በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

በድሬደዋ ከተማ አንዳንድ አካባቢዎች ከባንቧው ውስጥ እንዲህ ያለ ውሃ እንደሚወጣ ነዋሪዎች ይናገራሉ።

በድሬደዋ ከተማ ከሰባት ዓመት በፊት የተጀመረ የውኃ ፕሮጀክት ሳይጠናቀቅ በመዘግየቱ የሚጠጣ ውኃ አገልግሎት ችግር መኖሩን ነዋሪዎች እየገለፁ ነው። የከተማዪቱ የውኃና ፍሳሽ ባለስልጣን ፕሮጀክቱ በመጭዎቹ ሦስት ሣምንት ውስጥ እንደሚጠናቀቅም አመልክቷል።

ተይዞ የነበረው በጀት ከ650 ሚሊዮን ብር በላይ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ለፕሮጀክቱ ይሠራል የተባለ የኤሌክትሪክ አገልግሎትም በመዘግየቱ ለጀኔሬተር በወር በሚሊዮን የሚቀጠር ገንዘብ እየወጣ እንደሆነ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለቪኦኤ ገልፀዋል።

የከተማዪቱ የውኃና ፍሳሽ ባለስልጣን የፕሮጀክቱ ሥራ ለሁለት ዓመታት መዘግየቱን አምኖ “ከአቅም በላይ በሆነ ችግር ምክንያት ነው” ነው ብሏል። በመጭዎቹ ሦስት ሣምንት ውስጥ እንደሚጠናቀቅም አመልክቷል።

ከፕሮጀክቱ በጀት ላይ የ46 ሚሊዮን ብር ሥራ ለማከናወን የአገልግሎት ክፍያ የተፈፀመለት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የድሬዳዋ ዲስትሪክት በበኩሉ “በተያዘው የጊዜ ሠሌዳ መሠረት እየሠራሁ ነው፤ በሦስት ቀን ጊዜ ውስጥ አጠናቅቃለሁ” ብሏል። (ዝርዝርሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)

ሰባት ዓመት ያስቆጠረው የድሬደዋ ውሃ ፕሮጀክት
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:54 0:00

የሮማው ሊቀ-ጳጳስ አቡነ ፍራንሲዝ

በአንዳንድ ካቶሊካዊያን ቀሳውስት ዘንድ ይታያል ያሉት የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪነትና ግብረሥጋ ጠባይ በብርቱ እንደሚያሳስባቸው የሮማው ሊቀ-ጳጳስ አቡነ ፍራንሲዝ አስታውቀዋል።

በአንዳንድ ካቶሊካዊያን ቀሳውስት ዘንድ ይታያል ያሉት የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪነትና ግብረሥጋ ጠባይ በብርቱ እንደሚያሳስባቸው የሮማው ሊቀ-ጳጳስ አቡነ ፍራንሲዝ አስታውቀዋል።

ቤተክርስትያኒቱ አገልጋዮቿን ለቅስና ስታጭ ጥብቅ መሆን እንደሚኖርባትና የብቸኝነት ሕይወት ለመምራት የገቡትንም ቃል መጠበቅ እንደሚኖርባቸው አሳስበዋል።

አቡነ ፍራንሲዝ በተመሳሳይ ፆታዊ ግንኙነት ላይ ያላቸውን አቋም እጅግ ግልፅ ያደረጉበትን ሃሣባቸውን ይፋ ያደረገ መፅሐፍ ነው ሰሞኑን የወጣው።

የቤተክርስትያናቸው ቀሳውስት ምግባር ጉዳይ በእጅጉ እያሳሰባቸው መሆኑን ፓፓው የገለፁት በተለይ የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት በየማኅበረሰቡ ውስጥ “እንደቄንጥ እየተስፋፋ በመጣበት” ሲሉ እራሣቸው በገለፁት ጊዜ ነው።

“የሙያ ጥንካሬ፤ የዛሬ የቅድስና ሕይወት” በሚል ርዕስ በተሰናዳ መፅሐፍ የታተመው ከስፓኛዊው ሚሲዮናዊ ቄስ፤ አባት ፌርናንዶ ፕራዶ ጋር ባለፈው ነኀሴ የተደረገው የተራዘመ ቃለ-ምልልስ አቡነ ፍራንሲዝ በመሣሣይ ፆታ ግንኙነት ጉዳይ ላይ “የተመሣሣይ ፆታ ግንኙነት እጅግ አሳሳቢ ጉዳይ ነው፤ በዕጩ ቀሳውስት ዘንድ ገና ከጅምሩ አንስቶ ተነጥሎ ሊወገዝ የሚገባው ነው” ማለታቸውን ያስነብባል።

በርግጥ የሮማ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን የአንድ ዓይነት ፆታ ሰዎች የመፋቀር አዝማሚያ ‘ኃጢአት ነው’ አትልም፤ “ወደ ግብረሥጋ ከዘለቁ ግን ውጉዝ አድራጎት፤ ኃጢአት ነው” - በቤተክርስትያኒቱ ትምህርት።

በተመሣሣይ ፆታ ሥጋዌ ግንኙነት ውስጥ ያሉ ሰዎች ለቤተክርስትያን አገልግሎት “ሊጠሩም፤ ሊታጩም አይገባም” የሚል ብርቱ እምነት አቡነ ፍራንሲዝ እንዳላቸው ነው “የሙያ ጥንካሬ...” መፅሐፍ የሚተርከው።

ለሮማ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን የአገልጋዮቿ “የብቸኛነት ሕይወት” ሊከበር የሚገባው ሕግ ነው። “ለቅዱሣን የግዜር ሰዎች መንታ ሕይወት ይመሩ ዘንድ አይቻላቸውም” ብለዋል አቡኑ ፍራንሲዝ።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የተመሳሳይ ፆታ ፍቅርና የፓፓው አቋም
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:20 0:00

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG