በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

ፕረዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ በሰሜን ኮርያ ታስረው የነበሩት ሦስት አሜሪካውያን ተፈተው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖንፐዮ ጋር ወደ ሀገራቸው እየተመለሱ መሆናቸውን ገልፀዋል።

ፕረዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ በሰሜን ኮርያ ታስረው የነበሩት ሦስት አሜሪካውያን ተፈተው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖንፐዮ ጋር ወደ ሀገራቸው እየተመለሱ መሆናቸውን ገልፀዋል።

ትረምፕ ዛሬ ይህን ያስታወቁት “ሦስቱ በደህና የጤንነት ሁኔታ የሉ ይመስላል” ሲሉ በትዊተር ባስለታለፉት መልዕክት ነው። የተፈቱት አሜካውያን ሀገራቸው ሲገቡ እንደሚቀበሏቸውም ገልፀዋል።

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ትረምፕና የሰሜን ኮርያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ስለሚያደርጉት ንግግር ለመዘጋጀት ነበር ሰሜን ኮርያ የሄዱት።

ቶኒ ኪምና ኪም ሃክ ሶንግ የተባሉት አሜሪካውያን በፕዮንግያንግ የሳይንስና የቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ያስተምሩ ነበር። ባለፈው ዓመት የታሰሩት በፀረ መንግሥት ተግባር ተሳትፈዋል። መንግሥትን ለመገልበጥ ሞክረዋል በሚል ክስ ነበር።

ኪም ዶንግ ቹል የተባላው ደግሞ ከሦስት ዓመታት በፊት በሥለላ ተግባር ተከሶ የአሥር ዓመታት የከባድ ሥራ እሥራት ተበይኖበት ነበር።

የሶማልያ ባለሥልጣኖች እንደሚሉት አንድ አጥፍቶ ጠፊ በታችኛው ሸበሌ ክልል በሚገኝ ገበያ ላይ ባደረሰው ጥቃት ቢያንስ አሥራ አራት ሰዎች ተገድለው 15 ቆስለዋል። ክልሉ ከሶማልያ መዲና ሞቃዲሾ 90 ኪሎሜትር ርቆ ይገኛል።

የሶማልያ ባለሥልጣኖች እንደሚሉት አንድ አጥፍቶ ጠፊ በታችኛው ሸበሌ ክልል በሚገኝ ገበያ ላይ ባደረሰው ጥቃት ቢያንስ አሥራ አራት ሰዎች ተገድለው 15 ቆስለዋል። ክልሉ ከሶማልያ መዲና ሞቃዲሾ 90 ኪሎሜትር ርቆ ይገኛል።

በፀጥታ ጉዳይ የክልሉ ምክትል አስተዳዳሪ አብዲፋታሕ ሐጂ አብዱሌ አጥፍቶ ጠፊው ዒላማ ያደረገው ሰው የሚበዛበትን የጫት ገበያን ነው ብለዋል።

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG