በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

አቶ አታላይ ዛፌ

ጥያቄያቸው የማንነት እንጂ የልማት እንዳልሆነ በቅርቡ ከእስር የተፈቱት የወልቃይት ኮሚቴ አመራር አባላት አቶ አታላይ ዛፌ ለአሜሪካ ድምፅ ገለጹ።

ጥያቄያቸው የማንነት እንጂ የልማት እንዳልሆነ በቅርቡ ከእስር የተፈቱት የወልቃይት ኮሚቴ አመራር አባላት አቶ አታላይ ዛፌ ለአሜሪካ ድምፅ ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ መቀሌ ተጉዘው ከሕዝብ ጋራ ባደረጉት ውይይት የወልቃይትን የአርማጮ ጥያቄ የልማት መሆኑን በመናገራቸው እጅግ ማዘናቸውንም ተንግረዋል።

ከአቶ አታላይ ዛፌ ጋራ የተደረገውን ቃለምልልስ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

"ጥያቄያችን የማንነት ነው"- አቶ አታላይ ዛፌ
please wait

No media source currently available

0:00 0:12:16 0:00

በኦሮሚያ ክልል በኢሬቻ በዓል ላይ የነበረ ተቃውሞ

በኢትዮጵያ በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በትግራይና በኮንሶ የታሰሩ እስረኞችን በተመለከተ የተጠናቀረ ዘገባ።

ኢትዮጵያና እስረኞቿ
please wait

No media source currently available

0:00 0:19:51 0:00

ገዢው የኢትዮጵያ ፓርቲ ኢሕአዴግ በሀገሪቱ የተፈጠረውን ቀውስ ለማርገብ ከታኅሣሥ አጋማሽ አንስቶ ለ18 ቀናት የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴውን ውይይት ካካሄደ በኋላ የፖለቲካ እሥረኞችን ለመልቀቅ መወሰኑን ማስታወቁ ይታወሳል።

ይህንን ውሳኔ ታኅሣሥ 25 ካሳለፈና በወቅቱ የግንባሩን ሊቀመንበርና የሃገሪቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝን ጨምሮ የግንባሩ አባል የሆኑት የአራቱ ድርጅቶች የአመራር አባላት በጋራ በሰጡት መግለጫ ካስታወቁ በኋላ እስረኞች እየተፈቱ ይገኛሉ።

እስካሁን ስንት ሰው እንደተፈታ የመጨረሻው ቁጥር በእጃችን ባይኖርም ጉዳዩን የሚከታተሉ ግን ወደ 6 ሺህ እስረኞች መለቀቃቸውን ይናገራሉ።

ነገር ግን በየወኅኒው አሁንም ብዙ ሰው እሥር ላይ እንደሚገኝ ቀደም ሲል የተፈቱና በቅርብ እናውቃለን የሚሉም እየተናገሩ ነው።

በተጨማሪም ከአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ በኋላ ወደ አንድ ሺህ የሚጠጉ ሰዎች መታሰራቸውን ኮማንድ ፖስቱ አረጋግጧል።

ከእስረኞቹ መካከልና ጉዳዮቻቸውን ከሚከታተሉ ሰዎች ለአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከእስር የመፈታት ጥያቄ እየቀረበ ነው።

ተከታዩ የጽዮን ግርማ ዘገባ በኢትዮጵያ የተለያዩ ቦታዎች የታሰሩ እስረኞች ሁኔታ ምን እንደሚመስል ይዳስሳል

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG