በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

ዛሬ ጠዋት ተፈጥሮ የነበረው የበርካታ በረራዎች መስተጓጎል ችግር እልባት ማግኘቱንና የተለመደው ሥራ መቀጠሉን የኢትዮጵያ ሲቪል አቬሽን ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡

ዛሬ ጠዋት ተፈጥሮ የነበረው የበርካታ በረራዎች መስተጓጎል ችግር እልባት ማግኘቱንና የተለመደው ሥራ መቀጠሉን የኢትዮጵያ ሲቪል አቬሽን ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡ ችግሩ የተፈጠረው በህመም ምክንያት የቀሩ ባልደረቦቻቸው ቦታ ጭምር ሸፍነው እንዲሰሩ የተጠየቁ ሁለት የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ትዕዛዝ ባለመቀበላቸው ነው ብሏል - የኢትዮጵያ አየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ማኅበር እስከአሁን በጉዳዩ ላይ መግለጫ አልሰጠም ሊቀመንበሩን ለማግኘት እያደረግን የነበረው ጥረትም አልተሳካም፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

በኢትዮጵያ የአውሮፕላን በረራዎች መስተጓጎል
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:13 0:00

ሞያሌ

ዛሬ ረፋድ በሞያሌ ተከስቶ በነበረዉ አለመረጋጋት 3 ሰዎች ሞተዉ ከ 50 በላይ የሚሆኑት ከባድ ና ቀላል የመቁሰል አደጋ እንደደረባቸዉ ነዋሪዎች ለአሜርካ ድምፅ ተናግረዋል። ግጭቱ የተከሰተዉ በሞያሌ 02 ቀበሌ መናኸርያ በሚባል ቦታ ሲሆን አንድ የእጅ ቦምብ መወርወሩንና ሽጉጥ መተኮሱን ነዋሪዎች ይናገራሉ።

ዛሬ ረፋድ በሞያሌ ተከስቶ በነበረዉ አለመረጋጋት 3 ሰዎች ሞተዉ ከ 50 በላይ የሚሆኑት ከባድ ና ቀላል የመቁሰል አደጋ እንደደረባቸዉ ነዋሪዎች ለአሜርካ ድምፅ ተናግረዋል። ግጭቱ የተከሰተዉ በሞያሌ 02 ቀበሌ መናኸርያ በሚባል ቦታ ሲሆን አንድ የእጅ ቦምብ መወርወሩንና ሽጉጥ መተኮሱን ነዋሪዎች ይናገራሉ።

የሞያሌ ሆስፒታል ጠቅላላ ሕክምና ዶ/ር ንጉሴ አዱኛ በሆስፒታላቸው ለመታከም ከመጡ ሰዎች የ1 ሰዉ ሕይወት ወዲያዉ ማለፉን ተናግረዋል። የሞያሌ 02 ቀበሌ አስተዳደር አቶ ኩሉ ገልገሎ ሦስት ሰዎች መሞታቸውን አረጋግጠው፣ ድርጊቱን የፈፀሙ ሰዎች ግን በህግ ቁጥጥር ሥር አለመዋላቸዉን ለአሜርካ ድምፅ ተናግረዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

በሞያሌ የእጅ ቦምብ ተወርውሮ ሦስት ሰዎች ሞቱ፤ ከ50 በላይ ቆስሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:11 0:00

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG