በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

ዶ/ር አብይ ለፓርላማው ያደረጉት ንግግር

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ

ኢትዮጵያ ውስጥ እየተደረገ ያለው ይቅርታ መንግሥትን ጭምር መጥቀሙን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ ውስጥ እየተደረገ ያለው ይቅርታ መንግሥትን ጭምር መጥቀሙን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ተናግረዋል።

“ሽብር ሥልጣን ላይ ለመቆየት ኃይል መጠቀምንም ይጨምራል” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

“የታሠረን ሰው መግረፍ፣ ጭለማ ውስጥ ማስቀመጥና አካልን ማጉደል የእኛ የአሸባሪነት ተግባር ነው” ሲሉ ዶ/ር አብይ ዛሬ ለፓርላማው ባደረጉት ንግግር ግልፅ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ኢሕአዴግ ሥልጣን ላይ በቆየባቸው ባለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት በዚህ ደረጃ ኃላፊነት የወሰደ መሪ ከእርሣቸው በፊት አልታየም።

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ዶ/ር አብይ ለፓርላማው ያደረጉት ንግግር
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:47 0:00

ከፍያለው ተፈራ

"የሦስተኛ ዓመት ትምሕርቴን ጨርሼ ወለጋ ቤተሰቦቼንለመጠየቅ መንገድ ጀመርኩ። መስከረም 3/1999ዓ.ም ካደርኩበት አዲስ አበባ ካራ ቆሬ የምትገኝው እህቴ ቤት ወጥቼ ከጓደኞቼ ጋራ ወደ አውቶብስ ተራ መንገድ ጀመርን። አንድ ፌርማታ እንደሄድን ተኩስ ተከፈተብን። ሦስቱ ወዲያው ሞቱ። እኔ አንድ እግሬ ተጎዳ። ፖሊስ ሆስፒታል ገባሁና ጤነኛው እግሬ ተቆረጠ። ሁለቱም ተቆርጦ ከእነ ቁስሎቼ ወደ ማዕከላዊ ተወሰድኩ"- አርብ ዕለት ከእስር የተፈታው ከፍያለው ተፈራ የተናገረው ነው።

"አንድ እግሬ በጣም ተጎድቶ ነበር። አንድ እግሬ ደግሞ ጤነኛ ነበር። የመጀመሪያው እግሬ ታክሞ መዳን ሲገባው እኔን ሳያስፈቅዱና ሳያስፈርሙኝ ጤነኛውን እግሬን ሦስት ጊዜ ቆረጡት። ቆይቶ ደግሞ ግራ እግሬ ተቆረጠ"

(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ)

"ሁሉም ሰው በሕግ ፊት እኩል የሚሆንበትን ጊዜ ተስፋ አደርጋለሁ" - ከፍያለው ተፈራ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:11 0:00

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG