በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

ቤንሻንጉል ጉምዝ

በቤንሻንጉል ጉምዝ ማኦኮሞ ወረዳ ውስጥ በአልሚዎች የእርሻ ቦታ በቀን ሥራ ላይ ተሰማርተው እንደነበር የሚናገሩ የትግራይ ተወላጆች ተለይተው በታጣቂዎች ጥቃት እንደረሰባቸው የተወሰኑት ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ።

ሰባቱ ታፍነው መወሰዳቸውን ሰባቱ ደግሞ ሸሽተው ጫካ ውስጥ መግባታቸውን ገልፀዋል። ንብረት የተዘረፈባቸው ባለሀብቶች እንዳሉም ጠቁመዋል። የክልሉ መንግሥት የፀጥታ ዘርፍ ኃላፊው መረጃው እንደደረሳቸውና እየተጣራ መሆኑን ገልፀው፤ በአካባቢው ጥቃት ያደርሳሉ ያሏቸው ታጣቂዎች ብሔር እየለዩ እንዳልሆነ ተናግረዋል።

በሌላ ከዚሁ ክልል ጋር በተያያዘ ዜና የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የ102 በእርሻ ሥራ ላይ ከተሰማሩ አልሚዎች ላይ ከ62 ሺሕ ሄክታር በላይ የእርሻ መሬት መነጠቁን፣ ወደ 37 ለሚጠጉ ፕሮጀክቶች ከቀረጥ ነፃ የገቡ የእርሻ መኪናዎች የጉምሩክን ሕግ እንዲያከብሩ መወሰኑን፣ በተጨማሪም የእጣን ምርትን በስፋት ይዘው ከነበሩ ባለሃብቶች 24 ፕሮጀክቶች መነጠቃቸውን የክልሉ የአከባቢ ደንና መሬት አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢሳቅ አብዱልቃድር ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል። አብዛኞቹ ባለሀብቶች የትግራይ ተወላጆች እንደሆኑም ኃላፊው ጨምረው ገልፀዋል።

(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)

በቤንሻንጉል ጉምዝ የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች ጥቃት እንደደረሰባቸው ተናገሩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:12:49 0:00

IFC CEO Philippe Le Houerou, Ahimed Shedie and Yinnager Desie at the Presser.

የግሉን ክፍለ-ኢኮኖሚ የመዋዕለ-ነዋይ አቅም ሊያግዝና ሊገነባ የሚያስችል የተባለ ስምምነት ዓለምቀፍ የገንዘብ ኮርፖሬሽን ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ጋር ተፈራርሟል።

የግሉን ክፍለ-ኢኮኖሚ የመዋዕለ-ነዋይ አቅም ሊያግዝና ሊገነባ የሚያስችል የተባለ ስምምነት ዓለምቀፍ የገንዘብ ኮርፖሬሽን ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ጋር ተፈራርሟል።

ኮርፖሬሽኑ የሃገሪቱ የልማት እንቅስቃሴ ስትራተጂያዊ አጋር ለመሆን መወሰኑን ኃላፊው ገልፀዋል።

ዛሬ የተፈረመው ስምምነት መንግሥት የግሉን ክፍለ-ኢኮኖሚ ለማሳደግ ያለውን ቁርጠኛነት ያሳያል ተብሏል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ

ዓለምቀፍ የገንዘብ ኮርፖሬሽን ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ጋር ተፈረመ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:01 0:00

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG