በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

በሞያሌ ከተማ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በከተማዋ ያሉትን የኦሮምያንና የሶማሌ ክልልን የፀጥታ ኃይሎች ትጥቅ ማስፈታቱ ታውቋል።

በሞያሌ ከተማ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በከተማዋ ያሉትን የኦሮምያንና የሶማሌ ክልልን የፀጥታ ኃይሎች ትጥቅ ማስፈታቱ ታውቋል። ሀገር እያስተዳደረ የሚገኘዉ ኮማንድ ፖስት ሠክሬታርያት ትላንት በመግለጫው የታጠቁ ኃይሎች በከተማዋ ለሰው ሕይወት መጥፋት ተጠያቂ እንደሆኑ ገልጿል።

የሞያሌ ከተማ ነዋሪዎች ግን በክልል የፀጥታ ኃይሎች መፍታት ደስተኛ አለመሆነቸውን ነዉ የገለፁት።

በቦረና ዞን የሞያሌ ወረዳ የፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ንጋቱ ካሳሁን የነዋሪዎች ሥጋት ትክክል መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የመከላከያ ኃይል የሞያሌ ከተማ የፀጥታ ኃይሎችን ትጥቅ አስፈታ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:49 0:00

ሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ኃ.የተ.የግል.ማ

የለገደንቢ የወርቅ ማዕድን አደረሰ የተባለውን የአካባቢ ብክለትና የአስከተለውን ጥፋት በመቃወም ለሰልፍ በወጣ ሕዝብና በፀጥታ ኃይሎች መካከል በተፈጠረ ግጭት በአዶላ ከተማ ከትናንት እስከ ዛሬ አምስት ሰዎች መገደላቸውንና ሰባት መቁሰላቸውን ምንጮች ለቪኦኤ አስታወቁ፡፡

የለገደንቢ የወርቅ ማዕድን አደረሰ የተባለውን የአካባቢ ብክለትና የአስከተለውን ጥፋት በመቃወም ለሰልፍ በወጣ ሕዝብና በፀጥታ ኃይሎች መካከል በተፈጠረ ግጭት በአዶላ ከተማ ከትናንት እስከ ዛሬ አምስት ሰዎች መገደላቸውንና ሰባት መቁሰላቸውን ምንጮች ለቪኦኤ አስታወቁ፡፡

ዛሬ በከተማዋ መሃል የመከላከያ ሰራዊት መስፈሩንና ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ እንደሌለም ተነገረ፡፡ በአካባቢው በአጋዋዩ ወረዳ አይዲማ ከተማም ሕዝብ ለተመሳሳይ ተቃውሞ ወጥቶ እንደሰነበተ፣ የሚድሮክ ኩባንያ እንዲወጣ እየጠየቀ መሆኑ ታውቋል፡፡

በሌላ በኩል የማዕድን ነዳጅና ተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስቴር የሚድሮክ ጎልድ የለገደንቢ ፈቃድን ከዛሬ ጀምሮ ማገዱ ተሰማ፡፡

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

በአዶላ ግጭት አምስት ሰዎች መገደላቸውንና ሰባት መቁሰላቸው ተጠቆመ
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:34 0:00

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG