በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

የኢትዮጵያን ፖለቲካና ምጣኔ ኃብት ሁኔታ የመቀየር ሃሣብ የዞ በ1983 ዓ.ም ወደ ሥልጣን የወጣው አማፂው ኢሕአዴግ መንግሥት ከሆነ በኋላ ባለፉ ሃያ ዓመታት ያሳየው ክፉ ወይም የጭቆና አካሄድ አካባቢያዊና የጎሣዎችን መከፋትን አስከትሏል ሲል - ካርኔጊ ኢንዶውመንት ፎር ኢንተርናሽናል ፒስ የሚባለው የዓለምአቀፍ ሰላም ቅኝት ተቋም ገልጿል፡፡

የኢትዮጵያን ፖለቲካና ምጣኔ ኃብት ሁኔታ የመቀየር ሃሣብ የዞ በ1983 ዓ.ም ወደ ሥልጣን የወጣው አማፂው ኢሕአዴግ መንግሥት ከሆነ በኋላ ባለፉ ሃያ ዓመታት ያሳየው ክፉ ወይም የጭቆና አካሄድ አካባቢያዊና የጎሣዎችን መከፋትን አስከትሏል ሲል - ካርኔጊ ኢንዶውመንት ፎር ኢንተርናሽናል ፒስ የሚባለው የዓለምአቀፍ ሰላም ቅኝት ተቋም ገልጿል፡፡

Carnegie Endowment for International Peace
Carnegie Endowment for International Peace

ተቋሙ ይህንን ያሳወቀው ዛሬ ይፋ ባደረገው ሰፊ ሪፖርቱ ላይ ነው፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ የኢትዮጵያ መንግሥት እሥር ላይ የሚገኙትን የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበሩን የዶ/ር መረራ ጉዲናን የዋስትና መብት እንዲያከብርና ክሦቹም ሁሉ እንዲሠረዙ፤ በኦሮሞ ማኅበረሰብና ሌሎችም ላይ ተፈፅመዋል ባላቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ግድያዎች ጉዳይ በግልፅና በነፃ አካል እንዲመረመር የአውሮፓ ፓርላማ ለኢትዮጵያ መንግሥት ጥሪ አስተላልፏል፡፡

በኢትዮጵያና በአውሮፓ ኅብረት መካከል ያለው ግንኙነት በተለያዩ ገፆች ጠንካራ መሆኑን የገለፁ አንድ የኢትዮጵያ መንግሥት ቃል አቀባይ የአሁኑን የአውሮፓ ፓርላማ ጥሪ የተለመደ ውንጀላና ከመደርደሪያ ላይ የማያልፍ ነው ብለውታል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

የዓለም የጤና ድርጅት ለመምራት የታጩ

የኢትዮጵያ የቀድሞ የውጭ ጉዳይና የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የዓለም የጤና ድርጅት ለመምራት ከታጩ ሦስት ተወዳዳሪዎች አንዱ ናቸው።

የኢትዮጵያ የቀድሞ የውጭ ጉዳይና የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የዓለም የጤና ድርጅት/WHO/ ለመምራት ከታጩ ሦስት ተወዳዳሪዎች አንዱ ናቸው። የዓለሙ ድርጅት አባል ሀገራት በሚቀጥለው ሳምንት ድምፅ እንደሚሰጡ ይጠበቃል። የዶ/ር ቴድሮስ አድሃምች ዕጩነት በኢትዮጵያዊያን ዘንድ መከፋፈልን ፈጥሯል።

በአንድ ወገን ዶ/ር ቴድሮስ በኢትዮጵያ የጤና ዘርፍ እንዲሁም የዓለም አቀፍ ድርጅቶችን በመምራትና በጋራ በመሥራት ዘርፈ ብዙ ለውጦችና መሻሻሎችን አስመዝግበዋል የሚሉ ሲደግፏቸው፤ በአንፃሩ ዶ/ር ቴድሮስ ያገለገሉት መንግሥት የዜጎቹን መብት የሚገፉ፣ ፍትሃዊ የጤና አገልግሎቶችን ለዜጎች ማዳረስ ያልቻለና፤ እንደ ኮሌራ ያሉ በሽታዎችን የተለየ ስም በመስጠት “አጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት” በሚል መድሃኒት እንዳይደርስ አድርጓል፤ ለዓለም ጤናም አሉታዊ የመሸፋፈን ሥራ ተሰርቷል በሚል፤ አጥብቀው በመቃወም ላይ ናቸው።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ፎቶ ፋይል

ለሶማልያ እየተሰጠ ያለው የሰብዓዊ ዕርዳታ ውጤት እያስመዘገበ መሆኑን የገለፁት አንድ የዓለማቀፍ ቀይ መስቀል ማኅበር ባለሥልጣን፣ የቀጣይ ዕርዳታ አስፈላጊነት ጉልህ እንደሆነም ተናገሩ።

ለሶማልያ እየተሰጠ ያለው የሰብዓዊ ዕርዳታ ውጤት እያስመዘገበ መሆኑን የገለፁት አንድ የዓለማቀፍ ቀይ መስቀል ማኅበር ባለሥልጣን፣ የቀጣይ ዕርዳታ አስፈላጊነት ጉልህ እንደሆነም ተናገሩ።

ሶማልያ ውስጥ የደረሰው ብርቱ ድርቅ የሀገሪቱን ግማሽ ያህል ወይም ስድሥት ሚሊዮን የሚሆነውን ሕዝብ ለአጣዳፊ ዕርዳታ ማጋለጡም ታውቋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

የፓርቲዎች ቅድመ ድርድር

በገዥው ኢህአዴግና በሀገር አቀፍ ፓርቲዎች መካከል ሊካሄድ የታቀደው ድርድር ከአንድ ወር ባነሰ ጊዜ ውስጥ እንደሚጀመር አጀንዳ ለማደራጅት የተቋቋመው ኮሚቴ አስታወቀ፡፡

በገዥው ኢህአዴግና በሀገር አቀፍ ፓርቲዎች መካከል ሊካሄድ የታቀደው ድርድር ከአንድ ወር ባነሰ ጊዜ ውስጥ እንደሚጀመር አጀንዳ ለማደራጅት የተቋቋመው ኮሚቴ አስታወቀ፡፡

የኮሚቴው አባላት እንዳሉት በታዛቢነት የሚሳተፉ አስራ ሁለት ዓለምቀፍና ሀገር አቀፍ ተቋማትም በፓርቲዎች ስምምነት ተመርጠዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

ናይጄሪያ የቦኮ ሃራሞችን ጭካኔ የተመላበት ዓመፅ እየተዋጋች ባለችበት በአሁኑ ወቅት የጦር ኃይሏ የዚያኑ ያህል አደገኛ የሆነ ጠላት ሙስና እያሰነካከለው ነው።

ናይጄሪያ የቦኮ ሃራሞችን ጭካኔ የተመላበት ዓመፅ እየተዋጋች ባለችበት በአሁኑ ወቅት የጦር ኃይሏ የዚያኑ ያህል አደገኛ የሆነ ጠላት ሙስና እያሰነካከለው ነው።

ፅህፈት ቤቱ ጀርመን የሆነው መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሺናል ባወጣው አዲስ ሪፖርት መሠረት የናይጄሪያ ወታደራዊ መኮንኖች ፖለቲከኞች እና ሌሎችም ከፍተኛ ቦታ ላይ ያሉ ሰዎች ሽብርተኝነትን ለመዋጋት የታለመ ገንዘብ እየወሰዱ ወደኪሳቸው ከትተው ከብረውበታል ብሏል።

ገንዘቡ በጉቦ በሌሉ ወታደሮች ስም በሚከፈል ደመወዝ መልክ እንደሚባክን ሪፖርቱ አውስቷል።

ከመንግሥት ጋር ትሥሥር ላላቸው የሥራ ተቆራጮች ኮንትራት ያለጨረታ እየተሰጠ፣ መጠነ ሰፊ ገንዘብ በሙስና ይወድማል ሲልም አስረድቷል።

በተጭበረበረ የጦር መሣሪያ ግዢ ውል የጠፋው ገንዘብ አሥራ አምስት ቢሊዮን ዶላር ይደርሳል ብለው እንደሚያምኑ የናይጄሪያ ምክትል ፕሬዚዳንት ገልፀዋል።

የናይጄሪያ የመከላከያ መረጃ ኃላፊ ሜጀር ጄነኢራል ጆን ኤንንች በበኩላቸው ሪፖርቱ አሳዛኝና ከዕውነት የራቀ ነው ብለዋል።

በዩጋንዳ ውስጥ ፖሊሶች በተጠርጣሪዎች ላይ ሰቆቃ ፈፅመዋል በመባሉ ከፍተኛ ችግር ውስጥ መግባታቸው ተገለፀ።

በዩጋንዳ ውስጥ ፖሊሶች በተጠርጣሪዎች ላይ ሰቆቃ ፈፅመዋል በመባሉ ከፍተኛ ችግር ውስጥ መግባታቸው ተገለፀ።

ፕሬዚዳንቱና የአገር ውስጥ ሚኒስቴር ግን ጉዳዩ እልባት እንዲያገኝ በዚህ ሳምንት ውስጥ በይፋ መጠየቃቸው ታውቋል።

እአአ ባለፈው መጋቢት 17 ቀን የዩጋንዳ ፖሊስ ረዳት ተቆጣጣሪ ካማፓላ ውስጥ ይገደላሉ፣ ፖሊሶች ደግሞ ከአምስት ቀናት በኋላ 17 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር እንዳዋሉ አስታወቁ።

ሰዎቹ ከወር በኋላ ፍርድ ቤት ቢቀርቡም፣ ሂደቱ ለጋዜጠኞች ክፍት አልነበረም። ይሁንና ተጠርጣሪዎች ሰውነታቸው ላይ ሰቆቃና ወከባ እንደተፈፀመባቸው የሚያሳዩ ፎቶግራፎች ሾልከው ወጡ።

ባለፈው አስራ ቀን፣ እአአ ግንቦት 5 ቀን፣ ለ2ኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ሲቀርቡ፣ “ተገርፈናል፣ ተደብድበናል” ብለው ያመለክታሉ።

“እጅና እግራችን ታስሮ እንዳለ ተደብድበናል” በማለት፣ የቆሰሉ የሰውነት ክፍሎቻቸውንም አሳይተዋል።

ሁኔታው በብሔራዊ ቴሌቪዥን ተላለፈና ከፍተኛ ሕዝባዊ ቁጣ ቀሰቀሰ።

የዩጋንዳ ፖሊስ ቃል አቀባይ አሳን ካሲንጌይ እንደተናገሩት፣ ሁለት ፖሊሶች ታስረዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

የተባበሩት መንግሥታት የዓለም የጤና ድርጅት በዛሬው ዕለት እንዳስታወቀው የመን ውስጥ እስካሁን በኮሌራ ወረርሺኝ ከተጠቁት ሃምሳ ሺሕ ሰዎች በተጨማሪ በቀጣዮቹ ስድሥት ወራት ውስጥ ሁለት መቶ ሽሕ ሰው በበሽታው ይያዛል።

የተባበሩት መንግሥታት የዓለም የጤና ድርጅት በዛሬው ዕለት እንዳስታወቀው የመን ውስጥ እስካሁን በኮሌራ ወረርሺኝ ከተጠቁት ሃምሳ ሺሕ ሰዎች በተጨማሪ በቀጣዮቹ ስድሥት ወራት ውስጥ ሁለት መቶ ሽሕ ሰው በበሽታው ይያዛል።

የዓለም የጤና ድርጅት የየመን ተወካይ ኔቪዮ ዛጋሪያ የአሁኑ የኮሌራ ወረርሽኙ እያተዛመተ ያለበት ፍጥነት ከአሁን ቀደም ታይቶ የማያውቅ ነው ብለዋል።

እስካሁን የሞቱት ሰዎች ቁጥር ሁለት መቶ አርባ ደርሷል። ባለፉት ሦስት ሳምንታት ውስጥ ከሃምሳ ሺሕ በላይ በበሽታው ተይዘዋል።

በሁቲ አማፅያን እና በሳውዲ በሚመሩ የአረብ ሀገሮች ወታደራዊ ሕብረት የሚታገዙት የመንግሥት ሃይሎች ውጊያ ሁለት ዓመት ያስቆጠረ ሲሆን ከሥምንት ሺሕ በላይ ህዝብ አልቆበታል።

የመን በኮሌራ ወረርሺኝ ምክንያት ትናንት በዋና ከተማዋ ሰንዓ አስቸኳይ ጊዜ አውጇል።

ፎቶ ፋይል፡- ደቡብ ሱዳን

የደቡብ ሱዳን መንግሥት ደጋፊ ኃይሎች ዬዪ ከተማ ውስጥ እአአ 2016 እስከ ጥር 2017 በነበረው ጊዜው ውስጥ ቢያንስ አንድ መቶ አሥራ አራት ሲቪሎችን መግደላቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ያወጣው አዲስ ሪፖርት ገለጠ፡፡

የደቡብ ሱዳን መንግሥት ደጋፊ ኃይሎች ዬዪ ከተማ ውስጥ እአአ 2016 እስከ ጥር 2017 በነበረው ጊዜው ውስጥ ቢያንስ አንድ መቶ አሥራ አራት ሲቪሎችን መግደላቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ያወጣው አዲስ ሪፖርት ገለጠ፡፡ የተባበሩት መንግሥታት የደቡብ ሱዳን ተልዕኮ /UNMISS/ እና የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ቢሮ ዛሬ ባወጡት ሪፖርት ላይ የመንግሥት ወገንተኞቹ ሐይሎች በሲቪሎች ላይ መድፍ መተኮሳቸው ዒላማ አድርገው የገደሏቸው ሰዎች መኖራቸውንና ንበረቶች መዝረፋቸውንና መንደሮች ማቃጠላቸውን ዘርዝረዋል።

ሴቶችና ልጃገረዶችን፣ ከግጭት እየሸሹ የነበሩትንም ጭምር ደፍረዋል ብለዋል።

የተፈፀሙት ወንጀሎች በጦርነት ወንጀል፣ በሰብዕና ላይ በተፈፀመ ወንጀል ሊያስጠይቅ እንደሚችል ሪፖርቱ አክሎ አስገንዝቧል።

አፍሪካ በጋዜጦች

  • አዳነች ፍሰሀየ
ዶክተር ቴዎድሮስ አድሀኖም

አፍሪካ በጋዜጦች የተሰኘው ፕሮግራማችን፣ ስለ አፍሪካ ከተፃፉት፣ የተወሰኑትን ጨምቆ ያቀርባል።

አፍሪካ በጋዜጦች የተሰኘው ፕሮግራማችን፣ ስለ አፍሪካ ከተፃፉት፣ የተወሰኑትን ጨምቆ ያቀርባል።

ዶክተር ቴዎድሮስ አድሀኖም ለዓለምቀፍ የጤና ድርጅት መሪነት ጠንካራ ተውዳዳሪ መሆነቸው ተገለፀ፣ የኢትዮጵይ የቡና ምርት እጥፍ ገቢ ለማግኘት በሚችለብት መንገድ እየተሻሻለ መሆኑ ተገለፀ፤ የሚሉትን ርዕሶች ነው ተካተዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የጎረቤት አገሮች ጉዳይ ኃላፊ አቶ መለስ አለም

ከፊል ራስ ገዧ ሶማሌላንድ እንደ ሀገር እውቅና ለማግኘት በመጣር ላይ ትገኛለች፡፡

ከፊል ራስ ገዧ ሶማሌላንድ እንደ ሀገር እውቅና ለማግኘት በመጣር ላይ ትገኛለች፡፡ ኢትዮጵያ ለሶማሌላንድ እውቅና ለመስጠት “የመጀመሪያዋ ሀገር አልሆንም” የሚል አቋም እንዳላት የመንግሥቱ ባለሥልጣናት ይናገራሉ፡፡

ግዙፍ የህዝብ ቁጥር ያላትና የባህር በር አልባ የሆነችው ኢትዮጵያ የተለያዩ የወደብ አገልግሎቶችን የምትሻ ስትሆን፣ በርበራ ወደብን ለማልማት ከሶማሌላንድና መሠረቱን በተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች ካደረገ ድርጅት ጋር ሥራ ልትጀምር እየተንቀሳቀሰች ነው፡፡

ኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ በፖለቲካ እውቅና እና የወደብ አማራጭን በመጠቀም በሚገኙ በመሳሰሉ ጥቅሞች ባላቸው ግንኙነት ምን ይመስላል?

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ አለምን አነጋግረናቸዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

XS
SM
MD
LG