በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

ኬንያ

ምሥራቅ አፍሪካ አሁንም ለጋዜጠኞች አስቸጋሪ ቦታ እንደሆነ ለመረጃ ነጻነት የሚሟገተው አርቲክል 19 አስታወቀ።

ምሥራቅ አፍሪካ አሁንም ለጋዜጠኞች አስቸጋሪ ቦታ እንደሆነ ለመረጃ ነጻነት የሚሟገተው አርቲክል 19 አስታወቀ።

የሰብዓዊ መብት ተከራካሪዉ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ዛሬ በኬንያ ናይሮቢ የመረጃ ነፃነት ቀን መታሰብያ ፕሮግራም ላይ ባቀረበው ሪፖርት፣ የኬንያ የ2010 ምርጫ ተከትሎ በጋዜጠኞች ላይ የሚደርስ ጥቃት መብዛቱን፥ ታንዛኒያ በጦማሪዎች ላይ ክፍያን የሚያስገድድ ህግ ማፅደቋና ኡጋንዳ ደግሞ በቅርቡ የማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ላይ ታሪፍ ልትጥል ማሳወቋ፣ የመረጃ ነፃነት በምሥራቅ አፍሪካ ይባስኑ እንዲያሽቆለቁል ማድረጉን የአርቲክል 19 ምሥራቅ አፍሪካ ቦርድ ሰብሳቢ ጆን ጋሺ ተናግረዋል።

በዝግጅቱ ላይ በቅርቡ ከእሥር የተለቀቀዉ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ለታዳሚዎች በምሥራቅ አፍሪካ ነፃ ፕሬስ እንዳይተገበር እንቅፋት የሆኑት የሀገር መሪዎች ሲል ተናግረዋል።

ኬንያ
ኬንያ

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

"ምሥራቅ አፍሪካ ለጋዜጠኞች አስቸጋሪ ሥፍራ ነው" - የአርቲክል 19 ሪፖርት
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:33 0:00

ድንበር የለሽ ሪፖርተሮች - አር. ኤስ.ኤፍ. የሚባለው የፕሬስ ነፃነት ተሟጋች ቡድን ኢትዮጵያን በፕሬስ ነፃነት ይዞታዋ ከ180 ሀገሮች 150ኛ ቦታ ላይ አስቀምጧታል።

ኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን ዝም ለማሰኘት የምትጠቀምበትን አፋኝ ሕጎቿን ካላሻሻለች፣ የመጻፍና የመናገር ነፃነትን የምታፍንበትን የእጅ አዙር አስጨናቂ አካሄድ ካላስተካከለች፣ጋዜጠኞችን ከእስር መልቀቋ ብቻ ነፃ ሀገር ሊያሰኛት አይችልም ሲል ዋና ቢሮውን በዚህ በዩናይትድ ስቴትስ ያደረገው የጋዜጠኞች ደህንነት ተሟጋቹ በእንግሊዘኛው ምሕፃረ ቃል (CPJ) አስታወቀ።

“ጋዜጠኞችን መፍታት ብቻውን የፕሬስ ነፃነትን አያረጋግጥም” - ጋዜጠኞችና ሲፒጄ
please wait

No media source currently available

0:00 0:12:46 0:00


ኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን ዝም ለማሰኘት የምትጠቀምበትን አፋኝ ሕጎቿን ካላሻሻለች፣ የመጻፍና የመናገር ነፃነትን የምታፍንበትን የእጅ አዙር አስጨናቂ አካሄድ ካላስተካከለች፤ ጋዜጠኞችን ከእስር መልቀቋ ብቻ ነፃ ሀገር ሊያሰኛት አይችልም ሲል ዋና ቢሮውን በዚህ በዩናይትድ ስቴትስ ያደረገው የጋዜጠኞች ደህንነት ተሟጋቹ ድርጅት ሲፒጄ አስታወቀ።

ሲፒጄ በእስር ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞችን ቁጥር ቀምሮ ይፋ በሚያደርግበት ዓመታዊ ሪፖርቱ በአውሮፓውያን ዘመን አቆጣጠር በ2017 በዓለም ዙሪያ 259 ጋዜጠኞች ታስረው እንደሚገኙና ከዚህም ውስጥ ኢትዮጵያ 16 ጋዜጠኞችን በማሰር በአፍሪካ ከግብፅና ከኤርትራ ቀጥሎ ሦስተኛ አፋኝ ሀገር ብሏት ነበር።

በእስር ላይ የነበሩት 16 ጋዜጠኞችና የኢንተርኔት ጸሐፊዎች ከእስር ተለቀዋል። ለመጀመሪያ ጊዜም የኢትዮጵያ እስር ቤቶች ከጋዜጠኞችና ከጸሐፊዎች ነፃ ሆነዋል። የእነዚህ ጋዜጠኞች ከእስር መለቀቅ ኢትዮጵያን ከፕሬስ ነፃነት አፋኝነት የመጀመሪያ ተርታ ውስጥ ያወጣታል ወይ? የሚል ጥያቄ ለጋዜጠኞች ደህንነት ተሟጋቹ ድርጅቱ (ሲፒጄ) የአፍሪካ ቀንድ ተከራካሪ አንጄላ ኲንታል ጥያቄ አቅርቤ ነበር። አጭር መልስ ሰጥተውኛል “በፍፁም አያወጣትም” የሚል።

ምክኒያታቸውን ሲያስረዱ፤ “ጋዜጠኞችና የጦማር ጸሐፊዎችን መፈታት እንደበጎ እመርታ እንመለከተዋለን። የመገናኛ ብዙሃን ነጻነት ግን ጋዜጠኞችን በማሰርና በመፍታት ብቻ አይረጋገጥም። ኢትዮጵያን በተመለከተ የሚያሳስበን በመገናኛ ብዙሃኑ ላይ የተጣለው አፋኝ ሕግ ነው።ለመንግሥቱ የምናቀርበው ጥሪ ቀድሞውኑም ጋዜጠኞቹን ለማሰር የዋለውን ሕግ ማሻሻልና ይሄን ዕድል ተጠቅመው አመቺ ሁኔታዎችን እንዲፈጥሩ ነው።” ብለዋል።

የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅቱ አጥኝ አንጀላ ኩዊንታል የጠቀሱትና ሊለወጥ ይገባዋል የሚሉት ሕግ ከዘጠኝ ዓመታት በፊት የጸደቀው የጸረ-ሽህብር ህግ ነው። የኢትዮጵያ መንግሥት የሕዝቡን ደህንነት ለማስጠበቅ ያወጣሁት ነው ቢልም፤ የዚህ ሕግ አንቀጾች እየጠተቀሱ ጋዜጠኞች፣ ጸሐፊዎችና የፖለቲካ ተቀናቃኞች ሲታሰሩ መቆየታቸውን ይጠቅሳሉ።

“ከሕግ ማሻሻዎች በተጨማሪም የሚያሳስበን ነጻና ገለልተኛ የመገናኛ ብዙሃን መጥፋት ነው። ባለፉት ሦስት ዓመታት በርካታ የመገናኛ ብዙሃን ተዘግተዋል ወይንም ሕትመታቸውን አቋርጠዋል። እነዚህ የተዘጉ የመገናኛ ብዙሃን አልተከፈቱም። በተደጋጋሚ የኢንተርኔት አግልግሎት መቋረጡና ሌሎች ችግሮችም ይታያሉ።” ያሉት የደህንነት ተሟጋቹ ድርጅቱ (ሲፒጄ) የአፍሪካ ቀንድ ተከራካሪ አንጄላ ኲንታል ናቸው።

(ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ)

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG