በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

ዛሬ ጠዋት በአዳማ ከተማ ቀበሌ 13 አቅራቢያ በሚገኛና በተለምዶ “የጨረቃ ቤት” እየተባለ የሚጠራ መንደርን ለማፍረስ በተሰማራ ግብረ ኃይልና በነዋሪዎቹ መካከል በተፈጠረ ግጭት የሰው ሕይወት መጥፋቱንና ሰዎችንም በታጣቂዎች መደብደባቸውን ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ገለፁ። ሟቾቹን በተመለከተ ከክልሉ መንግሥት ያገኘነው መረጃ የለም።

ስማቸውን እንዳንጠቅስ የጠየቁን በአካባቢው ነበርኩ ያሉ የዐይን እማኝ ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት፤ ዛሬ ጠዋት ፖሊስና የመዘጋጃ ቤት ሠራተኞች ወደ ስፍራው ሄደው ነዋሪዎቹ እንዲወጡ ማደረጋቸውን ነው። “ነዋሪዎቹ ቤት የሚያፈርስ ግሬደር መኪና ሲመለከቱ በአንድ ጊዜ ቤት ሊፈርስባቸው እንደማይገባ ተራበሸ። ከዛ ቀስ በቀስ ተጋግሎ ወደ ተኩስ ተሸጋገረ።” ብሎናል።

ነገሩ እየተጋጋለ ሲሄድ የታጠቀ ኃይል እየተበራከተ መምጣቱን የሚናገረው ነዋሪው፤ “በረብሻው መካከል ሚሊቴሪ ኃይሎቹ ብዙ ሰዎችን ደበደቡ። በቁጥር መለየት ባልችልም ብዙ ሰው ቆስሏል። ሁለት ሰውም ተመቶ ሞቷል። አንዱ የቤት ባለቤት አንዱ ደግሞ እዛው ነዋሪ የነበረ ሰው ነው። ከዛ እዛ የነበሩ በተለይ አዛውንትና ሴቶች ሸሹ ወጣቶቹ ግን እየጮሁ ከተማውን መዞር ጀመሩ” ሲል በዛሬው ዕለት የነበረውን ሁኔታ አስረድቷል።

በመጨረሻ ቤቶቹ ባይፈርሱም ታጣቂዎቹ አካባቢውን በብዛት በመቆጣጠራቸው ሁኔታው መብረዱን ነዋሪው ገልፆ ቀስ እያሉ ግን እንነሱም እየተቀነሱ መሄዳቸውን ጠቁሟል። ሁኔታውን ለማጣራት የክልሉ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋን ለማግኘት ጥረት አድርገን አልተሳካም።

በነገው ምሽት የሬዲዮ ፕሮግራማችን በጉዳዩ ላይ ሰፋ ያለ ዘገባ ይዘን እንመለሳለን።

ፕሮፌሰር መሐመድ አባጀበል

ኢሚግራንቶች ለአሜሪካ ሸክም ሳይሆኑ ሃብት ናቸው ሲሉ የቴክሳሷ ዳላስ ውስጥ የምጣኔ ኃብት ምሁርና ፕሮፌሰር የሆኑት ዶ/ር መሐመድ ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል።

ኢሚግራንቶች ለአሜሪካ ሸክም ሳይሆኑ ሃብት ናቸው ሲሉ የቴክሳሷ ዳላስ ውስጥ የምጣኔ ኃብት ምሁርና ፕሮፌሰር የሆኑት ዶ/ር መሐመድ አባጀበል ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል።

“በአንፃራዊ ሁኔታ የፕሬዚዳንት ትረምፕ የትናንት አቀራረብ ጥሩ ነበር” ብለዋል ትውልደ ኢትዮጵያ አሜሪካዊ ምሁርና ፖለቲከኛው ዶ/ር መሐመድ።

ዲቪ ሎተሪ በፕሬዚዳንት ትረምፕ ጥያቄ መሠረት ይቀር ይሆን እንደሆነ ፕሮፌሰር መሐመድ ሲጠየቁ ከዘጠኝ ወራት በኋላ በሚካሄደው የአማካይ ጊዜ የተወካዮች ምክር ቤት ምርጫ ዴሞክራቶቹ አንዱን ወይም ሁለቱንም የምክር ቤቱን ክንፎች ከተቆጣጠሩ ይሠረዛል ብለው እንደማያስቡ አመልክተው አሁን ባለው ሁኔታ ውስጥ በአሜሪካ ፖለቲካ ውስጥ ማንኛውም ነገር የሚሸጥ ነውና የተሻለ የሚሉት መደራደሪያ ከቀረበላቸው ምናልባት ዴሞክራቶቹ እጅ ሊሰጡ ይሆናል የሚል ሃሣብ እንዳላቸው ገልፀዋል።

የአሜሪካ የአክስዮን ገበያዎች ታይተው የማይታወቁ ጣሪያዎችን መንካት የነጋዴው ትረምፕ ወደ መንበረ ፕሬዚዳንቱ የመዝለቃቸው የገበያው ሥነ‑ልቦና ውጤት ሊሆን ይችላል ብለው እንደሚገምቱም ዶ/ር መሐመድ ተናግረዋል።

ከዶ/ር መሐመድ አባጀበል ጣሂሮ ጋር የተደረገውንም ሙሉ ቃለ‑ምልልስ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ኢትዮ­­‑አሜሪካዊው ምሁር በትረምፕ ንግግር ላይ
please wait

No media source currently available

0:00 0:24:09 0:00

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ከትናንት በስተያ ለተወካዮች ምክር ቤቱ ጥምር ጉባዔ ያደረጉት ንግግር በተከታተሉት አሜሪካዊያን በአመዛኙ አዎንታዊ አቀባበል ማግኘቱ እየተሰማ ነው። ፕሬዚዳንቱ በንግግራቸው ላይ መተባበርና የሁለቱንም ገዥ ፓርቲዎች የጋራ ውሣኔዎች መጠየቃቸው ብዙ ሪፐብሊካንን አስደስቷል።ዴሞክራቶቹ ግን በትረምፕ እውነተኛ አቋም ላይ ጥርጣሬአቸው እንደበረታ ነው።

እጅግ ጎርበጥባጣ ከነበረውና ብዙ ድምፅ ከበዛበት የትራምፕ አስተዳደር የመጀመሪያ ዓመት በኋላ ፕሬዚዳንቱ ለእንደራሴዎች፣ ለሕዝባቸውም፣ ለዓለምም ያደረጉት ንግግር የሃገራቸውን የፖለቲካ ሰዎችና ዜጎቻቸውንም ለአንድነት የሚጣራ መልዕክት የጎላበት ነበር፡፡

ይህንን የተለሳለሰ የሚመስለውን የፕሬዚዳንቱን የንግግር ቃናና ከተቃዋሚው ፓርቲ ጋር አብሮ የመሥራት ጥሪ ሪፖብሊካኑ ወድደውታል፡፡

ዴሞክራቶቹ ግን ፕሬዚዳንቱ በተናገሩበት ጊዜ ሁሉ በአብዛኛው አላጨበጨቡላቸውም፡፡ በፕሬዚዳንት ትረምፕ ልባዊነት ላይ ጥርጣሬ እንዳላቸው ነው በዚያ የጠቆሙት - ያመለካቱት።

ፕሬዚዳንቱ ከተናገሩ በኋላ የተወሰዱ የሕዝብ አመለካከት ናሙናዎች ለጊዜው የሚያሳዩት ግን ሰዉ ያንን መላዘባቸውን እንደወደደላቸው ነው፡፡ ቢያንስ ለጊዜው ያሰቡት የተሳካ ይመስላል፡፡

ጥያቄው ግን ይዘልቅ ይሆን? የሚል ነው፡፡

የተያያዙትን የድምፅና የቪድዮ ፋይሎች ይክፈቱ።

ዶናልድ ትረምፕ በኮንግረስ ቃናቸው ይዘልቁ ይሆን?
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:11 0:00
ዶናልድ ትረምፕ በኮንግረስ ቃናቸው ይዘልቁ ይሆን?
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:35 0:00

ፎቶ ፋይል፡- በዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ውስጥ፣ በሦስተኛ ደረጃ ከፍተኛው ዲፕሎማት ቶማስ ሻነን

በዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ውስጥ፣ በሦስተኛ ደረጃ ከፍተኛው ዲፕሎማት፣ ከ35ዓመት አገልግሎት በኋላ ሥልጣን መልቀቃቸውን ዛሬ ሐሙስ አስታወቁ።

በዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ውስጥ፣ በሦስተኛ ደረጃ ከፍተኛው ዲፕሎማት፣ ከ35ዓመት አገልግሎት በኋላ ሥልጣን መልቀቃቸውን ዛሬ ሐሙስ አስታወቁ።

"ቤተሰቤንና የራሴን ሕይወት በቅርብ ለመንከባከብና አዲስ የሕይወት አቅጣጫ ለመጀመር ስል ነው፣ በራሴ ፍላጎትና ፈቃድ ሥልጣን የለቀቅሁት" ያሉት ቶማስ ሻነን ናቸው።

ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን ስለ ባለሥልጣኑ ተጠይቀው ሲናገሩ፣ “በሥራ እንዲቆዩ ፈልገን ነበር፣ ግን አልሆነም። ይሁን እንጂ የርሳቸው ሥራ መልቀቅ ቀላል ጉዳት አይደለም” ብለዋል።

የዲሞክራሲ ታጋይ ኡን ሳን ሱቺ

ያንኡን ውስጥ በሚገኘው በሚያንማር የቀድሞዋ በርማ የዲሞክራሲ ታጋይ ኡን ሳን ሱቺ መኖሪያ ቤት ላይ ዛሬ ሐሙስ ቦምብ መወርወሩን፣ ቃል አቀባያቸው አስታወቀ፡፡

ያንኡን ውስጥ በሚገኘው በሚያንማር የቀድሞዋ በርማ የዲሞክራሲ ታጋይ ኡን ሳን ሱቺ መኖሪያ ቤት ላይ ዛሬ ሐሙስ ቦምብ መወርወሩን፣ ቃል አቀባያቸው አስታወቀ፡፡

ቃል አቀባዩ ዛወ ሃታይ እንዳስታወቁት፣ ቦምቡ በተወረወረበት ወቅት፣ የኖቤል ሰላም ሎሬቷ ኡን ሳን ሱቺ ቤታቸው አልነበሩም፤ በመኖሪያ ቤቱ ላይም የደረሰ ጉዳት የለም።

ላለፉት ሃያ ዓመታት በቀድሞው የሚያንማር ወታደራዊው ዡንታ የቁም እሥር ላይ የሚገኙት ሳን ሱቺ፤ አብዛኛውን ጊዜ የሚጠፉት፣ አሁን አደጋ በተቃጣበትና ያንኡን ውስጥ በሚገኘው ሐይቅ አካባቢ ባለው መኖሪያቸው ውስጥ እንደሆነ ይታወቃል።

ሳን ሱቺ፣ የበርማ የአሁኗ ሚያንማር የዲሞክረሲ ተምሳሌት ተደርገው ነው፣ በመላው ዓለም የሚታወቁት፡፡

ሦስት የኬንያ ታዋቂ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች፣ የተቃዋሚውን የራይላ ኦዲንጋን የይስሙላ ቃለ-መኃላ በማስተለፋቸው፣ መንግሥት አየር ላይ እንዳይውሉ ያስተላለፈውን ዕገዳ እንዲያነሳ፣ የኬንያ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ዛሬ ሐሙስ ትዕዛዝ አስተላለፈ።

ሦስት የኬንያ ታዋቂ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች፣ የተቃዋሚውን የራይላ ኦዲንጋን የይስሙላ ቃለ-መኃላ በማስተለፋቸው፣ መንግሥት አየር ላይ እንዳይውሉ ያስተላለፈውን ዕገዳ እንዲያነሳ፣ የኬንያ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ዛሬ ሐሙስ ትዕዛዝ አስተላለፈ።

በዚህ፣ የፕሬዚደንት ኡሑሩ ኬንያታን መመረጥ ለመቃወም በተካሄደው የቀልድ ሥነ ሥርዓት ላይ ግን፣ በአሥር ሺሕዎች የሚቆጠሩ የራይላ ኦዲንጋ ደጋፊዎች መገኘታቸው ታውቋል። ኦዲንጋ ይህን የፕሬዚዳንት ኡሑሩን ምርጫ፣ “የተጭበረበረ ነው” ነው የሚሉት።

መንግሥት፣ ለማክሰኞው የይስሙላ ቃለ መኃላ ሥነ ሥርዓት በሰጠው መልስ፣ የተቃዋሚው እንቅስቃሴ ሕገወጥና ድርጅቱም ወንጀለኛ መሆኑን አመልክቶ፣ ሥነሥርዓቱን የዘገቡ ጣቢያዎችም እንዳያስተላልፉ አዟል።

ሆኖም ከፍተኛው የኬንያ ፍርድ ቤት ዳኛ ቻቻ መዊታ በዛሬው ችሎት፣ መንግሥት ጣቢያዎቹ ላይ ያስተላለፈውን ዕገዳ እንዲያነሳ አዘው፣ እንዲዘጉ የተላለፈባቸው ጉዳይ በፍ/ቤት እስኪታይ ድረስም፣ መንግሥቱ በመገናኛ ብዙኃን ሥራ ላይ ጣልቃ እንዳይገባ ወስኗል።

የዩናይትድ ስቴትሱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን

የዩናይትድ ስቴትሱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን፣ የሥድስት ቀን የላቲን አሜሪካ ሀገሮች ጉብኝታቸውን ዛሬ ሐሙስ ጀመሩ። ሚስተር ቲለርሰን በዚህ ጉብኝታቸው፣ በቀውስ በተመታችው ቬኔዙዌላ ዴሞክራሲያዊ ለውጦች እንዲካሄዱ የክልሉ መንግሥታት ጫና እንያደርጉ ያሳስባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የዩናይትድ ስቴትሱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን፣ የሥድስት ቀን የላቲን አሜሪካ ሀገሮች ጉብኝታቸውን ዛሬ ሐሙስ ጀመሩ። ሚስተር ቲለርሰን በዚህ ጉብኝታቸው፣ በቀውስ በተመታችው ቬኔዙዌላ ዴሞክራሲያዊ ለውጦች እንዲካሄዱ የክልሉ መንግሥታት ጫና እንያደርጉ ያሳስባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የሥድስቱ ቀናት የቲለርሰን ጉዞ ወደ ሜክሲኮ፣ አርጀንቲና፣ ፔሩ፣ ኮሎራዶ እና በመጨረሻ ጃማይካ እንደሚወስዳቸው ታውቋል።

አንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ ባለሥልጣን እንደተናገሩት፣ ዩናይትድ ስቴትስ የቬኔዙዌላን ሁኔታ ለማርገብ ዲፕሎማሲያዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ መንገዶችን ሁሉ ትጠቃማለች።

ቬኔዙዌላ በከፍተኛ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ቀውስ ውስጥ ከገባች እነሆ አምስተኛ ዓመቷን ይዛለች።

ባለፈው የአውሮፓውያኑ ጥር ወር፣ የዩናይትድ ስቴትስ የገንዘብ ሚኒስቴር፣ ቀደም ብሎ በማዕቀብ መዝገቡ ውስጥ በነበሩት ላይ፣ “በከፍተኛ ሙስና የተዘፈቁ ናቸው” ባሏቸው ሌሎች አራት ወታደራዊ ባለሥልጣናት ላይ፣ ማዕቀብ መጣሉ ይታወቃል።

ፕሬዚዳንት ዮሴፍ ካቢላ

ፕሬዚዳንት ዮሴፍ ካቢላ ሕገ መንግሥቱን እንደሚያከብሩና፣ ከመጪው ታኅሣሥ ወር ምርጫ በኋላም ሥልጣን ለማስረከብ መወሰናቸውን፣ አንድ የዴሞክራቲክ ኮንጎ ሪፖብሊክ መንግሥት ቃል አቀባይ አስታወቁ።

ፕሬዚዳንት ዮሴፍ ካቢላ ሕገ መንግሥቱን እንደሚያከብሩና፣ ከመጪው ታኅሣሥ ወር ምርጫ በኋላም ሥልጣን ለማስረከብ መወሰናቸውን፣ አንድ የዴሞክራቲክ ኮንጎ ሪፖብሊክ መንግሥት ቃል አቀባይ አስታወቁ።

ላምበርት ሜንዲ ወደ አፍሪካ ለሚተላለፈው የቪኦኤ ፈረንሳይኛ አገልግሎት በሰጡት ቃል፣ በአሁኑ ወቅት የድምፅ አሰጣጡ ምዝገባ ተጠናቆ ምርጫው በታቀደለት መርኃ ግብር መሠረት እንደሚካሄድ አስታውቀዋል።

ቃል አቀባዩ አክለውም፣ ፕሬዚዳንት ካቢላ ድጋሚ ለመመረጥ እንደማያስቡ አመልክተው፣ በታኅሣሱ ምርጫ የሚወዳደረውን ዕጩ ማንነትም በመጪው ሐምሌ ይፋ እንደሚያደርጉም ገልፀዋል።

በአገሪቱ ሕገ መንግሥት መሠረት፣ ፕሬዚዳንቱ ለሦስተኛ ጊዜ መወዳደር አይችልም።

ፎቶ ፋይል

እአአ በ2014 ሶቼ ባዘጋጀችው የክረምት ኦሎምፒክ ውድድር ወቅት አበረታች መድሃኒት በመውሰድ የተከሰሱ 28 የሩሲያ አትሌቶች፣ ያስመዘገቧቸው ውጤቶች እንዲሠረዙና ዕድሜ ልክ ከኦሎምፒክ ውድድሮች እንዲተገዱ መደረጋቸው ይታወሳል።

እአአ በ2014 ሶቼ ባዘጋጀችው የክረምት ኦሎምፒክ ውድድር ወቅት አበረታች መድሃኒት በመውሰድ የተከሰሱ 28 የሩሲያ አትሌቶች፣ ያስመዘገቧቸው ውጤቶች እንዲሠረዙና ዕድሜ ልክ ከኦሎምፒክ ውድድሮች እንዲተገዱ መደረጋቸው ይታወሳል። ጉዳዩን ሲያይ የቆየው ዓለምቀፉ የስፖርት ይግባኝ ፍ/ቤት ዛሬ ብይኑን ሠርዞ የአትሌቶቹን አቤቱታ አፅድቋል።

በሌላ በኩል ደግሞ ደቡብ ኮሪያ በምታዘጋጀው ኦሊምፒክ የምትሳተፈው የኮሚኒስት ሰሜን ኮሪያ ሰንደቅ ዓላማ ዛሬ በአትሌቶቿ መንደር ውስጥ መውለብለብ ጀምሯል።

ክሪስ ሃናስ እና ሪቻርድ ግሪን ከቪኦኤ ዜና ማደራጃ ያጠናቀሯቸው አጫጭር ዘገባዎች አሉ።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

በክረምት ኦሎምፒክ አበረታች በመውሰድ የተከሰሱ 28 የሩሲያ አትሌቶች
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:40 0:00

XS
SM
MD
LG