በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

ኢትዮጵያና ኤርትራ

በሰሜን ወሎ በወልዲያ፣ በመርሳ፣ በቆቦና በሌሎች የዞኑ ከተሞች ከተፈጠረው ግጭት በኋላ ዛሬም ሰዎች እየታሰሩ መሆኑን ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምጽ ገለጹ።

በሰሜን ወሎ ዞን ሰዎች እየታሰሩ መሆኑን ነዋሪዎች ገለፁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:22 0:00

ሰሜን ወሎ ዞን በወልዲያ፣በቆቦና በመርሳ ከተሞች ዛሬም ተረጋግቶ የሥራ እንቅስቃሴ አለመጀመሩን ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል። ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

አቶ በቀለ ገርባ ፍርድ ቤት በቀረቡበት ወቅት ከማኅበራዊ ድረ ገፅ(ፌስቡክ) ላይ የተገኘ

በምንሊክ ሆስፒታል የመረመራቸው ሃኪም ተጨማሪ ሕክብና በአስቸኳይ የማያገኙ ከሆነ ለሁልጊዜ ማየት ሊከለክላቸው እንደሚችል በሃኪም እንደተነገራቸው ልጃቸው ለአሜሪካ ድምፅ ተናግራለች። ማረሚያ ቤቱ ወደ ግል ሆስፒታል ሊወስዳቸው እንደማይችል እንደገለፀላቸውም ጠቁማለች።

በእስር ላይ የሚገኙት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ ደም ግፊታቸው በመጨመሩ ምክኒያት የግራ ዐይናቸው መጎዳቱን ልጃቸው ቦንቱ በቀለ ገልፃ በአስቸኳይ ተጨመሪ ሕክምና ካላገኙ ለሁልጊዜ ማየት ሊከለክላቸው እንደሚችል በሃኪም እንደተነገራቸው ተናግራለች።

ቦንቱ በቀለ የአባቷን ሁኔታ በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥታናለች።

አቶ በቀለ ገርባ ግራ ዐይናቸው መጎዳቱን ልጃቸው ቦንቱ በቀለ ገለፀች
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:34 0:00

Congressman Mike Coffman
በUS ምክር ቤት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ረቂቅ ሕግ ቀጣይ እጣ እና ...
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:37 0:00

በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩ ግፊት ለማድረግ በሚል ባለፈው ዓመት በየካቲት ወር መጀመሪያ ለዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት የቀረበ ረቂቅ ሕግ ቀጣይ ሂደት ዙሪያ የተካሄደ ጋዜጣዊ ጉባኤ ነው የቀጣዩ ዘገባ መነሻ።

ባሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የሚታየው ሁኔታ ካልተለወጠ HR-128 የሚል መጠሪያ የተሰጠው ይህ ረቂቅ ሕግ ወደ ሙሉ ምክር ቤቱ የሚተላለፍና ሊጸድቅ የሚችል መሆኑ ነው፤ በምክር ቤቱ የብዙኃኑ ፓርቲ ተጠሪ በተገኙበት በተካሄደው ጋዜጣዊ ጉባኤ የተገለጸው።

በኢትዮጵያ ተፈጽመዋልና እየተፈጸሙ ናቸው የሚላቸውን የመብት ጥሰቶች የሚያወግዘው ባለፈው ዓመት በየካቲት ወር መጀመሪያ የቀረበው ይህ የሕግ ረቂቅ፤ በኢትዮጵያ የዜጎችን ሰብዓዊ መብት ከበሬታ መረጋገጥ እና ብሎም ሁሉን አቀፍ አስተዳደር መፈጠር የታለመ መሆኑን ይዘረዝራል።

ኮንግሬስማን ማይክል ሃዋርድ ኮፍማን በUS የተወካዮች ምክር ቤት የኮሎራዶ ክፍለ ግዛት ስድስተኛው የምክር ቤታዊ የአስተዳደር ክልል ተወካይ ናቸው።

ረቂቅ ሕጉ ያለበትን ሁኔታ እንዲያስረዱ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት መልስ፤ ከምክር ቤቱ አመራር አባላት ጋር ባደረግናቸው ንግግሮች “በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብትና አስተዳደር ጉዳዮች ያሉትን አማራጮች ለማየት ከሚያስችለን ስምምነት ላይ ደርሰናል፤” ይላሉ።

“የኢትዮጵያ መንግስት እስረኞችን እየፈታ ነው፤ አንዳንድ መሻሻሎችንም እያደረገ ነው፤ እናም በረቂቅ ሕጉ ላይ ድምጽ ከመ’ሰጠቱና ከመጽደቁ አስቀድሞ ነገሮችን ወደሚፈለገው አቅጣጫ ይወስዳል፤” የሚል አስተያየትም ተነስቷል። በእርግጥ እኔ በዚያ ግምት አልስማም። ለሁሉም የምናየው ይሆናል። ካልሆነም ረቂቅ ሕጉ እውን ወደሚሆንበት መንገድ እናመራለን።” የሚሉት ኮንግሬስማን ኮፍማን የጊዜ ገደቡ እየተጤነ መሆኑንም ጨምረው ገልጠዋል።

ሁኔታዎች ተሥፋ እንደተጣለባቸው ባይይዙና ቀደም ብለው እንደገለጹት የሕግ ረቂቁን ተፈጻሚ ወደሚያደርገው አማራጭ የሚኬድ ቢሆን፤ በእርግጥ ሕጉ ምን ዓይነት ጉዳዮች ላይ ተፈጻሚነት ያስገኝ ይሆን? በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄም ኮፍማን እንዲህ ይመልሳሉ።

“ዩናይትድ ስቴትስ በክልሉ ላላት በብሔራዊ ደህንነት ጉዳዮች ዙሪያ ትኩረት ለሚያደርገው ግንኙነቷ ቅድሚያ በመስጠት በኢትዮጵያ መንግስት የሚፈጽሙትን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ለረዥም ጊዜ አይታ እንዳላየች ስታደርግ ቆይታለች። ያ! ፍጹም የተሳሳተ ነገር ነው። በመሆኑም ይሄ ያን ስህተት የማመን የመጀመሪያ እርምጃ ነው። የኢትዮጵያ መንግስት በገዛ ዜጎቹ ላይ የሚፈጽመው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ፈጽሞ ተቀባይነት የለውም።”

የመቶ ሚልዮን ሕዝብ መኖሪያ የሆነችው፤ በአፍሪቃ ቀንድ ዋነኛዋ የዩናይትድ ስቴትስ ሃጋር የሆነችው ኢትዮጵያ፥ የፖለቲካ ቀውስ ውስጥ መሆኗ እየተዘገበ ነው። ለመሆኑ ያች ሃገር ቀውሱ ተባብሶ የከፉ ሁኔታዎች ውስጥ እንዳትወድቅ የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ሊወስዳቸው የሚችላቸው እርምጃዎች ይኖሩ ይሆን? ለሚለውም ኮፍማን ጥረታቸው ያ እንዳይሆን መሆኑን ያስረዳሉ።

“ቀውስ በተንሰራፋበት የሚሆነውን እናውቃለን። እርግጥ ነው፤ የኢትዮጵያ መንግስት የገዛ ዜጎቹ ላይ ሽብር እየፈጸመ ነው። መንግስት አልባነት በኢራቅ ይሁን በሊቢያ ያደረገው ቢኖር፤ የአሸባሪዎች መፈልፈያ መሆን ነው። የኢትዮጵያ መንግስት ሁኔታዎቹን መለወጥ አለበት። የዚህ ረቂቅ ሕግ መመሪያም ሆነ ሌላው እየሠራን ያለነው ያን ለመከላከል ነው።” ይላሉ።

የአሜሪካ ድምፅ በዌብ ሳይቱና በፌስ ቡክ ገፆቹ የፕሬዚዳንቱን ንግግር በቀጥታ የሚያስተላልፍ ሲሆን በፕሬዚዳንቱ ንግግር ወቅት የየርዕሰ ጉዳዩን ማጠቃለያም በአማርኛው የፌስ ቡክ ገፅ ላይ ያወጣል፤ ተከታተሉት።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ ሃገራቸው የምትገኝበትን አጠቃላይ ሁኔታ የሚዘረዝረውንና የወደፊት አቅጣጫቸውን የሚያመላክቱበትን የመጀመሪያ ንግግራቸውን ለተወካዮች ምክር ቤቱ ጥምር ጉባዔ ዛሬ ማታ ያደርጋሉ።

ፕሬዚደንቱ ለሀገር ውስጥና ለውጭውም ያላቸውን እና ገና የተጀመረውን የአውሮፓ 2018 ዓመተ ምኅረት ትልም የሚያዳምጡት በኮንግሬሱ አዳራሽ ውስጥ የሚታደሙት እንደራሴዎች ብቻ ሳይሆኑ በግዙፎቹ የቴሌቪዥን መረቦች በቀጥታ በሚተላለፉ ሥርጭቶች የመላው ዓለም ህዝብም ይከታተለዋል።

ትረምፕ ይህንን ንግግራቸውን የሚያደርጉት በሀገሪቱ የግብርና ቀረጥ ህግ ማሻሻያ ላይ ድል አጎናጽፏቸዋል የተባለ ውሣኔ በተወካዮች ምክር ቤቱ ከተላለፈላቸውና ፈርመውም የሀገሪቱ የታክስ ህግ ባደረጉት ሰሞን ቢሆንም ያለፈው ፕሬዚደንታዊ ዓመታቸው በብዙ ወጀብ እና ትርምስ የታጀበ እንደነበርም ታዛቢዎች እየተናገሩ ናቸው ።

ፕሬዚደንት ትረምፕ ባሳለፉት አንድ ዓመት ለአዲስ ፕሬዚደንት በዩናይትድ ስቴትስ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ እጅግ የወረደ የህዝብ ተቀባይነት ያላቸው ፕሬዚደንት መሆናቸውንም የህዝብ አስተያየት ክትትል አኀዞች ያሳያሉ።

የአሜሪካ ድምፅ በዌብ ሳይቱና በፌስ ቡክ ገፆቹ የፕሬዚዳንቱን ንግግር በቀጥታ የሚያስተላልፍ ሲሆን በፕሬዚዳንቱ ንግግር ወቅት የየርዕሰ ጉዳዩን ማጠቃለያም በአማርኛው የፌስ ቡክ ገፅ ላይ ያወጣል፤ ተከታተሉት።

ለተጨማሪ የተያይዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ፕሬዚዳንት ትረምፕ ዛሬ ምሽት ለኮንግረሱ ንግግር ያደርጋሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:52 0:00

በምኅፃር ናሳ (NASA) ተብሎ የሚጠራው የኬንያው ግዙፍ የተቃውሞ ጥምረት ብሄራዊ እምቢ ባይነት ንቅናቄ “የወንጀል ቡድን ነው” ሲል የሀገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስቴሩ አስታወቀ።

በምኅፃር ናሳ (NASA) ተብሎ የሚጠራው የኬንያው ግዙፍ የተቃውሞ ጥምረት ብሄራዊ እምቢ ባይነት ንቅናቄ “የወንጀል ቡድን ነው” ሲል የሀገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስቴሩ አስታወቀ።

የራይላ ኦዲንጋ ደጋፊዎች በኡሁሩ አደባባይ
የራይላ ኦዲንጋ ደጋፊዎች በኡሁሩ አደባባይ

መሥሪያ ቤቱ መግለጫውን ያወጣው የናሳ መሪ ራይላ ኦዲንጋ ዛሬ እንደ ፕሬዚደንት ቃለ­‑መሃላ ከፈፀሙ በኋላ ነው።

ኦዲንጋ የዛሬውን ቃለ‑መሃላቸውን በሺሆች በሚቆጠሩ ደጋፊዎች ፊት አደባባይ ላይ የፈፀሙት ያለፈውን ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ውጤት እንደማይቀበሉ አሳውቀው ከምርጫው ከወጡ በኋላ መሆኑ ነው።

ሚኒስቴሩ አድራጎቱን “በመንግሥት ላይ የተፈፀመ ክህደት እና አመፃ” ነው ሲል ከስሷል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

“የሕዝብ ፕሬዚዳንት?” ኦዲንጋ ቃለ¬¬¬¬ መሃላ ፈፀሙ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:11 0:00

XS
SM
MD
LG