በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የታሪክ ትምሕርት መምሕር ረዳት ፕሮፌሰር አቶ አበባው አያሌው ከአዲስ አበባ፣ አቶ አሉላ ሰለሞን ከዋሽንግተን ዲሲና አቶ ገረሱ ቱፋ ከአምስተርዳም

ለ18 ቀናት ስብሰባ የተቀመጠው ገዢው ፓርቲ በመጨረሻ ቅዳሜ ዕለት ያወጣውን የጹሑፍ መግለጫ በተመለከተ የተለየያዩ አስተያየቶች እየተሰጡ ይገኛሉ። በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የታሪክ ትምሕርት መምሕር ረዳት ፕሮፌሰር አቶ አበባው አያሌው ከአዲስ አበባ፣ አቶ አሉላ ሰለሞን ከዋሽንግተን ዲሲና አቶ ገረሱ ቱፋ ከአምስተርዳም በመግለጫው ላይ ተወያተዋል።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የታሪክ ትምሕርት መምሕር ረዳት ፕሮፌሰር አቶ አበባው አያሌው፤ "የኢሕአዴግ መግለጫ ከሕዝብ ይልቅ ፓርቲው ላይ ትኩረት ያደረገና ሀገሪቱ ያለችበት ችግር ትኩረት ውስጥ ያላስገባ ነው" ብሎታል።

አቶ አሉላ ሰለሞን ደግሞ "መግለጫው ብዙ ነገሮችን ከግምት ውስጥ ያስገባ ተግባራዊ ሲደረግ ውጤት የሚያመጣ ነው" ብሎታል።

አቶ ገረሱ ቱፋ፤ "ኢሕአዴግ እንደ ድርጅት መቀጠል ከፈለገ የነበረውን ዕድል ያበላሸና ችግሮች እየተወሳሰቡ እንዲሄዱ መንገድ የከፈተ ነው" ይላል።

ሁሉንም ከውይይቱ ተከታተሉት።

የኢሕዴግ መግለጫ - አስተያየት ተሰጥቶበታል
please wait

No media source currently available

0:00 0:15:31 0:00

የኢንተርኔት ጸሐፊው በፍቃዱ ኃይሉና የሰብዓዊ መብት ተከራካሪው አቶ ያሬድ ኃይለማርያም ናቸው።

የሰብዓዊ መብት ተከራካሪው አቶ ያሬድ ኃይለማርያምና የዞን ዘጠኝ የኢንተርኔት ጸሐፊው በፍቃዱ ኃይሉ በየትኛውም ቋንቋ ቢገለፅ ኢትዮጵያ ውስጥ ቁጥራቸው እንኳን በግልፅ የማይታወቅ የፖለቲካ እስረኞች መኖራቸውን ይናገራሉ።

የገዢው ፓርቲ ኢሕአዴግ የግምገማ ማጠናቀቂያ ጹሑፍና ተከትሎ የተሰጠው መግለጫ አነጋጋሪው የሳምንቱ ጉዳይ ነበር። ከመግለጫው በኋላም “ፖለቲከኞች” እና “የፖለቲካ እስረኞች” የሚለው አገላለፅም እንዲሁ መምታታትን የፈጠር ሆኖ ሰንብቷል።

በሳምንቱ ውስጥ ያነጋገርናቸው አስተያየት ሰጪዎች በየትኛውም ቋንቋ ቢገለፅ ኢትዮጵያ ውስጥ ቁጥራቸው እንኳን በግልፅ የማይታወቅ የፖለቲካ እስረኞች መኖራቸውን ይናገራሉ።

ጽዮን ግርማ “የፖለቲካ እስረኛ ማለት ምን ማለት ነው? ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የፖለተካ እስረኛ ማነው?” የሚል ጥያቄን አንስታ መቀመጫውን ጄኔቫ፣ ስዊዘርላንድ ያደረገው ‘ስብስብ ለሰብኣዊ መብቶች በኢትዮጵያ’ ተብሎ የሚጠራ የሰብአዊ መብት ድርጅት ዋና ዳይሬክተር አቶ ያሬድ ኃይለማርያምን ጠይቃለች። የዞን ዘጠኝ ጸሐፊው በፍቃዱ ኃይሉ በተመሳሳይ አስተያየቱን ተጠይቋል።

በኢትዮጵያ ያለውን መንግሥት ፖሊሲውን፣ አፈፃፀሙን እና ድርጊቱን በመቃወማቸው፣ በመጻፋቸውና የፖለቲካና የኢኮኖሚ እኩልነት በመጠየቃቸው፣ መንግሥት በኃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ መግባት የለበትም በማለታቸው፣ የማንነትና የመሬት ይዞታን ማስከበር በመጠየቃቸው ሁሉ የታሰሩ "የፖለቲካ እስረኞች ናቸው " - ይላሉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾቹ።
"ከእነዚህም ውስጥ የሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴዎች፣ በዋልድባ ገዳም ጉዳይ የታሠሩ መነኮሳት፣ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች፣ጋዜጠኞች ፣ የወልቃይት የማንነት ጥያቄ ኮሚቴዎች፣ ፍትሕዊ የሀብት ክፍፍልና የመሬት ቅርምትን ተቃውመው የታሰሩ፣ ከጋምቤላ፣ ከኮንሶ የታሰሩ፣ ሐሳባቸውን በመግለፃቸው የታሰሩ፣ በአማራና በኦሮሚያ ሕዝባዊ ተቃውሞ ውስጥ ተሳትፋችኋል በሚል የታሰሩ ወጣቶች በአጠቃላይ ቁጥራቸው ተለይቶ የማይታወቁ "በሺዎች" የሚቆጠሩ የፖለቲካ እስረኞች በሀገሪቱ አሉ" ይላሉ - የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾቹ። ዝርዝሩን አዳምጡት

በዚህ ዙሪያ የተሰናዳውን ዘገባ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

የ"ፖለቲካ እስረኛ " ማነው?
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:25 0:00

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG