቃት አመለጡ
please wait

No media source currently available

0:00 0:00:57 0:00

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG