በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

አዲስ አበባ አራት ኪሎ የአርበኞች መታሰቢያ ሃውልት

ሰባ ስድስተኛው የድልና የነፃነት ቀን በመላ ኢትዮጵያ በዓለም ዙሪያ ባሉ ኢትዮጵያዊያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ዘንድ ተከብሮ ውሏል፡፡

ሰባ ስድስተኛው የድልና የነፃነት ቀን በመላ ኢትዮጵያ በዓለም ዙሪያ ባሉ ኢትዮጵያዊያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ዘንድ ተከብሮ ውሏል፡፡

አራት ኪሎ ላይ የሚገኘው የነፃነት ኃውልት መሠረት የተጣለው፤ አደባባዩም «የነፃነት አደባባይ» ተብሎ የተሰየመው ሚያዝያ 27/1935 ዓ.ም ልክ ከቀኑ አምስት ሰዓት ከአርባ አምስት ደቂቃ ላይ ነበር፡፡ ልክ የዛሬ ሰባ አራት ዓመት መሆኑ ነው፡፡

ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ፤ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ በዝግታ እርምጃ ወደ ኃውልቱ ጠጋ ብለው «በነበረው፤ በሚመጣውና በሚከተለው ትውልዶች ስም የሚመሠክሩ» ቅርሶችን በኃውልቱ መሠረት ውስጥ አኖሩ፡፡

በላዩ ላይ የተጣፈው በጊዜው ባይነገርም በነጭ ብራና ላይ የሠፈረ ፅሁፍ ከወርቅ ሣንቲሞች ጋር በኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ተጠቅልሎ ሕዝቡ እያየ በመድፍ ቀለህ ውስጥ ተከተተ ...

በበርሜል ዓይነት ቅርፅ የተዘጋጀው ደንጊያ አምስት ሜትር ጥልቅ በሆነ ጉዳጓድ አናት ላይ እንደቆመ ሃምሣ አንድ ዓመት ዕድሜአቸው ላይ የነበሩት ንጉሠ ነገሥት ግዙፍ በሆነ ግርማ ወደ ኃውልቱ ተጠግተው «ለትውልድና ለዘመን ሁሉ ምሥክር ይሁን» ብለው ቅርሶቹ የገቡበትን በርሜል የማዕዘን ደንጊያ በዙሪያቸው ከነበሩ ጀግኖች ጋር ሆነው መሠረቱ ላይ አኖሩት ...

ንጉሤ አክሊሉ ሙሉውን ትረካ ይዟል፤ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

ሞሃመድ አብዱላሂ /ፋርማጆ/ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሣለኝ

የጎረቤት ሶማሊያ ክልላዊ መሪዎች ወደ አዲሰ አበባ ሲመጡ የቆዩት በሀገሪቱ የፌደራል መንግሥት ፈቃድና ይሁንታ መሆኑን ጠ/ሚ ኃይለማሪያም ደሣለኝ ተናግረዋል፡፡

የጎረቤት ሶማሊያ ክልላዊ መሪዎች ወደ አዲሰ አበባ ሲመጡ የቆዩት በሀገሪቱ የፌደራል መንግሥት ፈቃድና ይሁንታ መሆኑን ጠ/ሚ ኃይለማሪያም ደሣለኝ ተናግረዋል፡፡

የሀገሪቱን የውጭ ዲፕሎማሲ ግንኙነት በተመለከተ ኃላፊነት ያለበት ብቸኛ አካል የሶማሊያ ፌደራል መንግሥት ነው ብለዋል ጠ/ሚ ኃይለማሪያም ደሳለኝ፡፡

ከፕሬዚዳንት ሞሃመድ አብዱላሂ /ፋርማጆ/ ጋር ሰሞኑን በብሔራዊ ቤተመንግሥት በሰጡት መግለጫ ነው ጠ/ሚኒስተር ኃይለማሪም ደሣለኝ ሰለ ጎረቤት ሶማሊያ ክልላዊ መንግሥታት የተናገሩት፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

አፍሪካ በጋዜጦች

  • አዳነች ፍሰሀየ
Ethiopia Drought

አፍሪካ በጋዜጦች የተሰኘው ፕሮግራማችን፣ ስለ አፍሪካ ከተፃፉት፣ የተወሰኑትን ጨምቆ ያቀርባል።

አፍሪካ በጋዜጦች የተሰኘው ፕሮግራማችን፣ ስለ አፍሪካ ከተፃፉት፣ የተወሰኑትን ጨምቆ ያቀርባል።

ኢትዮጵያ ከባድ ድርቅ እንደተደቀነባት ተገለፀ፣ ጃኮብ ዙባ በገጠማቸው ተቃውሞ ምክንያት ከሠራተኞች ቀን በዓል ለመውጣት መገደዳቸው ተዘገበ፣ አፍሪካ ብሩህ ተስፋ እንዳላት ተጠቆመ የሚሉትን ርዕሶች ተካተዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

XS
SM
MD
LG