በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

ፎቶ ፋይል:- ፊደል ካስትሮ ዲያዝ ባላርት

የኩባው ኮምኒስት መሪ የፊደል ካስትሮ ልጅ ትናንት ሐሙስ ራሳቸውን ማጥፋታቸው ተነገረ።

የኩባው ኮምኒስት መሪ የፊደል ካስትሮ ልጅ ትናንት ሐሙስ ራሳቸውን ማጥፋታቸው ተነገረ። ሰበቡ፣ ለወራት ያህል በከፍተኛ ድብርትና የመንፈስ ጭንቀት ውስጥ መክረማቸው ነው ተብሏል። ዕድሜያቸውም 68 ነበር።

አባታቸውን ይመስሉ ስለነበር ፊደሊቶ «ትንሹ ፊደል» ይባሉ የነበሩት ፊደል ካስትሮ ዲያዝ ባላርት፣ በቀድሞዋ ሶቭዬት ሕብረት ኒዩክለር ፊዚክስ አጥንተው፣ ኩባ ውስጥ የመንግሥቱ ምክር ቤት አማካሪ ነበሩ።

ፊደል ካስትሮ ዲያዝ ባላርት፣ የኩባ ሳይንስ አካዳሚ ምክትል ፕሬዚደንት ሆነው ከማገልገላቸውም በላይ፣ እአአ ከከ1980-1992 ፣ የኩባን የኑክሊየር ፕሮግራም በበላይነት መርተዋል።

H.R. 128
በዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ረቂቅ ሕግ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:49 0:00

ኢትዮጵያ ውስጥ የዜጎች ሰብዓዊ መብት እንዲከበር ግፊት ለማድረግ ታልሞ ባለፈው ዓመት በየካቲት ወር መጀመሪያ ለዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት በቀረበው የሕግ ረቂቅ ቀጣይ ሂደት ዙሪያ የተካሄደ ጋዜጣዊ ጉባኤ ተንተርሶ የተጠናቀረ ዘገባ በትላንትናው ምሽት አሰምተናል።

ባሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የሚታየው ሁኔታ ካልተለወጠ HR-128 የሚል መጠሪያ የተሰጠው ይህ ረቂቅ ሕግ ወደ ሙሉ ምክር ቤቱ ተመርቶ ሊጸድቅ የሚችል መሆኑን ነበር በምክር ቤቱ የብዙኃኑ ፓርቲ ተጠሪ በተገኙበት በተካሄደው ጋዜጣዊ ጉባኤ የተገለጸው።

በዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት የኮሎራዶ ክፍለ ግዛት ተወካይ ከኮንግሬስማን ማይክል ሃዋርድ ኮፍማን ከአሜሪካ ድምጽ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልሳቸው በእንቅስቃሴው አብረዋቸው እንደሚሰሩ ከጠቀሷቸው ኢትዮጵያውያን አሜሪካውያን አንዱ ናቸው።

አምሳሉ ካሳው ይባላሉ። የኢትዮጵያውያን አሜሪካውያን ግብረ-ኃይል ቃል አቀባይ ናቸው። ስለ ጋዜጣዊ ጉባኤው፥ ስለ ረቂቅ ሕጉ እና በኢትዮጵያ ጉዳይ ከምክር ቤት አባላቱ ጋር ስለሚሩት ሥራ ይወያያሉ።

የኢትዮጵያ ካርታ

በወልዲያ፣ በመርሳ፣ በቆቦና በሌሎች የዞኑ ከተሞች የሚታሰሩ ሰዎች ቁጥር በየቀኑ እየጨመረ መሆኑን ነዋሪዎች ይናገራሉ።የክልሉ መንግሥት ሕይወት በማጥፋት፣ አካል በማጉደልና ንብረት በማውደም የተጠረጠሩት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ማዋል መጀመሩን አረጋግጧል።

የሰሜን ወሎ ዞን ሀገረ ስብከት መንግሥት ነገሮችን እንዲያስተካክል ማሳሰባቸውን ገለጹ
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:55 0:00

የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት የብፁዕ አቡነ ቄርሎስ ረዳት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ኤርሚያስ የክልሉ መንግሥት ጉዳዩን በጥንቃቄ ተከታትሎ ዘላቂ መፍትሔ እንዲሰጥ ሀገረ ስብከቱ ማሳሰቡን ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል።

XS
SM
MD
LG