በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

ፕሬዚዳንት ቡሃሪ ከቺቦክ ልጃገረዶች ጋር

ቦኮ ሃራም ሠማኒያ ሁለት የቺቦክ ልጃገረዶች ለቀቀ አንድ መቶ አሥራ ሦስት ይቀራሉ

ቦኮ ሃራም ሠማኒያ ሁለት የቺቦክ ልጃገረዶች ለቀቀ አንድ መቶ አሥራ ሦስት ይቀራሉ

የናይጄሪያው ፅንፈኛ ቡድን ቦኮ ሃራም ከሦስት ዓመታት በፊት ሰሜን ምስራቋ ቺቦክ ከተማ ከአዳሪ ትምህርት ቤታቸው ጠልፎ ከወሰዳቸው ልጃገረዶች መካከል ሠማኒያ ሁለቱን ለቋል።

መለቀቃቸው የናይጄሪያ መንግሥት ልጃገረዶቹን እንዲያስለቅቅ ግፊት ሲያደርግ ለቆየው የማኀበረሠባዊ ሚዲያ ዘመቻ ድል ተደርጎ ታይቷል። ለቺቦክ ልጃገረዶች መለቀቅ ማኅበራዊ መገናኛ የተጫወተውን ሚና በተመለከተ ቺካ ኦዶሃ ያጠናቀረው፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ

የብዘሃ ሕይወት ጥበቃ የተወሰኑ ቦታዎችን ለብሔራዊ ፓርክነት ወይም መናፈሻነት ከመመደብ በላይ ነው።

የብዘሃ ሕይወት ጥበቃ የተወሰኑ ቦታዎችን ለብሔራዊ ፓርክነት ወይም መናፈሻነት ከመመደብ በላይ ነው።

የንግድና የትምህርት ተቋማት መክፈትም በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን በዓለም ቅርስነት የተመዘገበውን አከባቢ ለመንከባከብ እየረዳ እንደሆነ የአሜሪካ ድምጽ ሪፖርተር ፌይዝ ላፒዱስ ዘገባ ይናገራል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ

የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ትላንት ዕሁድ ባደረጉት ንግግር የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት አባላት ከፓርቲያቸው አቋም ጋር ቢጣረስም ዕውነቱን መርምረው ሃቅ እንደሚናገሩ ጥልቅ ምኜቴ ነው ብለዋል፡፡

የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ትላንት ዕሁድ ባደረጉት ንግግር የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት አባላት ከፓርቲያቸው አቋም ጋር ቢጣረስም ዕውነቱን መርምረው ሃቅ እንደሚናገሩ ጥልቅ ምኜቴ ነው ብለዋል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የመጀመሪያው ጥቁር ፕሬዚዳንት ትላንት ይህን አስተያየት የሰጡት ቦስተን ከተማ ውስጥ የጆን ኤፍ ኬኔዲን ተቋም "የፅናት ተምሳሌት" በሚል ርዕስ የሚጠራውን ሽልማት በተቀበሉበት ወቅት ነው፡፡

የኦባማ አስተያየት የተሰማው የዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት ከክንዋኔዎቻቸው በዓይነተኛነቱ ተልይቶ የሚታወቀውን የሀገሪቱን የጤና ምርሃ ግብር የሚተካ አዲስ ፖሊሲ ባፀደቀ ከጥቂት ቀናት በኋላ መሆኑ ነው፡፡

ኦባማ በርሳቸው አስተዳደር የፀደቀና በስማቸው የሚጠራ የጤና ፖሊሲ ለመሻርና ለመተካት ግፊት በማድረግ ላይ የሚገኙትን ተተኪያቸውን ዶናልድ ትራምፕን በስም ከመጥራትም ሆነ እርሳቸውን ከማመላከት ተቆጥበዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

XS
SM
MD
LG