በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

የቁልቢ ገብርዔል ዓመታዊ ንግሥ በሰላም ተጠናቋል፡፡ ክብረ በዓሉ ከሃይማኖታዊነቱ በመለስ ማኅበራዊ ፋይዳውም የጎላ መሆኑን በሚያሳይ ሁኔታ የአካባቢው መስሊም በጎ ፍቃደኞች እንቅስቃሴ ከዚህ በፊት ከነበረው ሁሉ የበለጠ እንደነበር ተገልጿል፡፡

የቁልቢ ገብርዔል ዓመታዊ ንግሥ በሰላም ተጠናቋል፡፡ ክብረ በዓሉ ከሃይማኖታዊነቱ በመለስ ማኅበራዊ ፋይዳውም የጎላ መሆኑን በሚያሳይ ሁኔታ የአካባቢው መስሊም በጎ ፍቃደኞች እንቅስቃሴ ከዚህ በፊት ከነበረው ሁሉ የበለጠ እንደነበር ተገልጿል፡፡

ከኤርትራ ወደ ቁልቢ የተጓዙ ክርስቲያን አማንያንም ከሃያ ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ዛሬ ገብርዔልን ከኢትዮጵያውያን ጋር አንግሠዋል፡፡

ሪፖርተራችን አዲስ ቸኮል ከቁልቢ ተጨማሪ አለው፡፡

የቁልቢ ገብርዔል ዓመታዊ ንግሥ በሰላም ተጠናቀቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:12 0:00

ሲአን

ኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ ያለውን የለውጥ ሂደት “ለመቀልበስ የሚደረጉ” ያላቸውን እንቅስቃሴዎች እንደሚቃወም የሲዳማ አርነት ንቅናቄ - ሲአን አስታውቋል፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ ያለውን የለውጥ ሂደት “ለመቀልበስ የሚደረጉ” ያላቸውን እንቅስቃሴዎች እንደሚቃወም የሲዳማ አርነት ንቅናቄ - ሲአን አስታውቋል፡፡

ለውጡን “ከፍተኛ መስዋዕትነት የተከፈለበት” ብሎታል ሲአን። የተለያየ ስብጥር ባላቸው የሃዋሳ ከተማ ነዋሪዎች መካከል “አለመተማመን እንዲኖርና ሁከት እንዲፈጠር የሚያደርጉ ኃይሎችን አወግዛለሁ" ብሏል ሲአን ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ።

“በሃሳብ ልዕልናና በሰላማዊ መንገድ እንጂ ሁከት በመፍጠርና ሰላም በመንሳት የሚደረግ ትግል ተቀባይነት የለውም” ብሏል ንቅናቄው።

"የሲዳማ ህዝብ ጥያቄ ነው" ያለው የሲዳማ ክልልነት ጥያቄ ውሣኔ-ሕዝብ ሂደት የደረሰበትን ደረጃ መንግሥት ለህዝብ እንዲያሳውቅ ሲአን ጠይቋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ

የሲዳማ አርነት ንቅናቄ የ/ሲአን/ መግለጫ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:32 0:00

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG