በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ እና ሬሴፕ ታይፕ ኤርዶዋን

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ እና ሬሴፕ ታይፕ ኤርዶዋን ትናንት ዋይት ሃውስ ቤተመንግሥት ውስጥ ያደረጉት ስብሰባ "በሁለቱ ሃገሮች መካከል ለሚኖሩት ግንኙነቶች የአዲስ ዘመን መጀመሪያ ነው" ሲሉ ገልፀውታል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ እና ሬሴፕ ታይፕ ኤርዶዋን ትናንት ዋይት ሃውስ ቤተመንግሥት ውስጥ ያደረጉት ስብሰባ "በሁለቱ ሃገሮች መካከል ለሚኖሩት ግንኙነቶች የአዲስ ዘመን መጀመሪያ ነው" ሲሉ ገልፀውታል፡፡

ኤርዶዋን ወደ ዋሺንግተን የተጓዙት ዩናይትድ ስቴትስ የእሥላማዊ መንግሥት ቡድን ጠንካራ ይዞታ የሆነችውን የሶሪያዪቱን ራቃ ከተማ ለመቆጣጠር እየገሰገሱ ያሉትን የኩርድ ተዋጊዎች እንደምታስታጥቅ ይፋ ካደረገች ከሁለት ሣምንታት በኋላ ነው፡፡

የሶሪያ ኩርዶች ሽብርተኞች ናቸው ከምትላቸው የራሷ ኩርዶች ድርጅት ጋር ግንኙነት አላቸው የምትለው ቱርክ ሶሪያዊያኑን የማስታጠቁን ሃሣብ በብርቱ ትቃወማለች፡፡

ሌሎች የሁለቱ ሃገሮች ግንኙነት ጉዳዮች በዩኤስ-ቱርክ ጉባዔ ላይ ተመክሮባቸዋል፡፡

ዝላቲሳ ሆክ ዝርዝር አላት፤ ትዝታ በላቸው ታቀርበዋለች፡፡

ፎቶ ፋይል፡- የሱዳን ፕሬዚዳንት ሃሰን ኦማር አል በሺር

የሱዳን ፕሬዚዳንት ሃሰን ኦማር አል በሺር በያዝነው ሣምንት መጨረሻ ላይ ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ በሚካሄደው የመሪዎች ስብሰባ ላይ እንዲገኙ መጋበዛቸው የመብቶች ተሟጋቾችና ተንታኞችን እያነጋገረ ነው፡፡

የሱዳን ፕሬዚዳንት ሃሰን ኦማር አል በሺር በያዝነው ሣምንት መጨረሻ ላይ ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ በሚካሄደው የመሪዎች ስብሰባ ላይ እንዲገኙ መጋበዛቸው የመብቶች ተሟጋቾችና ተንታኞችን እያነጋገረ ነው፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ በዚያ ስብሰባ ላይ እንደሚገኙ ይጠበቃል፡፡

የሱዳኑ ፕሬዚዳንት በዓለምአቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት በጦር ወንጀሎች ተከስሰው የሚፈለጉ በመሆናቸው መጋበዛቸው ንግግርና ውዝግብ ፈጥሯል፤ ተቃውሞም ገጥሞታል፡፡

ጂል ክሬግ ከናይሮቢ የላከችውን ዘገባ ትዝታ በላቸው ታቀርበዋለች፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት

የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት /መኢአድ/ እና ሰማያዊ ፓርቲ በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የሚገኙ አባሎቻቸውን ለመጎብኘት እንደተከለከሉ ተናገሩ፡፡

የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት /መኢአድ/ እና ሰማያዊ ፓርቲ በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የሚገኙ አባሎቻቸውን ለመጎብኘት እንደተከለከሉ ተናገሩ፡፡

የታራሚዎችን ሕገ መንግሥታዊ መብት የጣሰ ነው ያሉትን ይኼን ዕርምጃ እንዲታረም ለፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር አቤቱታ ማቅረባቸውን አስታውቀዋል፡፡

ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ ለማግኘት ያደገግነው ጥረት አልተሳካም፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ፎቶ ፋይል

የተባበሩት መንግሥታት የሕፃናት መርጃ ድርጅት ዩኒሴፍ ከትናንት በስቲያ ባወጣው አዲስ ሪፖርት በመካከለኛው ምሥራቅና በሰሜን አፍሪካ ሀገሮች ከአራት ልጆች አንዱ እንደ ንፁህ ውሃና ተገቢ መጠለያ የመሳሰሉ እጅግ መሠረታዊ የሆኑ አቅርቦቶችን አጥተው በድኅነት እንደሚኖሩ አመለከተ።

የተባበሩት መንግሥታት የሕፃናት መርጃ ድርጅት ዩኒሴፍ ከትናንት በስቲያ ባወጣው አዲስ ሪፖርት በመካከለኛው ምሥራቅና በሰሜን አፍሪካ ሀገሮች ከአራት ልጆች አንዱ እንደ ንፁህ ውሃና ተገቢ መጠለያ የመሳሰሉ እጅግ መሠረታዊ የሆኑ አቅርቦቶችን አጥተው በድኅነት እንደሚኖሩ አመለከተ።

አሥራ አንድ የአረብ ሃገሮችና አካቶ የተካሄደው ጥናት ሃያ ዘጠኝ ሚሊዮን ሕፃናት ሁለት ወይም ከሁለት በላይ በቂ የተመጣጠነ ምግብ፣ መሠረታዊ ትምህርት፣ የንፅህናና የመረጃ አቅርቦት የመሣሳሉ ለሕይወት እጅግ መሠረታዊ ፍላጎቶች በማያገኙበት የድኅነት አረንቋ ይኖራሉ ብሉዋል።

የወጣቶች ደኅነት ዓይነተኛ ምክንያት የትምህርት ዕጥረት መሆኑን ስለአካባቢዎቹ የልጆች ደኅነት የተጠናቀረ የመጀመሪያ የሆነው ይህ መረጃ አመልክቷል።

የትምህርት ዕድል ባላገኙ የቤተሰብ አባላት የሚመሩ ቤተሰቦች ውስጥ የሚኖሩ ልጆች በድኅነት የመኖር ዕድላቸው ዕጥፍ መሆኑን ያመለክታል። በዚህ ዓይነት ከሚኖሩ ዕድሜአቸው ከአምስት እስከ አስራ ሰባት ዓመት ከሆኑ ልጆች ውስጥ አንድ አራተኛው ትምህርት ቤት ያልገቡ ወይም ከዕኩዮቻቸው በሁለት ክፍል ወደኋላ የቀሩ ናቸው ብለዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ የመካከለኛ ምሥራቅ እና የሰሜን አፍሪካ አካባቢ ድሬክተር ገርት ካፔሌሬ ሲናገሩ የልጆች ድኅነት አመዛኙ ምክንያት የቤተሰብ ገቢ ማነስ ሳይሆን ጥራት ያለው ትምህርት የጤና ጥበቃ መኖሪያና ንፁህ ውሃ ዕጦቱ ነው ብለዋል።

ፎቶ ፋይል

ሰሜናዊዋ የዩናይትድ ስቴትስ ክፍለ ግዛት ሚኔሶታ ያሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ አፍሪካዋያን የተሰጣቸውን የኢሚግሬሽን ጊዜያዊ ፈቃድ ሊያጡ ነው።

ሰሜናዊዋ የዩናይትድ ስቴትስ ክፍለ ግዛት ሚኔሶታ ያሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ አፍሪካዋያን የተሰጣቸውን የኢሚግሬሽን ጊዜያዊ ፈቃድ ሊያጡ ነው።

እኤአ በ2014 ዓ.ም ከሦስት ዓመታት በፊት፣ ሶስት የምዕራብ አፍሪካ ሃገሮች በኢቦላ በሽታ ወረርሺኝ ተጠቁ፣ በኋላ ከእነዚህ ሃገሮች የሆኑ ቁጥራቸው ወደ አምስት ሺሕ የሚደርስ አሜሪካ ነዋሪዎች ወረርሺኙ በቁጥጥር ሥር እስከሚውል ድረስ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ መኖር እና መሥራት እንዲችሉ ልዩ ፈቃድ ተሰጥቷቸው ነበር።

ባለፈው ዓመት ሦስቱም ሃገሮች ከኢቦላ ነፃ ተብለዋል። ስለዚህም የሚኔሶታ ራዲዮ እንደዘገበው ጊዜያዊ የመቆያ ፈቃድ የተሰጣቸው ሰዎች ወደሃገራቸው መመለስ ወይም ሕጋዊ መኖሪያ ማግኘት ይኖርባቸዋል።

በሚኔሶታ ብሩክሊን ፓርክ የአፍሪካውያን ኢሚግሬሽን አገልግሎቶች ዋና ሥራ አስኪያጅ አብዱላ ኪያታምባ እና ሌሎችም የኢሚግሬሽን ተሟጋቾች ባሁኑ ወቅት የጊዜያዊ የመኖሪያ ፈቃዱ መሰረዝ ትክክል እንዳልሆነ ይናገራሉ።

ለዚህም የሚሰጡት ምክንያት ጊኒ ሲየራሊዮን እና ላይቤሪያ እንዲሁም ከወረርሺኙ ገና በማገገም ላይ በመሆናቸው ሰዎቹ ቢመለሱ አደጋ ላይ ሊወድቁ ይችላሉ በሚል ነው።

ሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ የደረሰው ፍንዳታ

ሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ ውስጥ ዛሬ ረቡዕ መኪና ላይ የተጠመደ ቦምብ ፈንድቶ አምስት የፀጥታ ጥበቃ አባላት እና አንድ የተቀባረ ፈንጂዎች ኤክስፕርት ገደለ።

ሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ ውስጥ ዛሬ ረቡዕ መኪና ላይ የተጠመደ ቦምብ ፈንድቶ አምስት የፀጥታ ጥበቃ አባላት እና አንድ የተቀባረ ፈንጂዎች ኤክስፕርት ገደለ።

የሶማሊያ ፖሊስ ቃል አቀባይ ማሐመድ ዩሱፍ ኦማር ማዳሌ ሲናገሩ ቦምብ የተጠመደባት መኪና ሞቃዲሾ ዋዳጂር ቀበሌ ፖሊስ ጣቢያ አጠገብ ቆማ እንደነበረ እና የፀጥታ ኃይሎች ተጠራጥረው የመኪናዋን አሽከርካሪ አስረው ፈንጂውን ለማምከን ሲሞክሩ እንደፈንዳባቸው ገልፀዋል።

ለጥቃቱ እስካሁን ኃላፊነት የወሰደ ወገን የለም። ይሁን እንጂ እንዲህ ያሉ ሽብርተኛ ጥቃቶችን በማድረስ ብዙውን ጊዜ የሚጠረጠረው ፅንፈኛው ቡድን አልሸባብ ነው።

ፎቶ ፋይል

መካከለኛ አፍሪካ ሪፐብሊክ ውስጥ ውጊያው ማገርሸቱ ከባድ ማስጠንቀቂያ ደወል የሚያሻው ነው ሲሉ የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽነር አሳሰቡ።

መካከለኛ አፍሪካ ሪፐብሊክ ውስጥ ውጊያው ማገርሸቱ ከባድ ማስጠንቀቂያ ደወል የሚያሻው ነው ሲሉ የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽነር አሳሰቡ።

ባልፈው ሳምንት በሀገሪቱ በሙስሊሞችና ክርስቲያኖች መካከል በተቀሰቀሰ ውጊያ ከመቶ የሚበልጡ ሰዎች ሲሞቱ በሺዎች የተቆጠሩ ከቀያቸው ተሰደዋል።

ትናንት የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽነር ዜይድ ራአድ አል ሁሴን በሰጡት መግለጫ አንዳንዶቹ የሀገሪቱ የገጠር አካባቢዎች ወደተባባሰ ብጥብጥ እያሽቆለቆሉ መሄዳቸው በዋና ከተማዋ ባንጊ እና በሌሎችም ትላልቆቹ ከተሞች በመከራ የተገኘውን አንፃራዊ መረጋጋት አደጋ ላይ ይጥላል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

በእስር ላይ የሚገኘው የቀድሞው የሰማያዊው ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ላይ ሽብርተኝነትን በማበረታታት በሚል በቀረበበት ክስ የተላለፈው የጥፋተኝነት ውሳኔ ሐሳብን የመግለፅና እና በፌስቡክ ፁሑፎችን የማውጣት መብት የሚፃረር “አሳፋሪ” ውሳኔ ነው ሲል ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ገለፀ።

በእስር ላይ የሚገኘው የቀድሞው የሰማያዊው ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ላይ ሽብርተኝነትን በማበረታታት በሚል በቀረበበት ክስ የተላለፈው የጥፋተኝነት ውሳኔ ሐሳብን የመግለፅ እና በፌስቡክ ፁሑፎችን የማውጣት መብት የሚፃረር “አሳፋሪ”ውሳኔ ነው ሲል ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ገለፀ።

የአምነስቲ የአፍሪካ ቀንድ ተመራማሪ አቶ ፍሰሃ ተክሌ “ይህ የሚያሳየው መንግሥትን የሚቃወሙ ወይም ከመንግሥት የተለየ ሐሳብ የሚያራምዱ ሰዎች በኢትዮጵያ ተቀባይነት እንደሌላቸውና ሕጉንም በመጠቀም ወንጀለኛ እንደሚባሉ የሚያሳይ ነው”ብለውታል።

እንዲህ ያለ ውሳኔ አዲስ አለመሆኑን የተናገሩት ተመራማሪው “ነገር ግን ዮናታን የጥፋተኝነት ውሳኔው የተላለፈበት ፌስቡክ ላይ በሚያወጣቸው አቋሞቹ ምክንያት በመሆኑ መንግሥት በእንደዚህ ዓይነት ተቃውሞዎችና ሂሶች ያለውን አቋም የሚያሳይ ጉዳይ ነው” ብለዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

XS
SM
MD
LG