በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

“ወጥቼ አልወጣሁም"
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:55 0:00

በቅርቡ ለንባብ የበቃ መጽሐፍ ነው። “ወጥቼ አልወጣሁም” ይላል ርዕሱ። ከየት እና ለምን? ለመሆኑ ባለ ታሪኩስ ማን ይሆን?

የመጽሃፉ አብይ ትኩረት በሆነው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ከአራት አሥርታት የዘለቀ የአንድ ትውልድ ፖለቲካ ትላንት እና ዛሬን ለመቃኘት በፈቀዱ መጣጥፎቹ “ልጠየቅ?” የሚል ይመስላል .. ደራሲው አቶ ያሬድ ጥበቡ።

በተከታዩ ቅምሻ ወጋችን የመጽሃፉን መሄጃ፤ የታሪኩን መፍሰሻ ቦይ መልከት እናድርግ። ወጥቼ አልወጣሁም’ን እንተዋወቅ።

ለጥያቄዎ መልስ

በሚቺጋን ግዛት በኬተሪንግ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ ፕሮፌሰር ሕዝቅኤል ገቢሳ፤ ከኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያና የፖለቲካ ተንታኝ አቶ ውብሸት ሙላት

የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ወደ ሥልጣን መምጣት “ሰላም በማጣት ተቃውሳ የነበረችውን ኢትዮጵያን አረጋግቷል” ብለው ብዙዎች ይስማማሉ።

የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ወደ ሥልጣን መምጣት “ሰላም በማጣት ተቃውሳ የነበረችውን ኢትዮጵያን አረጋግቷል” ብለው ብዙዎች ይስማማሉ።

ይሁን እንጂ እርሳቸውን ወደ ሥልጣን ያመጣቸውን የሕዝብ የፖለቲካ ጥያቄ መመለስ ገና አለመጀመራቸውን የሚናገሩም አሉ።

የዶክተር አብይ አሕመድ አስተዳደር ሃገሪቱን በማረጋጋት ተስፋን የፈነጠቀ ቢሆንም የፖሊሲ ወይም መዋቅራዊ ለውጥ ያልታየበት፣ እንዲያውም እርሣቸው ወደ ሥልጣኑ ከመዝለቃቸው በፊት ለሃገር ሥጋት የነበሩ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁና የመከላከያ ሠራዊቱ ሕዝብን በየክልሉ ዒላማ ማድረግ አሁንም ያሉ መሆኑ ተነግሯል።

የአድማጮችን ጥያቄዎች የሚያስተናግዱት ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በሚቺጋን ግዛት በኬተሪንግ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ ፕሮፌሰር ሕዝቅኤል ገቢሳ፤ እንዲሁም ከኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያና የፖለቲካ ተንታኝ አቶ ውብሸት ሙላት ናቸው።

ምሁራኑ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ያለፉ ሁለት ወራት ክንውን በመገምገም ይጀምራሉ።

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ለጥያቄዎ መልስ -ክፍል አንድ
please wait

No media source currently available

0:00 0:17:03 0:00

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG