በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

ፎቶ ፋይል

ዩናይትድ ስቴትስ በአሉሚነምና በብረት ምርቶች ላይ በመላ ዓለም በጣለቻቸው አዳዲስ ታሪፎች ምክንያት ለደረሰባት ጉዳት ማካካሻ እንድትከፍል ሩሲያ ጠየቀች።

ዩናይትድ ስቴትስ በአሉሚነምና በብረት ምርቶች ላይ በመላ ዓለም በጣለቻቸው አዳዲስ ታሪፎች ምክንያት ለደረሰባት ጉዳት ማካካሻ እንድትከፍል ሩሲያ ጠየቀች።

164 አባል ሃገሮች ካሉት ዓለም የንግድ ድርጅት ኃያል አቅም ያላቸው ምጣኔ ሃብቶች አንዷ ነች የምትባለው ሩሲያ እንዲህ ዓይነቱን ጥያቄ ስታቀርብ ሦስተኛዋ ሃገር መሆኗ ታውቋል።

ቻይና፣ የአውሮፓ ኅብረትና ሕንድም ዋሺንግተን የወሰደችውን የአዲስ ታሪፍ እርምጃ የሃገር ውስጥ ምርቶችን ከገቢ ንግድ ለመከላከል ስትል ያደረገችው መሆኑን በመግለፅ የተቃወሙት ሲሆን እንዲህ ዓይነቱ አድራጎት በዓለሙ የንግድ ድርጅት ውል መሠረት ታሪፍ ጣዩ ሃገር ካሣ እንዲከፍል የሚያስገድድ መሆኑ ተገልጿል።

ከዚያ ሃሣብ ጋር እንደማይስማማ የሚገልፀው የትረምፕ አስተዳደር ግን ታሪፉን የጣለው በብሄራዊ ደኅንነት ምክንያቶች መሆኑን እያሳወቀ ነው።

የሩሲያ ጥያቄ በዓለሙ የንግድ ደርጅት ተቀባይነት ያግኝ አያግኝ ገና ግልፅ አይደለም።

ንግሥት ዳግማዊት ኤልሣቤጥ

በታላቋ ብሪታንያ ንግሥት ዳግማዊት ኤልሣቤጥ የሚመራው የጋራ ብልፅግና ሃገሮች መሪዎች ጉባዔ ለንደን ላይ እየተካሄደ ነው።

በታላቋ ብሪታንያ ንግሥት ዳግማዊት ኤልሣቤጥ የሚመራው የጋራ ብልፅግና ሃገሮች መሪዎች ጉባዔ ለንደን ላይ እየተካሄደ ነው።

በዛሬው ጉባዔ ላይ የጋራ ብልፅግና ኅብረቱን የወደፊት ዕጣ ፈንታ የሚመለከቱ ሃሣቦች የተንፀባረቁ ሲሆን የድርጅቱን አስፈላጊነትና የቀድሞዪቱ ገዥ ብሪታንያ ልትጫወት ስለምትችለው ሚና በውይይቱ ላይ የተነሱ ጥያቄዎች መሆናቸው ታውቋል።

ጉባዔው ሲከፈት ግርማዊትነታቸው ባደረጉት ንግግር የጋራ ብልፅግናው አመራር ወደፊትም በእርሣቸው ቤተሰብ እጅ ውስጥ እንዲቆይ እንደሚፈልጉ ጠቁመዋል።

የጋራ ብልፅግናው ማኅበር “ለመጭ ትውልዶችም መረጋጋትና ቀጣይነትን እንዲያበረክት ከልቤ እመኛለሁ፤ አንድ ቀን የዌልስ ልዑልም ኅብረቶቻችንንና ሥራዎቻችንን ከፍ በማድረግና በማጠናከር የእኔ አባት በ1949 ዓ.ም. ጀምረውት የነበረውን እጅግ ጠቃሚ ተግባር እንዲቀጥል ለማድረግ እወስናለሁ፤ ” ብለዋል ንግሥት ኤልሣቤጥ በኪንግሃም ቤተመንግሥት ውስጥ ለተሰበሰጡት መሪዎች።

ኮመንዌልስ ወይም የጋራ ብልፅግናው ማኅበር የተመሠረተው በዓለም ላይ ተንሠራፍቶ የነበረው የታላቋ ብሪያንያ ንጉሠ-ነገሥታዊ ቅኝ አገዛዝ ሲፈራርስ ሲሆን ዛሬ 53 አባል መንግሥታት ያሉት የወደፊት ሕልውናው እያንገራገረ እንደሆነ የሚታማ ድርጅት ነው።

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG