በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

የ2026ቱን የዓለም ዋንጫ ውድድሮች ካናዳ፣ ዩናይትድ ስቴትስና ሜክሲኮ በጋራ እንዲያዘጋጁ ፊፋ፣ ዓለምቀፉ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ወሰነ።

የ2026ቱን የዓለም ዋንጫ ውድድሮች ካናዳ፣ ዩናይትድ ስቴትስና ሜክሲኮ በጋራ እንዲያዘጋጁ ፊፋ፣ ዓለምቀፉ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ወሰነ። ውሳኔውን ከፊፋ አባል ሃገራት 134ቱ ሲደግፉት 65 ተቃውመዋል። ዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕም በፊፋ ምርጫ መደሰታቸው ተገልጿል። ዩናይትድ ስቴትስ ውድድሮቹን ስታዘጋጅ፣ ከ1994 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ይሆናል ማለት ነው።

በ2026ቱ የዓለም ዋንጫ የሚወዳደሩት ቡድኖች እንደ ቀድሞው 32 ሳይሆኑ 48 ይሆናሉ ተብሏል። 80 ከሚሆኑት የዓለም ዋንጫ ግጥሚያዎች - ዩናይትድ ስቴትስ 60ውን ስታስተናግድ፣ ካናዳና ሜክሲኮ እያንዳንዳቸው 10 ግጥሚያዎችን ብቻ ያስተናግዳሉ።

የዘንድሮው የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ውድድር ነገ የሚጀመረው፣ በአስተናጋጇ ሩሲያና ሳዑዲ ዓረቢያ ግጥሚያ ይሆናል። የ2022ቱን የምታስተናግደው ኳታር ትሆናለች።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የ2026 የዓለም ዋንጫ ውድድሮች አዘጋጅ ሀገሮች
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:04 0:00

በሀዋሳ ከተማ የጨምበላላ በዓል ላይ የተከሰተ ግጭት

በትናንትናው ዕለት በሐዋሳ ከተማ የፊቼ ጨምበላላ በዓል ዋዜማ ላይ በተፈጠረ ግጭት፤ የሰው ሕይወት መጥፋቱን ከ30 የበለጡ ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን በሐዋሳ ከተማ ያነጋግረናቸው ነዋሪዎች ገለፁ።

ሁለት የተለያዩ ነዋሪዎችን አነጋግረን ያጠናቀርነውን ዘገባ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

የሐዋሳው ግጭት በነዋሪዎች አንደበት
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:29 0:00

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG