በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

ሰኞ 5 የካቲት 2018

Calendar
ጥር የካቲት መጋቢት ሚያዚያ ግንቦት ሰኔ ሐምሌ ነሐሴ መስከረም ጥቅምት ህዳር ታህሳስ

የአድዋ ፓን አፍሪካን ዩኒቨርሲቲ ግንባታ

የአድዋ ፓን አፍሪካን ዩኒቨርሲቲ ግንባታ ለመነጋገር አዲስ አበባ በሚገኘው ሸራተን ሆቴል ጥር ሰባት ቀን ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የተገኙበት ጉባዔ ተካሂዷል።

የአድዋ ፓን አፍሪካን ዩኒቨርሲቲ ግንባታ ለመነጋገር አዲስ አበባ በሚገኘው ሸራተን ሆቴል ጥር ሰባት ቀን ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የተገኙበት ጉባዔ ተካሂዷል።

በጉባዔው የአድዋ ፓን አፍሪካን ዩኒቨርሲቲ የህንፃ ሥራ እንደሚጀመርና የኢትዮጵያ መንግሥት 2መቶ ሚልዮን ብር ለግንባታው እንዳበረከተ ተገልጿል።

የፓን አፍሪካን ዩኒቨርሲቲ ምሥራታ አስተባባሪ ኮሜቴ ዋና አባል የሆኑት ዶ/ር አየለ በከሬን ስለጉባዔው እንዲያብራሩልን ጋብዘናል። ዶ/ር አየለ በመቀለ ዩኒቨርሲቲ በቅርስ ጥናት ትምህርት ክፍል ተባባሪ ፕሮፌሰር ናቸው።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የአድዋ ፓን አፍሪካን ዩኒቨርሲቲ ግንባታ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:43 0:00


ፎቶ ፋይል

እሥራኤል በሺሕዎች የሚቆጠሩ አፍሪካውያን ስደተኞችን ከሀገሯ የማስወጣት እርምጃዎችን እየወሰደች መሆኗ ተሰማ።

እሥራኤል በሺሕዎች የሚቆጠሩ አፍሪካውያን ስደተኞችን ከሀገሯ የማስወጣት እርምጃዎችን እየወሰደች መሆኗ ተሰማ።

እሥራኤል፣ ሀገሯ ውስጥ ለሚገኙ ጥገኝነት ፈላጊዎች፣ ከሀገር መውጫ ትዕዛዝ መስጠት በመጀመሯ፤ ወደ 40ሺሕ አፍሪካውያን ፍልሰተኞች የወደፊት ተስፋ የደበዘዘ መሆኑ እየተሰዋለ ነው።

ፍልሰተኞቹ $3,500 እና ወደ ሩዋንዳ የመመለሻ የአውሮፕላን ትኬት እየተሰጣቸው በ60 ቀናት ውስጥ መውጣት እንዳለባቸው፣ አለበለዚያ ግን ለእስር እንደሚዳረጉ ነው የተገለፀው።

አብዛኛዎቹ ፍልሰተኞች፣ በጦርነት ከደቀቁት ከኤርትራና ከሱዳን ሲሆኑ፣ ባለፉት አሥር ዓመታት በሕገ ወጥ መንገድ እሥራኤል የገቡ ናቸው ነው የተባለው። ወደ አፍሪካ መመለስ ጥሩ አማራጭ አለመሆኑን የሚናገሩት ብዙዎቹ ታዲያ፣ አነስተኛ ጉዳት ወይም አደጋ ያለበትን አማራጭ መውሰድ ይገደዳሉ።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

እሥራኤል የሚገኙ አፍሪካውያን ስደተኞች
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:10 0:00

ከሰባተኛው የህውሃት ከፍተኛ አመራር ጉባዔ ቀጥሎ በየዞኖች ሲካሄድ የሰነበተው የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች የግምገማ ውጤት ይፋ ሆኖል፡፡

ከሰባተኛው የህውሃት ከፍተኛ አመራር ጉባዔ ቀጥሎ በየዞኖች ሲካሄድ የሰነበተው የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች የግምገማ ውጤት ይፋ ሆኖል፡፡

ግምገማዎቹ በሥድስት ዞኖችና በመቀሌ ከተማ የተካሄዱ መሆኑን ጠቅሶ ዓለም ፍስሃ ዜናውን አድርሶናል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የህውሃት ማዕከላዊ ጉባዔ ያደረጋቸው ውሳኔዎች
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:33 0:00

አቴንስ ውስጥ የተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ

ግሪክና ሜቄዶኒያ ለረጅም ጊዜ ሲያነታርካቸው በኖረው የሜቆዴንያ ስም ጉዳይ መግባባት ላይ ሊደርሱ መቃረባቸውን በመቃወም በብዙ አሥር ሺሕዎች የተቆጠሩ ተቃዋሚዎች አቴንስ ላይ ሰልፍ ወጥተዋል።

ግሪክና ሜቄዶኒያ ለረጅም ጊዜ ሲያነታርካቸው በኖረው የሜቆዴንያ ስም ጉዳይ መግባባት ላይ ሊደርሱ መቃረባቸውን በመቃወም በብዙ አሥር ሺሕዎች የተቆጠሩ ተቃዋሚዎች አቴንስ ላይ ሰልፍ ወጥተዋል።

የግሪክ መንግሥት የአጎራባች ሜቄዶኒያ ስም በመተመለከተ ከሃገሪቱ መንግሥት ጋር እንዳይስማማ ለመጠየቅ የወጣው ሰው ብዛት ፖሊሶች እንደሚሉት አንድ መቶ አርባ ሺህ ይደርሳል። የሰልፉ አደራጆች ግን አንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን ሰው ወጥቷል ብለዋል።

ሜቄዶኒያ እኤአ 1991 ከዩጎዝላቪያ ተገንጥላ ነፃ ከወጣችበት ጊዜ አንስቶ የስሟ ጉዳይ ከግሪክ ጋር ስያናቁራት ቆይቷል። ብዙዎች ግሪኮች በጥንታዊው የታላቁ እስክንድር ንጉሳዊ ግዛት ዋና ጠቅላይ ግዛት የነበረችውን የሜቄዶኒያን ስም ለጎረቤት ሃገር መስጠት የግሪክን ታሪክ ማዋረድ ነው ይላሉ፡፡

ሜቆዴኒያ ይህንኑ ስሟን ይዛ የአውሮፓ ህብረት አባል ለመሆን የምታደርገውን ግሪክ ስታከላክል ቆይታለች። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሜቄዶኒያን የቀድሞዋ የዩጎዝላቪያ ሪፐብሊክ ሜቄዶኒያ በሚል ስም ዕውቅና ሰጥቷል።

በሁለቱም ሃገሮች የተቃውሞ ሰልፍ የቀሰቀሰው ግራ ዘመሙ የግሪክ ጠቅላይ ሚኒስትር አሌክሲስ ሲፕራስ ለሃያ ሰባት ዓመታት የዘለቀውን ጭቅጭቅ በድርድር ለመፍታት ዝግጁ መሆናቸው ነው፡፡

በግሪክና ሜቄዶኒያ ጉዳይ ተቃዋሚዎች ሰልፍ ወጡ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:27 0:00

በእሥር የሚገኙት አራቱ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግሬስ አመራር አባላት እነ ጉርሜሳ አያኖ ችሎት በመዳፈር ወንጀል ዛሬም ተጫማሪ የእሥር ቅጣት ተጣለባቸው፡፡

በእሥር የሚገኙት አራቱ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግሬስ አመራር አባላት እነ ጉርሜሳ አያኖ ችሎት በመዳፈር ወንጀል ዛሬም ተጫማሪ የእሥር ቅጣት ተጣለባቸው፡፡

ችሎቱ የፍርድ ውሳኔውን ለማሰማት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አራተኛ ወንጀል ችሎት በአራቱ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግሬስ አመራር አባላት ላይ ችሎት ተዳፍራችኋል በማለት ዛሬ የሥድስት ወር ቅጣት ጣለባቸው፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የኦፌኮ አመራር አባላት ችሎት በመዳፈር የእሥር ቅጣት ተጣለባቸው
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:29 0:00

ፎቶ ፋይል

ከዓለም እጅግ የታወቁ የዝሆን ጥርስና የአውራሪስ ቀንድ ሕግ ወጥ ንግድ መርማሪዎች አንዱ፣ ኬንያ ውስጥ ተገደሉ።

ከዓለም እጅግ የታወቁ የዝሆን ጥርስና የአውራሪስ ቀንድ ሕግ ወጥ ንግድ መርማሪዎች አንዱ፣ ኬንያ ውስጥ ተገደሉ። ኤዝመንድ ብራድሊ ማርቲን ናይሮቢ የመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ አንገታቸው ላይ በስለት ተወግተው ተገድለው ነው የተገኙት ።

የሰባ አምስት ዓመቱ አሜሪካዊ ሕገወጥ የዝሆን ጥርስ ንግድ እና ገበያዎቹ ላይ፣ በድብቅ ያደረጉት ክትትል ድርጊቱን ለማጋለጥ አስችሏል።

ዋይልድላይፍ ዳይሬክት የተባለው ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ ፓውላ ካሁምቡ የማርቲን ሥራ በቅርቡ ዩናይትድ ስቴትስ ኮንጎ ቪየትናም ናይጄሪያ አንጎላ እና ቻይና ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የዝሆን ጥርስ ነጋዴዎችን ለማጋለጥ እንደረዳ ገልፀዋል።

ቻይና እኤአ በ1993 ሕጋዊ የአውራሪስ ቀንድ ንግድ በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ ሕጋዊ የዝሆን ጥርስ ንግድ ለመከልከል ያበቃት የሳቸው ሥራ ውጤት እንደሆነ ተነሯል።

የዝሆን ጥርስና የአውራሪስ ቀንድ ሕግ ወጥ ንግድ መርማሪ ኬንያ ውስጥ ተገደሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:12 0:00

XS
SM
MD
LG