በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን

ፈረንሣይን ሲንጣት ከከረመው ፀረ-መንግሥት ተቃውሞ በኋላ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ ወጥተው ባደረጉት ንግግር በርካታ የምጣኔ ኃብት ማሻሻያ ቃሎች ገብተዋል። ይሁን እንጂ ሥልጣናቸውን እንደማይለቅቁ ተናግረዋል።

ፈረንሣይን ሲንጣት ከከረመው ፀረ-መንግሥት ተቃውሞ በኋላ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ ወጥተው ባደረጉት ንግግር በርካታ የምጣኔ ኃብት ማሻሻያ ቃሎች ገብተዋል። ይሁን እንጂ ሥልጣናቸውን እንደማይለቅቁ ተናግረዋል።

“በርግጥ ሰዎችን በንግግሮቼ አስቀይሜ ሊሆን ይችላል፤ ለዚህ የራሴን ኃላፊነት እወስዳለሁ” ብለዋል ማክሮን በዛሬው ንግግራቸው።

የግብር ጭማሪ ሃሣባቸውም “ፍትሃዊ አይደለም” ሲሉ አምነዋል። ይሁን እንጂ የሰሞኑ ቁጣ የገነፈለው ላለፉት አርባ ዓመታት በተለይ በገጠሪቱ ፈረንሣይ ሲንተከተክ ከቆየ በኋላ ነው ብለዋል።

"ለዴሞክራሲያችን ዘብ እንቁም"

ጃን ኬሪ

"ለዴሞክራሲያችን ዘብ እንቁም" ያሉ አርባ አራት የዩናይትድ ስቴትስ የቀድሞ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤቱ አባላት ሃገራቸው አደገኛ ሲሉ ወደጠሩት ምዕራፍ እየተሸጋገረች እንደሆነች ገለፁ።

"ለዴሞክራሲያችን ዘብ እንቁም" ያሉ አርባ አራት የዩናይትድ ስቴትስ የቀድሞ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤቱ አባላት ሃገራቸው አደገኛ ሲሉ ወደጠሩት ምዕራፍ እየተሸጋገረች እንደሆነች ገለፁ።

የሁለቱም ፓርቲዎች አባላት የሆኑት የቀድሞ ሴናተሮች በዛሬው የዋሺንግተን ፖስት ዕትም ላይ ባወጡት የጋራ መልዕክታቸውን ያዘለ ፅሁፍ “የሕግ የበላይነት፣ ሕገመንግሥቱ፣ ገዥ ተቋሞቻችንና የሃገራችን ብሔራዊ ደኅንነት ተደቅነውባቸዋል” ያሉት ብርቱ ፈተና እያሳሰባቸው መሆኑንና በዚያም ምክንያት የአሁኖቹ እንደራሴዎች የፓርቲ አባልነትና ታማኝነታቸው “ሃገራቸውን ከአደጋ በመጠበቅ መንገድ ላይ ሊቆምባቸው አይገባም” ሲሉ ጥሪ አስተላልፈዋል።

ፅሁፉን ካወጡት የቀድሞ ሴናተሮች መካከል ዴሞክራቶቹ ጃን ኬሪ፣ ታም ዳሽልና ክሪስ ዶድ፤ እንዲሁም ሪፐሊካኑ ጃን ዋርነር፣ ሪቻርድ ላጋርና ቸክ ሄግል ይገኙበታል።

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG