በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

ቀጣዩ የኩባ ፕሬዚዳንት

ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ሚጌል ዳያዜል ካኔል ቤርሞዴዝን

ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ሚጌል ዳያዜል ካኔል ቤርሞዴዝን ለቀጣዩ ኩባ ፕሬዚዳንትነት ብቸኛው ዕጩ አድርጎ ማቀረቡን የኩባ መንግሥት አስታወቀ።

ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ሚጌል ዳያዜል ካኔል ቤርሞዴዝን ለቀጣዩ ኩባ ፕሬዚዳንትነት ብቸኛው ዕጩ አድርጎ ማቀረቡን የኩባ መንግሥት አስታወቀ።

ዕርምጃው ለኮምኒስቷ ሀገር፣ ከካስትልሮ ቤተሰብ ውጭ በሥልሳ ዓመታት ጊዜ ውስጥ የመጀመሪያው ፕሬዚዳንት ያደርጋቸዋል።

ተቀዳሚው ምክትል ፕሬዚዳንት የሀገር መምራቱን መንበር የሚረከቡት የሀገሪቱ ብሔራዊ ጉባዔ ዕጩውን ያፀደቀ እንደሆን ብቻ ነው። ይሁንና ጉባዔው በታሪኩ እስካሁን በዕጩነት የቀረቡለትን በሙሉ በማፅደቅ ነው የሚታወቀው።

ባልተለመደ አሠራር የሕግ አርቃቂው ምክር ቤት በሁለት ቀናት ውስጥ አዲሱን ፕሬዚዳንት ይመርጥ እና በማግሥቱ ሃሙስ ያሁኑን ፕሬዚዳንት ራውል ካስትሮን እንዲተኩ ያደርጋል።

ከዚህ ቀደም ምክር ቤቱ ዕጩውን ይመርጥና በዚያኑ ዕለት አፅድቆ የተተውን ማንነት ይፋ ያደርጋል።

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባት ሄዜር ኖሬት የኩባን ውሳኔ አስመልክቶ በሰጡት አስተያየት፣ ሽግግሩ ዲሞክራሲያዊ ባለመሆኑ የትረምፕ አስተዳደር “በእጅጉ አሳሳቢ” አድርጎ ይወስደዋል ብለዋል።

ሞያሌ

ትላንት ጠዋት በሞያሌ በደረሰዉ ግድያ የተጠረጠሩ ሁለት ሰዎች በፌደራል ፖሊስ ቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የሞያሌ ወረዳ ፖሊስ አስታወቀ።

ትላንት ጠዋት በሞያሌ በደረሰዉ ግድያ የተጠረጠሩ ሁለት ሰዎች በፌደራል ፖሊስ ቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የሞያሌ ወረዳ ፖሊስ አስታወቀ። ኮማንደር ነጋ ስርቢ በሁለቱ ሰዎች አሁንም ከሌላ የእጅ ቦምብ ጋር እንደተያዙ ለአሜርካ ድምፅ ተናግረዋል።

የሞያሌ ከተማ አሁንም ውጥረት እንደሰፈነበት ይነገራል፡፡ በከተማዋ ብዙም እንቅስቃሴ እንደሌለ ነዋሪዎች ተናግረዋል። በትናንቱ ጥቃት የሞቱ ሰዎች ቁጥር አራት ደርሷል - ዛሬም ለሞቱት የቀብር ሥነ ሥርዓት መፈፀሙን የአካባቢው አስተዳዳሪ ገልፀዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

በሞያሌ በደረሰዉ ግድያ የተጠረጠሩ ሁለት ሰዎች ተያዙ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:11 0:00

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG