በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

የሽብር ወንጀል ክስ ተመስርቶባቸውና በጥፋተኝነት ውሳኔ እስር ተፈርዶባቸው የነበሩት ሁለት ጋዜጠኞች ዳርሴማ ሶሪና ካሊድ መሐመድ

የሽብር ወንጀል ክስ ተመስርቶባቸውና በጥፋተኝነት ውሳኔ እስር ተፈርዶባቸው የነበሩት ሁለት ጋዜጠኞች ዳርሴማ ሶሪና ካሊድ መሐመድን ጨምሮ ስድስት የሙስሊም ጉዳዮች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ዛሬ በአመክሮ ከእስር መለቀቃቸውን ተናገሩ።

"የተፈታነው ከይቅርታም ሆነ ከምሕረት ጋር በተያያዘ አይደለም" ሁለቱ ጋዜጠኞች
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:12 0:00

"የተፈታነው ፖለቲከኞችና ሌሎች እስረኞችን መፍታትን በተመለከተ የኢትዮጵያ መንግሥት የዛሬ ሣምንት በሰጠው መግለጫ መሰረት በይቅርታም ሆነ በምሕረት አይደለም ፍርዳችንን ጨረሰ በአመክሮ ነው” ብለዋል። አያይዘውም “መፈታት የነበረብን ከአንድ ወር በፊት በመሆኑ እንደውም እላፊ ታስረናል።” ሲሉ ለአሜሪካ ድምጽ ገልፀዋል።

አሁንም የተፈታነው “በፍርድ ቤት የአመክሮ መብታችንን አስከብረን ነው” ብለዋል። ጋዜጠኛ ካሊድ እርሱና ሌሎች እስረኞች ከእስር እስከተፈቱበት ጊዜ ድረስ ድብደባን ጨምሮ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሲፈፀምባቸው እንደነበር ገልጾ፤ “ይህንን ወደፊት በይፋ ለሕዝብ አሳውቃለሁ” ብሎናል።

የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ ምክር ቤት ሦስተኛ አስቸኳይ ስብሰባ አካሄደ

የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ ምክር ቤት ሦስተኛ አስቸኳይ ስብሰባ አካሂዶ፣ የሕወሃት ሊቀመንበር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል የክልሉ ምክትል አስተዳዳሪ ሆነው እንዲሰሩ በሕወሃት አቅራቢነት ተሹመዋል። የትግራይ ዘጋብያችን አለም ፍሰሀ ከመቀሌ የላከው ዘገባ ዝርዝሩን ይዟል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የትግራይ ክልል ምክር ቤት አዳዲስ ሹመቶች
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:25 0:00

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG