በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

ፎቶ ፋይል፡- የኢትዮጵያ፣ የግብፅና የሱዳን መሪዎች

የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ የተሳተፉት የኢትዮጵያ፣ የግብፅና የሱዳን መሪዎች በሦስትዮሽ ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሂደዋል፡፡

የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ የተሳተፉት የኢትዮጵያ፣ የግብፅና የሱዳን መሪዎች በሦስትዮሽ ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሂደዋል፡፡

ውይይቱ የተሳካ እና ውጤት የተገኘበት መሆኑን የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል፡፡

አቶ መለስ ከውይይቱ ተገኘ የሚሉትን ውጤት በማብራራት ይጀምራሉ፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የኢትዮጵያ፣ የግብፅና የሱዳን መሪዎች በሦስትዮሽ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:54 0:00

በሰሜን ወሎ ዞን እስካሁን ውጥረት መንገሱን ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል። በወልዲያ፣ በቆቦ በመርሳና የንግድና የሥራ እንቅስቃሴ መቋረጡን ትምሕርት ቤት መዘጋቱን ነዋሪዎቹ ጨምረው ተናግረዋል።

የሰሜን ወሎ ዞን ሦስት ከተሞች የዛሬ ውሎ
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:48 0:00

ከዐሥር ቀናት በፊት በወልዲያ ከተማ የጥምቀት በዓል በማክበር ላይ እያሉ የተገደሉ ሰዎችን በፀሎት ለማሰብ በዛሬው ዕለት በወልዲያ ከተማ የጧፍ ማብራት ሥነ ስርዓት እያከናወኑ ባለበት ወቅት ተኩስ እንደተከፈተባቸው ያነጋገርናቸው የወልዲያ ከተማ ነዋሪዎች ገልፀውልናል።

በወልዲያ፣ በቆቦ በመርሳና የንግድና የሥራ እንቅስቃሴ መቋረጡን ትምሕርት ቤት መዘጋቱንም ጨምረው ነዋሪዎቹ ጨምረው ተናግረዋል።

የአካባቢው ወጣቶችና የሀገር ሽማግሌዎች የታሰሩ ሰዎችን ለማስፈታት ጥረት እያደረጉ መሆኑን የገለፁልን ነዋሪዎቹ በአንፃሩ ደግሞ ወጣቶች እየታሰሩ መሆኑ ተናግረዋል

በእነዚህ ከተሞች በተከታታይ በነበረው ሕዝባዊ ተቃውሞና ግጭት የሰው ሕይወት መጥፋቱን፣ አካል መጉደሉንና ንብረት መውደሙን ነዋሪዎችና መንግስት አስታውቋል።

የክልሉ መንግሥት ለዚህ አለመረጋጋት በመንግሥት በኩል ለሕዝቡ ጥያቄ በአፋጣኝ ምላሽ አለመሰጠቱ መሆኑን አስታውቋል። ሕይወታቸው ለጠፋውና አካላቸው ለጎደሉ ሰዎች የተሰማውን ሐዘን በመግለፅ መፅናናቱን ተመኝቷል። ግጭቶቹ መልካቸውን እንዲቀይሩ በተሰራው ሥራ ማንነታቸውን ብቻ ተስተውሎ ጥቃት በደረሰባቸው ሰዎች ማዘኑንም የክልሉ መንግስት አስታውቋል።

የዘገባውን ሙሉ ዝርዝር ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።

የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ

ትላንት የተከፈተው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ አሁን ማማሻውን ተጠናቋል። በሙስና ላይ የሚካሄደውን ትግል በማሸናፍ ላይ እንደሚያተኩር የተገልፀው ይኸው ጉባዔ ሌሎች ውሳኔዎችም ይፋ ተደርገውበታል።

ትላንት የተከፈተው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ አሁን ማማሻውን ተጠናቋል። በሙስና ላይ የሚካሄደውን ትግል በማሸናፍ ላይ እንደሚያተኩር የተገልፀው ይኸው ጉባዔ ሌሎች ውሳኔዎችም ይፋ ተደርገውበታል።

የሕብረቱ ሊቀመንበር ሆነው የተመረጡት የሩዋንዳው ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ አፍሪካውያን በአህጉሪቱ ውስጥ በአንድ ፓስፖርት እንዲንቀሳቀሱ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ይፋ አድርገዋል።

በጉባዔው መክፈቻ ላይ በተጋባዥነት የተናገሩት የፍልስጤም አስተዳደ ሙሐሙድ አባስ ደግሞ ሀገራት በእየሩሳሌም ምንም ዓይነት ኢንባሲ ከመክፈት እንዲቆጠቡ ጠይቀዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ውሳኔዎችን በማስተላለፍ ተጠናቀቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:06 0:00

አፍጋኒስታን ዋና ከተማ ካቡል ውስጥ በሚገኝ አንድ ወታደታዊ አካዳሚ በደረሰ ጥቃት፣ 11 የአፍጋኒስታን ብሔራዊ ጦር ኃይል አባላት ሲገደሉ ሌሎች 16 መቁሰላተው ተገለፀ።

አፍጋኒስታን ዋና ከተማ ካቡል ውስጥ በሚገኝ አንድ ወታደታዊ አካዳሚ በደረሰ ጥቃት፣ 11 የአፍጋኒስታን ብሔራዊ ጦር ኃይል አባላት ሲገደሉ ሌሎች 16 መቁሰላተው ተገለፀ።

ጥቃቱ በአካዳሚዎ ላይ ሳይሆን አካዳሚውን በሚጠብቁ ወታደሮች ላይ ያነጣጠረ እንደነበር፣ የአፍጋኒስታን መከላከያ ሚኒስቴር ቃልአባይ ዳወላተ ዋዚሪ አስታውቀዋል። ውጊያው፣ በማርሻል ፋሂም ብሔራዊ የመከላከያ ዩኒቨርሲቲ አካባቢ ከሰዓት በኋላም ቀጥሎ መዋሉ ተሰምቷል።

የመከላከያ ሚኒስቴሩ ቃልአቀባይ ዋዚሪ እንደተናገሩት፣ ጥቃቱን አምስት አጥፍቶ ጠፊዎች ናቸው ያደረሱት። ሁለቱ፣ በአካዳሚው መግቢያ በራፍ ላይ የታጠቁትን ቦምብ አፈንድተው ሲጋዩ፣ ወደ ቅጥር ጊቢው ለመግባት ከሞከሩት ከሦስቱ መካከል፣ ሁለቱ በብሔራዊው ጦር ተገድለው አንዱ በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተገልጧል።

ራሱን ስላማዊ መንግሥት ብሎ የሚጠራው ነውጠኛ ቡድን ለጥቃቱ ኃላፊነት መውሰዱንም፣ “አማቅ” በተሰኘው ዜና አውታሩ አማካኝነት ይፋ አድራል።

ፎቶ ፋይል

ከካናዳ፣ ከሜክሲኮና ከዩናይትድ ስቴትስ የተውጣጡ ከፍተኛ የንግድ ተወካዮች፣ በእንግሊዝኛው ምኅፃረ ቃል /NAFTA/ ስለሚባለው ስለ ሰሜን አሜሪካው ነፃ የንግድ ሥምምነት ለመደራደር ዛሬ ሰኞ መሰባሰባቸው ተሰማ።

ሦስቱ ሀገሮች ድርድሩን እአአ ባለፈው 2017 ለማጠናቀቅ አቅደው፣ ነገር ግን የተለያዩ ሀገሮች ባነሷቸው ጉዳዮች ምክንያት ቀኑ መጓተቱ ታውቋል።

በቅርቡ ሞንትሪያል ላይ የተካሄደው ስብሰባ፣ በተሽከርካሪ ኢንዱስትሪ ላይ በተላለፉ የክርክር ውሳኔዎች ላይ የተነሱ ጥያቄዎች ታክለው ቀርበው እንደነበር ታውቋል።

እናም በዛሬው ድርድር ውጤት ይገኛል የሚል አዎንታዊ ግምት ያለ ቢሆንም፣ በካናዳ በኩል ግን ብዙ መሠራት እንዳለበት ታውቋል።

የካናዳው ዋና ተደራዳሪ ወኪል ስቲቨ ቨርሁለ ባለፈው ቅዳሜ በተናከሩት ቃል፣ በተቻለ መጠን ወደ አዎንታዊ ውጤቱ ነው እያዘነበልን ያለንው ማለታቸው ተሰምቷል፡፡

ፈረንሳይ ውስጥ ባለማቋረጥ በጣለው ዝናብ ምክንያት፣ ፓሪስ ውስጥ የሰኒ ወንዝ ከልኩ በላይ አራት ሜትር ከፍታ ሞልቶ ጎርፍ ማስከተሉ ተነገረ።

ፈረንሳይ ውስጥ ባለማቋረጥ በጣለው ዝናብ ምክንያት፣ ፓሪስ ውስጥ የሰኒ ወንዝ ከልኩ በላይ አራት ሜትር ከፍታ ሞልቶ ጎርፍ ማስከተሉ ተነገረ።

በጎርፉ ምክንያትም ወደ 1ሺህ 5መቶ ቤተሰቦች መፈናቀላቸውና በአካባቢው ከሚገኙ ከ240 በላይ ከተሞችም መጥለቅለቃቸው ታውቋል።

የተጠራቀመው ውኃ ከፍታ 5.4ሜትር እንደሆ ነው የተገለጸው።

የመዝናኛና የቱሪስት ጀልባዎች፣ በዓለም ታዋቂው የለቨር ሙዚየም በጎርፉ ምክንያት አገልግሎት መስጠት አለመቻላቸውም ተገልጧል።

ሕዝቡ ወደ ወንዙ እንዳይሄድና ለአደጋ እንዳይጋለጥ፣ ፖሊስ እያስጠነቀቀ መሆኑም ተነግሯል።

ፈረንሳይ በጣለው ዝናብ 1ሺህ 5መቶ ቤተሰቦች ተፈናቀሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:46 0:00

ፎቶ ፋይል

ከፍተኛ የኢንፍሉዌንዛ ወረርሽኝ ስጋት መኖሩ፣ በሰሜንና በደቡብ ኮሪያዎች ዘንድ እየተሰማ መሆኑ ተነገረ።

ከፍተኛ የኢንፍሉዌንዛ ወረርሽኝ ስጋት መኖሩ፣ በሰሜንና በደቡብ ኮሪያዎች ዘንድ እየተሰማ መሆኑ ተነገረ።

ስጋቱ አሳሳቢ የሆነውም፣ ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች የተውጣጡ ጎብኚዎች ለ2018ቱ የክረምት ኦሊምፒክስ ውድድር፣ በደቡብ ኮሪያዋ ‘PyeongCang’ ሊገናኙ ከሁለት ሳምንት ያነሰ ጊዜ መሆኑ እንደሆነም ታውቋል።

የሰሜን ኮሪያ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እንዳረጋገጠው፣ እአአ ካለፈው ታህሣሥ 1/2017 እስካሁኑ ጥር 16/ 2018 ድረስ፣ 8መቶ ሰዎች በዚሁ ተላላፊ መሆኑ በተነገረለት ተስቦ ተይዘዋል። ይህንኑ የሰሜን ኮሪያ መግለጫ፣ ዓለማቀፉ የቀይ መስቀልና ቀይ ጨረቃ ማኅበር በመጽሔቱ አስፍሮት ለንባብ በቅቷል።

XS
SM
MD
LG