በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

የሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩ መታገል እጅግ አደገኛ በሆነባት በፓኪስታን የመብት ጠበቆች የዲጂታል ጥቃቶች እየደረሱባቸው ነው ሲል አምነስቲ ኢንተርናሽናል ዛሬ አስታውቋል።

የሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩ መታገል እጅግ አደገኛ በሆነባት በፓኪስታን የመብት ጠበቆች የዲጂታል ጥቃቶች እየደረሱባቸው ነው ሲል አምነስቲ ኢንተርናሽናል ዛሬ አስታውቋል።

ዓለምቀፉ የመብቶች ድርጅት ለአራት ወራት ያካሄደውን ምርመራ ውጤት ይፋ ሲያደርግ፣ ጥቃቶቹን “የክፋትና ተንኮል ዘመቻ” ሲል አውግዟል።

መቀመጫቸውን በፓኪስታን ያደረጉ ግለሰቦችና ኩባንያዎች ኔትወርክ በድብቅ እነዚህን የሣይበር ጥቃቶች ለመፈጸም፣ የሃሰት ፌስቡክና ጉግል አካውንት ይጠቀማሉ ሲልም አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታውቋል።

በሶማሊያ ፑንትላንድ አስተዳደሮች ባጨቃጫቂው የሰሜን ሡል ግዛት እንደገና የጀመሩትን ውጊያ እንዲያቆሙ የሶማሊያ መንግሥት ዛሬ ባወጣው መግለጫ ጥሪ አስተላልፏል።

በሶማሊያ ፑንትላንድ አስተዳደሮች ባጨቃጫቂው የሰሜን ሡል ግዛት እንደገና የጀመሩትን ውጊያ እንዲያቆሙ የሶማሊያ መንግሥት ዛሬ ባወጣው መግለጫ ጥሪ አስተላልፏል።

ተፋላሚዎቹ ወገኖች ቅዱሱን የሙስሊሞች የረመዳን ወር ፆም መጀመር ምክንያት በማድረግ በአስችኳይ ተኩስ ሊያቆሙ ይገባል ሲሉ - ፕሬዘዳንት ሞሃመድ አብዱላሂ ሞሃመድ ተናግረዋል።

በሱማልያ ሕዝቦች መካከል በዚህ ቅዱስ ወር ወቅት ሌላ ደም መፋሰስ ማየቱ ያሳዝናል ያለው የፕሬዛዳንት ሞሃመድ አብዱላሂ ሞሃመድ መግለጫ የአስተዳደሮቹ የፖለቲካና የሃይማኖት መሪዎች - የተኩስ አቁም ድርድሮችን እንዲሸመግሉ ጥሪ ያቀርባል።

በሶማሊያ ፑንትላንድ መካከል አዲስ ባገረሸው ውጊያ በትንሹ ስድሥት ወታደሮች ከሁለቱም ወገን መገደላቸውን በርካታ ምንጮች ገልፀዋል። ተኩሱን በመጀመር አንዱ ሌላውን ይወነጅላል።

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG