በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

ደቡብ አፍሪካ ውስጥ እየተካሄደ ያለው የዓለም ምጣኔ ኃብት ጉባዔ በድርቅና ተያያዥ የረሀብ ሁኔታዎች ምክንያት በአፍሪካ አህጉር ላይ የደቀኑትን ፈተና እየመረመረ ነው።

ደቡብ አፍሪካ ውስጥ እየተካሄደ ያለው የዓለም ምጣኔኃብት ጉባዔ በድርቅና ተያያዥ የረሀብ ሁኔታዎች ምክንያት በአፍሪካ አህጉር ላይ የደቀኑትን ፈተና እየመረመረ ነው።

መንግሥታት የምጣኔ ኃብት ፖሊሲያቸውን በምግብ ዋስትና ዙሪያ እንዲያጠናክሩም ጉባዔው መክሯል።

ጉባዔው ግብርናን ከንግድ ሥራ ፈጠራ ጋር በሚያገናኙ መስኮች ላይ ማተኮሩን ሪፖርተራችን አኒታ ፓወል ከጆሃንስበርግ ዘግባለች።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ፎቶ ፋይል

አፍሪካ ውስጥ የሚሠሩ የረድዔት ድርጅቶች በትራምፕ አስተዳደር የቀረበው የዕርዳታ ቅነሳ በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ለቸነፈር ለተጋለጡ ሰዎች ምግብ የማድረስ አቅማቸውን ሊጎዳ ይችላል ሲሉ ፍርሃታቸውን ገልፀዋል።

አፍሪካ ውስጥ የሚሠሩ የረድዔት ድርጅቶች በትራምፕ አስተዳደር የቀረበው የዕርዳታ ቅነሳ በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ለቸነፈር ለተጋለጡ ሰዎች ምግብ የማድረስ አቅማቸውን ሊጎዳ ይችላል ሲሉ ፍርሃታቸውን ገልፀዋል።

የአሜሪካ ድምጿ ሬብካ ዋርድ ድርጅቶቹ ሊገጥማቸው ስለሚችለው ፈተና የሪፊዊጂ ኢንተርናሽናል ተባለውን ድርጅት ባልደረባ ማርክ ያርኔልን አነጋግራ ተከታዩን ዘግባለች።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሺነር ዘይድ ራአድ አል ሁሴን

በተባበሩት መንግሥታት ከፍተኛ ኮሚሺነር ጋር ያደረጉት ውይይት በኢትዮጵያ ያለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ዓለም አቀፍ እውቅና እንዲያገኝ ያግዛል ሲሉ አንዳንድ የሀገር አቀፍ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ተናግረዋል፡፡

በተባበሩት መንግሥታት ከፍተኛ ኮሚሺነር ጋር ያደረጉት ውይይት በኢትዮጵያ ያለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ዓለም አቀፍ እውቅና እንዲያገኝ ያግዛል ሲሉ አንዳንድ የሀገር አቀፍ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ተናግረዋል፡፡

ኮሚሺነሩ ለመንግሥት ምክር ከመስጠት የዘለለ ተግባር ሊኖራቸው እንደማይችል የኢትዮጵያ ችግርም ከውጭ በመጡ ሰዎች ይፈታል ብለው እንደማያምኑ ግን ፓርቲዎቹ አስታውቀዋል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሺነር ዘኢድ አል ሁሴን ከገዥው ኢህአዴግና ከሀገር አቀፍ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሺነር ዘይድ ራአድ አል ሁሴን

“የኢትዮጵያ መንግሥት የሀገሪቱ መፃኢ ዕድል በእጁ ነው” ሲሉ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ከፍተኛ ኮሚሺነር አስገነዘቡ፡፡

“የኢትዮጵያ መንግሥት የሀገሪቱ መፃኢ ዕድል በእጁ ነው” ሲሉ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ከፍተኛ ኮሚሺነር አስገነዘቡ፡፡

ኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶችን በማስጠበቅ አዲስ ግስጋሴ መጀመር ከቻለችና በሕዝቧ የምትተማመን መሆንዋን ካሳየች ሁሉንም የሚጠቅም ጠንካራ እና አንድነቱን የጠበቀ ማኅበረሠብ መፍጠር እንደምትችል ገልፀዋል፡፡

“ያ ካልሆነና የምትደነቃቃፍ ከሆነች ግን” አሉ ከፍተኛ ኮሚሺነሩ ለልማት ሆነ በሕዝቡ አሉታዊ ውጤቶች ሊፈጠሩ ይችላሉ ሲሉ አሳሰቡ፡፡

ኮሚሺነሩ መንግሥት በፍርሃት ያሰራቸውንና የተፈረደባቸውም ያሏቸውን አያሌ እስረኞች እንዲፈታ ጠይቀዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

XS
SM
MD
LG