በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

የአፍሪካ ሕብረት ጉባዔ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ይገኛል። በዛሬው ዕለት አፍሪካ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ያላትን የንግድና ምጣኔ ኃብት ትስስር የተመለከተ ውይይት ተካሂዷል።

የአፍሪካ ሕብረት ጉባዔ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ይገኛል። በዛሬው ዕለት አፍሪካ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ያላትን የንግድና ምጣኔ ኃብት ትስስር የተመለከተ ውይይት ተካሂዷል።

የኢትዮጵያውን ጠቅላይ ሚኒስትር ጨምሮ ሌሎች ሦስት የአፍሪካ መሪዎች በተገኙበት ጉባዔ የንግድና ኢንቨስትመንት ትስስሩን ለማጠናከር አሜሪካ ያላትን ቁርጠኝነት በአፍሪካ ሕብረት የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ተናግረዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

አፍሪካ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ያላት የንግድና ምጣኔ ኃብት ትስስር
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:25 0:00

ንግድና ኢንቨስትመንት ለአፍሪካ መፃዒ ዕጣ ያላቸውን አስፈላጊነት እንደሚረዱ የገለፁ የአፍሪካ መሪዎች ለኢንቨስትመንት ምቹ የሆነ ሁኔታ ለመፍጠር የሚያደርጉትን ጥረት እያፋጠኑ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ንግድና ኢንቨስትመንት ለአፍሪካ መፃዒ ዕጣ ያላቸውን አስፈላጊነት እንደሚረዱ የገለፁ የአፍሪካ መሪዎች ለኢንቨስትመንት ምቹ የሆነ ሁኔታ ለመፍጠር የሚያደርጉትን ጥረት እያፋጠኑ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በአህጉሪቱ ምቹ የሆኑ የንግድና ኢንቨስትመንት ፖሊሲዎች እንዲኖሩ ለማስቻል እየሠራ መሆኑን የገለፀው ደግሞ የዩናይትድ ስቴጽ ኩባንያዎች ማኅበር የሆነው “የንግድ ተቋማት ምክር ቤት በአፍሪካ ጉዳይ” ወይም “Corporate Council on Africa” የተሰኘው ተቋም ነው።

ተቋሙ ከተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ጋር በመሆን ያዘጋጀውን የውይይት መድረክ መክፈቻ ዘገባ።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የአፍሪካ መሪዎች - ስለአፍሪካ የንግድና የኢንቨስትመንት ፖሊሲዎች
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:26 0:00

በሰሜን ወሎ በወልዲያ፣ በመርሳ፣ በቆቦና በሌሎች የዞኑ ከተሞች ውጥረት እስከዛሬ መቀጠሉንና ወጣቶች ከየቤቱ እየተለቀሙ እየታሰሩ መሆኑን ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ገለጹ።

የሰሜን ወሎ ዞን የዛሬ ውሎ- በመርሳ ዛሬ ወጣቶች መደብደባቸውን ነዋሪዎች ገልፀዋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:12:13 0:00

“በመርሳ የታሰሩ ይፈቱ” በሚል የጠየቁ ወጣቶች በአሰቃቂ ሁኔታ በታጣቂዎች መደብደባቸውን የዐይን እማኝ ነኝ ያሉ ነዋሪ ተናግረዋል። በከተሞቹ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችም ሆነ ንግድ ቤቶች መዘጋቱን በምትኩ በየፌዴራል አድማ በታኝና ነዋሪዎች “አጋዚ” እያሉ በሚጠሯቸው “ልዩ ሃይሎች” ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ይናገራሉ።

የመርሳ ከተማ ከንቲባ ከተማዋን ለማረጋጋት የሀገር ሽማግሌዎች ባሉበት ተነጋግረን ተስማምተን ተለያይተናል ብለዋል። ሽማግሌዎቹ የተስማማነው ነገር የለም ይላሉ።

ዝርዝርሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

የሩስያ ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን

ዩናይትድ ስቴትስ ከሩስያ ክሬምሊን ቤተ መንግሥት ጋር የቅርብ ግንኙነት ያላቸውን ሁለት መቶ አስር ሰዎች ሃብት እና የፖለቲካ ግንኙነቶቻቸውን በዝርዝር ይፋ ማድረጓ "የጠላት ተግባር ነው" ሲሉ የሩስያ ፕሬዚደንት ቪላዲሚር ፑቲን ተናገሩ። ሆኖም ሃገራቸው ባፋጣኝ የበቀል ርምጃ ለመውሰድ አትንቀሳቀስም ብለዋል።

ዩናይትድ ስቴትስ ከሩስያ ክሬምሊን ቤተ መንግሥት ጋር የቅርብ ግንኙነት ያላቸውን ሁለት መቶ አስር ሰዎች ሃብት እና የፖለቲካ ግንኙነቶቻቸውን በዝርዝር ይፋ ማድረጓ "የጠላት ተግባር ነው" ሲሉ የሩስያ ፕሬዚደንት ቭላዲሚር ፑቲን ተናገሩ። ሆኖም ሃገራቸው ባፋጣኝ የበቀል ርምጃ ለመውሰድ አትንቀሳቀስም ብለዋል።
የዩናይትድ ስቴትስ ኮንግሬስ ሩስያ በአምናው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ጣልቃ በመግባትዋ ለመቅጣት ባለፈው ነሃሴ ወር ባጽደቀው ህግ መሰረት የገንዘብ ሚኒስቴር የመዝገቡን ትናንት ሰኞ ይፋ አድርጉዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ህጉን እያመነቱ መፈረማቸው ሲታወስ ትናንት የአስተዳደራቸው ባለሥልጣናት በክሬምሊን ላይ አዲስ ማዕቀብ ለመጣል ለጊዜው ዕቅድ እንደሌለ ተናግረዋል። የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሄዘር ኑዌርት በጽሁፍ ባወጡት መግለጫ ህጉ ከወዲሁ የሩስያን ኩባኒያዎች እየጎዳ ነው ብለዋል።
በርካታ የሩስያ ባለሥልጣናት በሪፖርቱ የተቆጡ ሲሆን ጠቅላይ ምኒስትር ዲሚትሪ ሜድቬየዴየቭ ”ግንኙነታችንን ለረጅም ጊዜ የሚመርዝ ነው” ብለዋል።

ዛሬ ሞስኮ ውስጥ በአንድ የምረጡኝ ዘመቻ ዝግጅት ላይ ለዘብ ባለ መልኩ የተናገሩት ፕሬዚዳንት ፑቲን ግን ዝርዝሩ ይፋ መደረጉ ያሳዘነን ቢሆንም ለጊዜው የበቀል ርምጃ ከመውሰድ እንቆጠባለን ብለዋል።

የትረምፕ አስተዳደር "ከፍተኛ አደጋ የሚደቅኑ" ተብለው ከተፈረጁ አስራ አንድ ሃገሮች ወደዩናይትድ ስቴትስ ለመምጣት አመልካቾችን ታሪክ ላይ ጥልቅ የሆነ ፍተሻ በማድረግ የስደተኛ መቀበል ፖሊሲውን እያጠበቀ መሆኑ ተገልጿል።

የትረምፕ አስተዳደር "ከፍተኛ አደጋ የሚደቅኑ" ተብለው ከተፈረጁ አስራ አንድ ሃገሮች ወደዩናይትድ ስቴትስ ለመምጣት አመልካቾችን ታሪክ ላይ ጥልቅ የሆነ ፍተሻ በማድረግ የስደተኛ መቀበል ፖሊሲውን እያጠበቀ መሆኑ ተገልጿል።
ባለሥልጣናት ይህንኑ ትናንት ይፋ ባደረጉበት ወቅት የትኞቹ ሃገሮች አንደሆኑ ለጋዜጠኞች በዝርዝር ለመናገር ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል። ይሁን እንጂ ሀገሮቹ ግብጽ፣ ኢራን፣ ኢራቅ፣ ሊቢያ፣ ማሊ፣ ሰሜን ኮሪያ፣ ሶማሊያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሱዳን እና የመን እንደሆኑ በስፋት ሲዘገብ ቆይቱዋል።
አንዱ ከፊተኛው የሚለየው ከአስራ አንዱ ሀገሮች በሆኑት ስደተኞች ላይ ይበልጡን ጥልቀት ያለው ቃለ መጠይቅ የሚደረግ መሆኑ ነው ብለዋል። አብዛኛው የስደተኞች አቀባበል ለውጥ እኤአ ከፊታችን መጋቢት ወር መጨረሻ ሥራ ላይ እንደሚውል ከባለሥልጣናቱ አንዱ ገልፀዋል።

ዩናይትድ ስትቴትስ ኖርዌይና ብሪታንያ ደቡብ ሱዳን የሚዋጉት ሁሉም ወገኖች አሁንም በብዙ አስር ሺሕዎች የሚቆጠሩ ልጆችን ለተዋጊነት መመልመላቸውን መቀጠላቸው ያሳሰባቸው መሆኑን ገለፁ።

ዩናይትድ ስቴስ ትቴትስ ኖርዌይና ብሪታንያ ደቡብ ሱዳን የሚዋጉት ሁሉም ወገኖች አሁንም በብዙ አስር ሺሕዎች የሚቆጠሩ ልጆችን ለተዋጊነት መመልመላቸውን መቀጠላቸው ያሳሰባቸው መሆኑን ገለፁ።
"ትሮኢካ ሦስቱ" በሚል ቅፅል ስም የሚጠሩት ሃገሮች ትናንት ሰኞ ባወጡት መግለጫ የመንግሥቱ ኃይሎች በተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ታባን ዴንግ ጋይ የሚመራው አንጃ እና የሽምቅ ተዋጊ መሪ ሪያክ ማቻር ተዋጊዎች ልጆችን በተዋጊነት በማሰማራትና በመመልመል ተጠያቂ እንደሆኑ አመልክተዋል።

XS
SM
MD
LG