በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

ዶ/ር ፍቅሩ ማሩና አቶ አግባው ሰጠኝ

ከእስር ከተለቀቁት መካከል ዶ/ር ፍቅሩ ማሩንና አቶ አግባው ሰጠኝን አነጋግረናቸዋል። አቶ አግባው ሰጠኝ ዛሬም ድረስ ጨለማ ቤት ተዘግቶባቸው የሚገኙት ጓደኞቹ በሙሉ እስካልተፈቱ ደስተኛ እንዳልሆነ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግሯል። በምርመራ ወቅት በምስማር ከመቸንከር ጀመሮ አሰቃቂ ድብደባ እንደተፈፀመበት ተናሯል።

በእስር ላይ እያሉ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤትን በማቃጣል ክስ ቀርቦባቸው ከነበሩ 38 ተከሳሾች መካከል የልብ ሃኪሙና የ “አዲስ የልብ ሕክምና ማዕከል” ባለቤት ዶ/ር ፍቅሩ ማሩን ጨምሮ አራቱ በተጨማሪም በዚሁ ጉዳይ በሌላ መዝገብ ከተከሰሱት መካከል አንድ ሰው በአጠቃላይ በድምሩ አምስት ሰው በዛሬው ዕለት ከእስር ተፈተዋል።

ከእስር ከተለቀቁት መካከል የሰማያዊው ፓርቲ የጎንደር ጽ/ቤት አስተባባሪ አቶ አግባው ሰጠኝ ዛሬም ድረስ ጭለማ ቤት ተዘግቶባቸው የሚገኙት ጓደኞቹ በሙሉ እስካልተፈቱ ደስተኛ እንዳልሆነ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግሯል።

(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ)

ዶ/ር ፍቅሩ ማሩን ጨምሮ አምስት ሰዎች በዛሬው ዕለት ከእስር ተለቀቁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:37 0:00

ጠ/ሚኒስትር አብይ አሕመድ

ጠ/ሚኒስትር አብይ አሕመድ የሀገር ምጣኔ ኃብታዊ እድገት ተጨባጭ ከሆነ የሕዝብ ኑሮ እድገት ጋር ሊያገናዝብ እንደሚገባ አመለከቱ፡፡

ጠ/ሚኒስትር አብይ አሕመድ የሀገር ምጣኔ ኃብታዊ እድገት ተጨባጭ ከሆነ የሕዝብ ኑሮ እድገት ጋር ሊያገናዝብ እንደሚገባ አመለከቱ፡፡

የመንግሥት አሰራር ግልፅ እና ለህዝብ ክፍት እንዲሆን አሳሰቡ፡፡ በውጭ ሀገር ባንኮች ገንዘብ ያከማቹ ባለሥልጣናት የሒሳብ መዝገብ እየተጣራ እንደሆነም ገለፁ፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

"የሀገር ምጣኔ ኃብታዊ እድገት ተጨባጭ ከሆነ የሕዝብ ኑሮ እድገት ጋር ሊያገናዝብ ይገባል" - ጠ/ሚኒስትር አብይ አሕመድ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:18 0:00

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG