በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ በአሶሳ

የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ

ኢትዮጵያውያን በየትኛውም የሀገሪቱ አካባቢ ተዘዋውሮ የመሥራት መብት ጥያቄ ውስጥ ሊገባ እንደማይገባው፣ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ አሳሰቡ፡፡

ኢትዮጵያውያን በየትኛውም የሀገሪቱ አካባቢ ተዘዋውሮ የመሥራት መብት ጥያቄ ውስጥ ሊገባ እንደማይገባው፣ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ አሳሰቡ፡፡ ጠ/ሚኒስትሩ ይሔን ያሳሰቡት በቤንሻንጉል ጉምዝ ርዕሰ ከተማ አሶሳ ከነዋሪዎች ጋር ባደረጉት ውይይት ነው፡፡

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ በአሶሳ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:27 0:00

የሊቢያ ባለሥልጣናት በሰጡት መግለጫ፣ ዋና ከተማዋ ትሪፖሊ ውስጥ በሚገኘው በሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን ላይ በተካሄደ ጥቃት፣ አሥራ ሁለት ሰዎች መሞታቸውን አስታወቁ።

የሊቢያ ባለሥልጣናት በሰጡት መግለጫ፣ ዋና ከተማዋ ትሪፖሊ ውስጥ በሚገኘው በሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን ላይ በተካሄደ ጥቃት፣ አሥራ ሁለት ሰዎች መሞታቸውን አስታወቁ።

አጥቂዎቹ ህንጻውን ደርምሰው ሲገቡ፣ ከመካከላቸው አንዱ በራሱ ላይ ፍንዳታ በማድረስ ነው አጠቃላይ አደጋው የተፈፀመው።

ለጥቃቱ፣ እራሱን እስላማዊ መንግሥት ብሎ የሚጠራው አማፂ ቡድን፣ ኃላፊነት ወስዷል።

የቀድሞው መሪ ሞአመር ጋዳፊ እአአ በ2011 ከሥልጣን ከተወገዱ ወዲህ፣ ሊቢያ፣ በነውጥ ውስጥ ትገኛለች። በአሁኑ ወቅትም፣ እያንዳንዳቸው በተደራጁ ሚሊሽያዎች በሚደገፉ በሁለት ተቀናቃኝ መንግሥታት ተከፍላለች።

በአመራር ረገድ ግን፣ ዋና ከተማዋ ትሪፖሊ ውስጥ፣ አንድ ዓለማቀፍ እውቅና ያለው አስተዳደር እንደተመሰረተም ይታወቃል።

ዛሬ ሊቢያ ውስጥ ያለው አለመረጋት፣ እንደ /አይሲስ/ የመሰለ ሽብርተኛ ቡድን መቀመጫ እንዲያገኝ ሁኔታዎችን ያመቻቸ መሆኑ ይታወቃል።

ሊቢያ ውስጥ በሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን ላይ በተካሄደ ጥቃት ሰዎች ተገደሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:00:13 0:00

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG