በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

የረዥም ጊዜ የሞዛምቢክ ሽምቅ ተዋጊና የተቃዋሚ መሪ ድንገኛ ሞት፤ በሀገሪቱ ከፍተኛ ድንጋጤና ሥጋት መፍጠሩን ተንታኞች አመለከቱ።

የረዥም ጊዜ የሞዛምቢክ ሽምቅ ተዋጊና የተቃዋሚ መሪ ድንገኛ ሞት፤ በሀገሪቱ ከፍተኛ ድንጋጤና ሥጋት መፍጠሩን ተንታኞች አመለከቱ።

በ65 ዓመታቸው ትናንት ሐሙስ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት አፎንሶ ደላካማ ሞዛክቢክ ውስጥ ለሚካሄዱ እንቅስቃሴዎች የሩቅ ተመልካች አልነበሩም፤

የሬናሞ ሽምቅ ተዋጊ ቡድን ለ16 ዓመታት ያካሄደውንና እእአ በ1992 የተጠናቀቀውን የርስ በርስ ጦርነት መርተዋል፤ ሬናሞን ከደፈጣ ተዋጊነት ወደ ተቃዋሚ ፓርቲነት አድርሰዋል፤ አንዴም አልቀናችውም እንጂ፣ አምስት ጊዜ ለፕሬዚደንትነት ተወዳድረዋል።

ከመሞታቸው ጥቂት ጊዜያት አስቀድሞም፣ ከፕሬዚደንቱ ፊሊፔ ኑውሴ ጋር የሰላም ስምምነት ለመድረስ ጥሩ ሂደት ላይ እንደነበሩም ታውቋል።

የዳላካማን» ሞት፣ ፕሬዚደንት ኑውዌ ናቸው ይፋ ያደረጉት።

ጋዜተኛና ተንታኝ ፎርናንዶ ሊማ “አገሪቱ ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ ወድቃለች” ይላሉ።

“እኒህን መሰል ሰው ማጣት፣ ይህን ዓይነት ብርቱና አታጋይ ሰው ማጣት፣ ትልቅ በጣም ትልቅ ኪሳራ ነው» ሲሉ ለቪኦኤ የተናገሩት ተንታኙ ፌርናንዶ፣ «ስለሆነም አሁን ጠቅላላ የአገሪቱ ሕዝብ፣ በድን ሆኗል ብል ስህተት አይሆንም” ሲሉ የኃዘኑን ከፍተኛነት ገልጸዋል።

ሌሎች ተንታኞችም ተመሳሳይ ስሜት ገልፀው፣ በተለይም፣ የደኅንነት ጥናት ተቋም ባልደረባ የሆኑት ተንታኝ ሌስል ሎው ቫንድራን ለቪኦኤ በሰጡት ቃል፣ "የአፎንሶ ደላካማ ድንገኛና ያልተጠበቀ ሞት የተወው ክፍተት አለ፣ ያም፣ ተጀምሮ ያልተቋጨው የሰላም ስምምነት ነው" ብለዋል።

አፍሪካ በጋዜጦች

አፍሪካ በጋዜጦች የተሰኘው ፕሮግራማችን ስለ አፍሪካ ከተፃፉት የተወሰኑትን ጨምቆ ያቀርባል።

አፍሪካ በጋዜጦች የተሰኘው ፕሮግራማችን ስለ አፍሪካ ከተፃፉት የተወሰኑትን ጨምቆ ያቀርባል። ኢትዮጵያና ሱዳን ፖርት ሱዳንን አብረው ለማልማት እንደተስማሙ ታወቀ፣ ኢትዮጵያና ጂቡቲ በመንግሥት የንግድ ተቋማት የአክስዮን ድርሻ ለመለዋወጥ እንደተስማሙ ተገለፀ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት የወታደራዊው ኃይል የማዳበርያ ኩባንያ ኩንትራት ሊሰርዝ ይችላል ተባለ የሚሉትን ርዕሶች ነው በዛሬው አፍሪካ በጋዜጦች ቅንብራችን የምንመለከተው።

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

አፍሪካ በጋዜጦች
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:38 0:00

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG