በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

የኢትዮጵያ ካርታ

በባሕርዳር ከተማ ውስጥ በአንድ ላይ የነበሩ የዩኒቨርስቲ ምሑራን፣ የመንግሥትና የግል ጋዜጠኞችና ሌሎች ባለሞያዎች በአጠቃላይ 19 ሰዎች ቅዳሜ መጋቢት 15/2010 ዓ/ም መታሰራቸውን ያነጋገርናቸው ሰዎች ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ።

ግለሰቦቹ የአማራ ሕዝብ እየተፈፀመበት ላለለው የመብት ጥሰትና በኢኮኖሚ ተጠቃሚነት መረሳት ተወካይ አካል ያስፈልገዋል በሚል ሕጋዊ የፖለቲካ ፓርቲ ለማቋቋም ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የጠየቃቸውን መስፈርት ለማሟሟላት በመንቀሳቀስ ላይ እንደነበሩም ተናግረዋል። በዕለቱም ስለሚያስፈልጋቸው ነገር ተወያይተው ከጨረሱ በኋላ እራት እየበሉ መታሰራቸን ነው የገለፁት። የአማራ ክልል ቃል አቀባይ ስልካቸው ስለማይነሳ ልናገኛቸው አልቻልንም።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

በባሕርዳር ከተማ የታሰሩ ሰዎች የአማራን ጉዳይ ስላነሱ ነው ሲሉ ያነጋገርናቸው ሰዎች ገለጹ
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:08 0:00

ከእስር የተለቀቁ ሰዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ተመልሰው መታሰር በአጠቃላይ ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት የሥርዓት ለውጥ መሆኑን ማሳያ ነው ሲል ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ።

“ሰዎች መኖሪያ ድረስ በመሄድ ማኅበራዊ መቀራረቦችን በማፈን ማሰር አፋኝ ከሆነው የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅም መንፈስ በላይ ነው” ያለው ደግሞ መቀመጫውን ጄኔቫ፣ ስዊዘርላንድ ያደረገው 'ስብስብ ለሰብኣዊ መብቶች በኢትዮጵያ' ተብሎ የሚጠራ የሰብአዊ መብት ድርጅት ነው።

የኢትዮጵያ መንግሥትም ሆነ ፖሊስ ስለታሰሩት ሰዎች የሚለውን ምላሽ ማግኘት በስልክ ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

"እስሩ ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት የሥርዓት ለውጥ መሆኑን ማሳያ ነው "- አምነስቲ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:46 0:00

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG