በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

ሞሃመድ አብዱላሂ /ፋርማጆ/ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሣለኝ

አልሸባብን በሁለት ዓመታት ውስጥ ለማሸነፍ የሚያስችል ስልት ማዘጋጀቱን የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሞሃመድ አብዱላሂ /ፋርማጆ/ አስታወቁ።

አልሸባብን በሁለት ዓመታት ውስጥ ለማሸነፍ የሚያስችል ስልት ማዘጋጀቱን የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሞሃመድ አብዱላሂ /ፋርማጆ/ አስታወቁ።

ለሦስት ቀናት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ የገቡት ፕሬዚዳንቱ ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሣለኝ ጋር ተነጋግረዋል መግለጫም ሰጥተዋል።

የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሞሃመድ አብዱላሂ
የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሞሃመድ አብዱላሂ

በአለፈው የካቲት የተመረጡት በአንዳንድ የመገናኛ ብዙኅንም በኢትዮጵያ ለመምጠት ዘግይተዋል ሲባሉ የነበሩት ሞሃመድ አብዱላሂ /ፋርማጆ/ ለሦስት ቀናት የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ጋዜጠኛ ዳዊት ይስሃቅ

የኤርትራ መንግሥት የታላቁ የፕሬስ ነፃነት ሽልማት ተሸላሚ የሆነውንና ላለፉት አስራ ስድስት ዓመታት በእስር ላይ የሚገኘውን ጋዜጠኛ ዳዊት ይስሃቅ መልቀቅ አለበት ሲሉ አንድ የተመድ የሰብዓዊ መብት ኤክስፐርት አሳሰቡ።

የኤርትራ መንግሥት የታላቁ የፕሬስ ነፃነት ሽልማት ተሸላሚ የሆነውንና ላለፉት አስራ ስድስት ዓመታት በእስር ላይ የሚገኘውን ጋዜጠኛ ዳዊት ይስሃቅ መልቀቅ አለበት ሲሉ አንድ የተመድ የሰብዓዊ መብት ኤክስፐርት አሳሰቡ።

የመንግሥታቱ ድርጅት ኤርትራ ሰብዓዊ መብት ይዞታ ልዩ መርማሪ ሺላ ኪታሩት የዘንድሮ የ2017 የዓለም የፕሬስ ነፃነት ሽልማት ለታሳሪው ጋዜጠኛ ዳዊት ይስሃቅ መሰጠቱን ምክንያት በማድረግ ባወጡት መግለጫ የአስመራ ባለሥልጣናት ሌሎቹንም በሕገወጥ መንገድ ያሰሩዋቸውን በሙሉ እንዲለቁ ጠይቀዋል።

ለጋዜጠኛ ዳዊት ይስሃቅ የተሰጠውን የዩኔስኮና የጉሌይረሞ ካኖ የዓለም የፕሬስ ነፃነት ሽልማት እና ሃያ አምስት ሺሕ ዶላር የጋዜጠኛው ልጅ ቤተልሄም ዳዊት ተገኝታ ተቀብላለች።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

የኢትዮጵያው አስቸኳይ ጊዜ ዓዋጅ፣ ባለፈው ዓመት በኦሮሚያ ክልል ተጀምሮ በተለይም በሰሜኑ የአማራው ክልል ከነበረው ሕዝባዊ አለመረጋጋት ጋር በተያያዘ ለብዙ ሺሕ ሰዎች ወህኒ መውረድ ምክንያት ሆኗል። ከታሳሪዎቹ መካከል ጋዜጠኞችና ጦማርያን ይገኙባቸዋል።

የኢትዮጵያው አስቸኳይ ጊዜ ዓዋጅ፣ ባለፈው ዓመት በኦሮሚያ ክልል ተጀምሮ በተለይም በሰሜኑ የአማራው ክልል ከነበረው ሕዝባዊ አለመረጋጋት ጋር በተያያዘ ለብዙ ሺሕ ሰዎች ወህኒ መውረድ ምክንያት ሆኗል። ከታሳሪዎቹ መካከል ጋዜጠኞችና ጦማርያን ይገኙባቸዋል።

ማርቲ ቫንዳር ወልፍ ከዛሬው የዓለም የፕሬስ ነፃነት ቀን ቀደም ብላ፣ ከሦስቱ የኢትዮጵያ ብሎገሮች ጋር ያደረገችውን ውይይት፣ ለቪኦኤ ልካለች፡፡

በዘገባውም የዩኒቨርሲቲ መምህርና ሃያሲ ሥዩም ተሾመ፣ ለጀርመኑ ራድዮ ጣቢያ ዶቼ ቬሌ በሰጡት ቃለ መጠይቅ ላይ የመንግሥቱን እንከን በመናገራቸው፣ በጥቅምት ወር ለሁለት ወራት እስር ቤት ቆይተዋል።

ከተፈቱ በኋላም፣ በሳምንት በተደጋጋሚ ጊዜያት በተለያዩ የፖለቲካ ዓምዶችና ማኅበራዊ ድረ ገፆች ላይ ፁሑፎችን አውጥተዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀኃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ

ዓለም አቀፍ የፕሬስ ነፃነትን ዕለት ምክንያት በማድረግ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀኃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ በማስመልከት ባስተላለፉት መልዕክት፣ ጋዜጠኞች እጅግ በጣም አደገኛ በሆኑ ቦታዎች እየተገኙ ድምፅ ለሌላቸው ድምፅ የሚሆኑ የሕዝብ ልሣን ናቸው - ብለዋል፡፡

ዓለም አቀፍ የፕሬስ ነፃነትን ዕለት ምክንያት በማድረግ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀኃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ በማስመልከት ባስተላለፉት መልዕክት፣ ጋዜጠኞች እጅግ በጣም አደገኛ በሆኑ ቦታዎች እየተገኙ ድምፅ ለሌላቸው ድምፅ የሚሆኑ የሕዝብ ልሣን ናቸው - ብለዋል፡፡

ጋዜጠኞች ሙያቸውን በሚከናውኑበት ወቀት፣ ለስም ማጥፋት፣ የወሲብ ጥቃት፣ ለእስራት፣ ለድብደባና ሁኔታው የከፋ ሲሆን ለሞትም የተጋለጡ መሆናቸውን ጠቅሰው ይሕ ጥቃት እንዲቆም ጥሪ አድርገዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

ሂለሪ ክሊንተን

ሂለሪ ክሊንተን ባለፈው ኅዳር ወር በተካሄደው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ከተሸነፉ ወዲህ ለመጀመርያ ጊዜ በተደረገላቸው ቃለ መጠይቅ ለመሸነፋቸው የራሳቸውም ኃላፊነት እንዳለበት ገልፀዋል።

ሂለሪ ክሊንተን ባለፈው ኅዳር ወር በተካሄደው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ከተሸነፉ ወዲህ ለመጀመርያ ጊዜ በተደረገላቸው ቃለ መጠይቅ ለመሸነፋቸው የራሳቸውም ኃላፊነት እንዳለበት ገልፀዋል።

ቃለ መጠይቁ ትላንት የተካሄደው ኒው ዮርክ ከተማ በተደረገው የሴቶች መድረክ ላይ ሲሆን ጋዜጠኛ ክሪስያን አላምፑር ናት ያነጋገረቻቸው።

የሩስያ ጣልቃ ገብነትና የፌደራል ምርመራ ሥራ አስኪያጅ ጀምስ ኮሚቴ መግለጫ ሪፐብሊካዊው ዶናልድ ትራምፕ እንዲያሸንፉ እንደረዱ ክሊንተን አስገንዝበዋል። የአሜሪካ ድምፅ ራድዮ ዘጋቢ ዝላቲካ ሆክ ያቀነባበርችውን ዘገባ አዳነች ፍሰሀየ ታቀርበዋለች።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG