በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

ሳምንታዊ ስፖርት

  • ሰሎሞን ክፍሌ
አትሌት ለተሰንበት ግደይ

በኦክፔክፔ ናይጀሪያው የጎዳና ሩጫ ኢትዮጵዮውያኑ ልዕል ገ/ሥላሴና አዝመራ ገብሩ ድል ተደዳጅተዋል፡፡

በኦክፔክፔ ናይጀሪያው የጎዳና ሩጫ ኢትዮጵዮውያኑ ልዕል ገ/ሥላሴና አዝመራ ገብሩ ድል ተደዳጅተዋል፡፡

በቀለች ዳባ ደግሞ በሪጋ ላትቪያው ማራቶን የሥፍራውን ርኮርድ ሠበራለች፡፡ በስዊዘርላንድ ማራቶን ኤርትራዊው ግርማይ ገ/ሥላሴ አሸንፋል፡፡

በሳምንቱ ማብቂያ በኢትዮጵያ እና አውሮፓ የተካሄዱ የፕሪምየር ሊግ እግር ኳስ ግጥሚያ ወጤቶችንም ይዘናል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

አፍሪካ ነክ ርዕሶች

  • አዳነች ፍሰሀየ

ከባድ የሙስና ተግባር በሚፈፀምባቸው ሀገሮች ውስጥ የንግድን ሥነ ምግባር የሚከተሉ ድርጅቶች ቁጥር ሊበዛ አንደሚችል አንድ አዲስ ጥናት ሰሞኑን ቢያመለክትም የሕዝቡንና የመዋዕለ ንዋይ ድጋፍ ለማግኘት ግን ጊዜ እንደሚጠይቅ ተገለፀ፡፡

ከባድ የሙስና ተግባር በሚፈፀምባቸው ሀገሮች ውስጥ የንግድን ሥነ ምግባር የሚከተሉ ድርጅቶች ቁጥር ሊበዛ አንደሚችል አንድ አዲስ ጥናት ሰሞኑን ቢያመለክትም የሕዝቡንና የመዋዕለ ንዋይ ድጋፍ ለማግኘት ግን ጊዜ እንደሚጠይቅ ተገለፀ፡፡

በሕንድ በግብፅና በዚምባዌ ላይ ያተኮረው ጥናት የሥነ ምግባር ጉድለትን የሚያሰወግዱ ኩባንያዎች የሕዝብና የመዋዕለ ንዋይ አፍሳሾች ድጋፍ እንደሚያገኙ አንድ አዲስ ጥናት ሊገነዘብ ችሏል፡፡

በኤክሰን ዩኒቨርስቲ የአስተዳደር ጥናት ተባባሪ ፕሮፌሰር ዊሊያም ሃርቢ ከቻይናውያንና ከአሜሪካዊያን ባልደረቦቻቸው ጋር ሆነው በጥናቱ ሥራ ተሳትፈዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የብሔራዊ የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሮክተሬት ዳይሬክተር አቶ ደበበ ዘውዴ

የብሔራዊ አደጋ ሥጋት አመራር ኮሚሽን በኢትዮጵያ የተከሰተውን ድርቅ ወደ ረሃብ ሳይቀየር መቋቋም መቻሉን እየገለፀ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ በሦስት ወራት ጊዜ ውስጥ ፤ “ከ5.6 ሕዝብ ወደ 7.8 ሚሊዮን ሕዝብ በላይ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ይፈልጋል ለዚህም 742 ሚሊዮን ዶላር ከለጋሾች ይጠበቃል።” ይላል።

የብሔራዊ የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሮክተሬት ዳይሬክተር አቶ ደበበ ዘውዴ ፤ ድርቁ በጣም እያጠቃ ያለው የቆላማ አርብቶ አደር አካባቢዎችን እንደሆነ ይናገራሉ። “ረሃብ ያልተከሰተው ምግብ ለሚፈልገው ሕዝብ መመገብ ስለቻልን ነውም” ይላሉ።

ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር በትብብር የሚሰሩ ለጋሾች በበኩላቸው የተጎጂዎች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል እና ገንዘቡ ካልተገኘ አደጋው ከፍተኛ ሊሆን እንደሚችል እየወተወቱ ይገኛሉ።

ጽዮን ግርማ አቶ ደበበን አነጋግራለች።

ፎቶ ፋይል

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ለደቡብ ሱዳን ስደተኞች ምግብ፣ ውኃና የጤና አገልግሎት ለማድረስ ያቀረበውን የዕርዳታ ጥያቄ ከ1 ቢልዮን ሁለት መቶ ሚሊየን ዶላር ወደ አንድ ቢልዮን 400 ሚሊየን ዶላር ከፍ አደረገ፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ለደቡብ ሱዳን ስደተኞች ምግብ፣ ውኃና የጤና አገልግሎት ለማድረስ ያቀረበውን የዕርዳታ ጥያቄ ከ1 ቢልዮን ሁለት መቶ ሚሊየን ዶላር ወደ አንድ ቢልዮን 400 ሚሊየን ዶላር ከፍ አደረገ፡፡

እጅግ የመረረ ግጭትና እየተባላሸ የመጣው የሰዉ ሕይወት ሁኔታ ደቡብ ሱዳናዊያንን ታይቶ በማይታወቅ ቁጥር ለመፈናቀልና ለስደት እየዳረገ መሆኑን የመንግሥታቱ ድርጅት የስደተኞች ጉዳዮች ከፍተኛ ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲ አስታውቀዋል፡፡

በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረ በመምጣቱ መጠን ከዓለም አቻ እንደሌለው በተነገረው መፈናቀልና ፍልሰት የደቡብ ሱዳን ስደተኞች ቁጥር ከ 1 ሚልዮን ስምንት መቶ ሺህ በላይ መሆኑንና ከመካከላቸውም አንድ ሚሊየን የሚሆኑት ሕፃናት መሆናቸውን ከፍተኛ ኮሚሽነሩ ተቋም ዛሬ ባወጣው መግለጫ አመልክቷል፡፡

ደቡብ ሱዳናዊያኑ እየተሰደዱ ያሉት ወደ ሁሉም ጎረቤት ሃገሮች፤ ማለትም ወደ ዩጋንዳ፣ ሱዳን፣ ኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ኮንጎና ሴንትር አፍሪክ መሆኑን ኮሚሽነሩ አስታውቋል፡፡

በሃገር ውስጥም በርስ በርሱ ቁርቁስ ምክንያት 1 ነጥብ ስምንት ሚሊየን ደቡብ ሱዳናዊያን እየተፈናቀሉ ቀዬዎቻቸውን እየጣሉ መሸሻቸውን የኮሚሽነሩ መግለጫ ገልጿል፡፡

አሁን ያለውን የደቡብ ሱዳን ሁኔታ «ሊታሰብ የማይችል» እና «ገደል አፋፍ ላይ ያለ» ሲሉ የዓለም የምግብ መርኃግብር ኃላፊ ዴቪድ ቢስሌ ገልፀውታል፡፡

የዓለምአቀፍ ድጋፍ ጥያቄው እንደቀጠለ ቢሆንም ሃገሪቱ ውስጥ እርዳታ ለማድረስ እየተረባረቡ ያሉት የሕፃናቱ መርጃ - ዩኒሴፍ፣ የስደተኞች ጉዳዮች ተቋሙ ዩኤንኤችሲአር እና ምግብ አቅራቢው ዳብልዩ ኤፍ ፒ የሚፈለገው ገንዘብ በሚገባው መጠን አለመገኘቱን እያስታወቁ ናቸው፡፡

ፎቶ ፋይል

ወደ አውሮፓ የሚጎርፈውን የአፍሪካ ስደተኛ ለማቆም በኒዠርና በሊብያ ድንበር ላይ የሚቆም ኃይል እንዲሠማራ የጀርመንና የጣልያን የሃገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስትሮች ለአውሮፓ ኅብረት ጥሪ አስገቡ፡፡

ወደ አውሮፓ የሚጎርፈውን የአፍሪካ ስደተኛ ለማቆም በኒዠርና በሊብያ ድንበር ላይ የሚቆም ኃይል እንዲሠማራ የጀርመንና የጣልያን የሃገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስትሮች ለአውሮፓ ኅብረት ጥሪ አስገቡ፡፡

ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

ሚኒስትሮቹ ለአውሮፓ ኮሚሽን ባስገቡት ደብዳቤ ፍልሰቱን ለመቆጣጠር እስከአሁን የተደረገው ዓለምአቀፍ ጥረት «በቂ አይደለም» ብለዋል፡፡

ይህ የአውሮፓ ዓመት ከባተ ወዲህ ባለፈው የአራት ወራት ተኩል ጊዜ ውስጥ ብቻ ከ43 ሺህ በላይ ፍልሰተኛ በአመዛኙ ከሰሃራ በስተደቡብ ካሉ ሃገሮች እየጎረፈ በሊብያ አድርጎ ወደ አውሮፓ መዝለቁን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታውቆ ቁጥሩ በመጭዎቹ የመፀው እና የበጋ ወራት በእጅጉ ሊያሻቅብ እንደሚችል ተንብይዋል፡፡

የአፍሪካ ፍልሰተኞች ሜዲቴራንያን ባህርን ለማቋረጥ በሚያደርጉት ጥረት እስከአሁን ወደ 1 ሺህ ሁለት መቶ ሰው መሞቱም ተገልጿል፡፡

የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ አራት ከፍተኛ የአመራር አባላትን ጨምሮ በሃያ ሁለት ተከሳሾችና በዐቃቤ ህግ መካከል ባለው ክርክር ላይ ዛሬ ሊሰጥ የነበረው ብይን እንዳልደረሰለት የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አራተኛ ወንጀል ችሎት አስታወቀ፡፡ ችሎቱ ተለዋጭ ቀጠሮም ሰጥቷል።

የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ አራት ከፍተኛ የአመራር አባላትን ጨምሮ በሃያ ሁለት ተከሳሾችና በዐቃቤ ህግ መካከል ባለው ክርክር ላይ ዛሬ ሊሰጥ የነበረው ብይን እንዳልደረሰለት የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አራተኛ ወንጀል ችሎት አስታወቀ፡፡ ችሎቱ ተለዋጭ ቀጠሮም ሰጥቷል።

ቀደም ሲል ከተመሠረተባቸው የሽብር ክሥ በነፃ ተሰናብተው የነበሩት የቀድሞ የአንድነት ፓርቲ አመራር አባል አቶ ዳንኤል ሺበሺና የአረና ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ አብረሃ ደስታ እንዲቀርቡ አራተኛ ወንጀል ችሎት አዝዟል፡፡

የችሎቱ ትዕዛዝ የወጣው በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ መሠረት እንደሆነ ታውቋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ምሥራቅ አፍሪካ ላይ በደረሰው ድርቅ ምክንያት የአስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታ የሚያስፈልጋቸው ኢትዮጵያዊያን ትክክለኛ ቁጥር የሚታወቀው ሰሞኑን ከሚጀመረው ግምገማ በኋላ መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ዕርዳታ ማስተባበሪያ ቢሮ አስታወቀ፡፡

ምሥራቅ አፍሪካ ላይ በደረሰው ድርቅ ምክንያት የአስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታ የሚያስፈልጋቸው ኢትዮጵያዊያን ትክክለኛ ቁጥር የሚታወቀው ሰሞኑን ከሚጀመረው ግምገማ በኋላ መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ዕርዳታ ማስተባበሪያ ቢሮ አስታወቀ፡፡

UNOCHA Logo
UNOCHA Logo

በያዝነው የአውሮፓ 2017 ዓመት መጀመሪያ ላይ የወጣው የሰብዓዊ ድጋፍ መጠየቂያ ሰነድ በዚህ ግምገማ መሠረት እንደሚከለስ የቢሮው ቃል አቀባይ ቾይዝ ኦኮሮ ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል፡፡

በኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ ዕርዳታ የሚያስፈልጋቸው ዜጎች ቁጥር 2.2 ሚሊዮን መጨመሩ ይፋ የተደረገው ሰሞኑን ነው፡፡ በዚህም መሠረት 5.6 ሚሊዮን የነበረው ቁጥር 7.8 ሚሊዮን ደርሷል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ፕሬዚዳንታዊ ሥልጣናቸውን ትናንት የተረከቡት ኢማኑኤል ማክሮን ቀኝ ዘመሙን ኤድዋር ፊሊፕን የፈረንሣይ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርገው ሾሙ፡፡

ፕሬዚዳንታዊ ሥልጣናቸውን ትናንት የተረከቡት ኢማኑኤል ማክሮን ቀኝ ዘመሙን ኤድዋር ፊሊፕን የፈረንሣይ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርገው ሾሙ፡፡

46 ዓመት ዕድሜአቸው ላይ የሚገኙት ፊሊፕ ሎ አርቭ የምትባለው ወደብ ከተማ ከንቲባና እንደራሴም ሆነው ያገለገሉ ሲሉ የሪፐብሊካን ፓርቲው ለዘብተኛ የሚባለው ክንፍ ወገን የሆኑ ፖለቲከኛ ናቸው፡፡

በ39 ዓመት ዕድሜአቸው የፈረንሣይ ፕሬዚዳንት የሆኑት ኢማኑኤል ማክሮን መንበረ-ሥልጣኑን በይፋ የተረከቡት ትናንት ዋና ከተማዪቱ ፓሪስ ላይ በተካሄደ ደማቅ የተባለ ሥነ-ሥርዓት ነበር፡፡

ፕሬዚዳንት ማክሮን በቃለ-መኃላ ንግግራቸው ላይ በአውሮፓና በዓለምም የፈረንሣይን ቦታ መልሰው እንደሚያስከብሩ፤ ሃገራቸው ከሽብር ፈጠራ ጋር የያዘችውን ፍልሚያም እንደሚቀጥሉ ቃል ገብተዋል፡፡

ማክሮን ባለፈው ሣምንት በተካሄደው የፕሬዚዳንታዊ ምርጫው ሁለተኛ ዙር ድምፅ ያሸነፉት ፀረ-አውሮፓ ኅብረትና ፍልሰተኛ ጠል የሆኑትን ቀኝ አክራሪ ዕጩ ማሪን ሎ ፔን አሸንፈው ነው፡፡

ፎቶ ፋይል

በማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ባንጋሱ ከተማ ሰላሣ ሲቪሎችና ስድስት ሰላም አስከባሪ ወታደሮች በአማፂያን ተገደሉ፡፡

በማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ባንጋሱ ከተማ ሰላሣ ሲቪሎችና ስድስት ሰላም አስከባሪ ወታደሮች በአማፂያን ተገደሉ፡፡

ከማዕከል ርቃ በምትገኘው ከተማ ውስጥ አማፂያኑ እያካሄዱ ባሉት ዘመቻ ሙስሊሞች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት እየፈፀሙ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ባንጋሱ ውስጥ በተከፈተባቸው ጥቃት ምክንያት እየተፈናቀሉ ያሉት ሲቪሎች በአንድ መስጂድ፣ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን እና በድንበር የለሽ ሃኪሞች ሆስፒታል ውስጥ ጥገኝነት እግኝተው መጠለላቸውን ሚኑስካ በሚል ምኅፃር የሚታወቀው በሴንትር አፍሪክ የተባበሩት መንግሥታት ዘርፈ ብዙ የተቀናጀ ማረጋጋት ተልዕኮ አስታውቋል፡፡

የመንግሥታቱ ድርጅት ኃይሎች ባንጋሱን ፈጥነው ለመቆጣጠር እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውን ለሮይተርስ የተናገሩት የማኑስካ አዛዥ ፓርፌ ኦናንጋ ኦኛንጋ በአካባቢው ያለውን ሁኔታ «እጅግ የተበላሸ» ሲሉ ገልፀውታል፡፡

ተገድደው ብረት እንዲጨብጡ የተደረጉ ሕፃናት ወታደሮችም ከጥቃት አድራሾቹ መካከል እንደሚገኙ ኦኛንጋ አክለው ጠቁመዋል፡፡

አይቮሪ ኮስት በአዲስ ሁከት ውስጥ

  • ቪኦኤ ዜና

ሁለት የአይቮሪ ኮስት ከተሞች በወታደራዊ አመፅ ተውጠዋል፡፡

ሁለት የአይቮሪ ኮስት ከተሞች በወታደራዊ አመፅ ተውጠዋል፡፡

የአሁኑን ቁጣ ያነሱት ቀደም ስል የአማፂ ቡድን አባላት የነበሩና ጦራቸው ከተፈታ በኋላ ወደ ሃገሪቱ የፀጥታ ኃይሎች እንዲቀላቀሉ የተደረጉ ወታደሮች ሲሆኑ የቀድሞ ትጥቃቸውን ሲፈቱ ይሰጣችኋል ተብለው የነበረ የጉርሻ ክፍያ እስከአሁን እንዳልተሰጣቸው ተገልጿል፡፡

የአይቮሪ ኮስት የምጣኔ ኃብት ማዕከል በሆነችው አቢዦን በርካታ ወታደራዊ ተቋማት ውስጥና ሁለተኛዪቱ ግዙፍ ከተማ ቡአኬ ውስጥ ዛሬ ተኩሶች መሰማታቸው ቢዘገብም የደረሰ ጉዳት ይኑር አይኑር ገና አልተገለፀም፡፡

ያመፁት ወታደሮች ቡአኬን የከትናንት በስተያው ዓርብ ሙሉ በሙሉ የተቆጣጠሩ ሲሆን መንግሥቱ መልሶ ለመያዝ ጦር መላኩ ታውቋል፡፡

ትናንት - ዕሁድ በተካሄዱ የተኩስ ልውውጦች አንድ ሰው ሲገደል ሃያ ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱ ተሰምቷል፡፡

አማፂያኑ ትጥቅ የማስቀመጥ ሃሣብ እንደሌላቸውና የመንግሥቱን ወታደሮች ለመግጠም እየጠበቁ መሆናቸውን ከመካከላቸው አንዱ የሆነ ሃምሣ አለቃ ለሮይተርስ የዜና አውታር ተናግሯል፡፡

ሶማሊያ ውስጥ በወታደራዊ ችሎቶችና በአማፂ ተዋጊ ቡድኖች በዘፈቀደ የሚተላለፉና ተፈፃሚ የሚደረጉ የሞት ፍርዶች ቁጥር በእጅጉ እየጨመረ መምጣት እያሰጋቸው መሆኑን የመብቶች ተሟጋቾች አስታወቁ፡፡

ሶማሊያ ውስጥ በወታደራዊ ችሎቶችና በአማፂ ተዋጊ ቡድኖች በዘፈቀደ የሚተላለፉና ተፈፃሚ የሚደረጉ የሞት ፍርዶች ቁጥር በእጅጉ እየጨመረ መምጣት እያሰጋቸው መሆኑን የመብቶች ተሟጋቾች አስታወቁ፡፡

ባለፈው የአራት ወር ተኩል ጊዜ ብቻ ሁለቱም ወገኖች እያንዳንዳቸው ቢያንስ አሥራ ሁለት ግድያዎችን በአደባባይ መፈፀማቸውንና ሁሉም ግድያዎች ሲካሄዱ ከሰላሣ እስከ ሦስት መቶ የሚደርስ ቁጥር ያለው ሰው ቆሞ እንደሚመለከት ተነግሯል፡፡

በፍርድ የሚፈፀሙ የሚመስሉ የዘፈቀደ ግድያዎች ለሶማሊያ አዲስ ባይሆኑም የግድያው ቁጥር እንዲህ ማሻቀብ እንዳሰጋቸው አምነስቲ ኢንተርናሽናልና የአውሮፓ ኅብረት የሶማሊያ ልዑክ አስታውቀዋል፡፡

የአውሮፓ ኅብረቱ ልዑክ በተጨማሪ የሃገሪቱ መንግሥት የሞት ፍርድን እንዲያስቆም ጠይቋል፡፡

በተለይ ባለፈው የአውሮፓ ወር አፕሪል ውስጥ ብቻ በአሥራ አንድ ሶማሊያዊያን ላይ የሞት ፍርድ ያሳለፉት ወታደራዊ ችሎቶች ጉዳዮችን የሥልጣን ገደቦቻቸውን እያለፉ እንደሚመለከቱና ተከሳሾችም በአግባቡ እንዲከላከሉ ሳይደረግ ፍትሕ እንደሚዛባ ተሟጋቾቹ ይናገራሉ፡፡

ባለፈው መጋቢት 30 ከፊል ራስ ገዟ ፑንትላንድ ውስጥ በአደባባይ በጥይት ተደብድበው የተገደሉ አምስት ታዳጊ ወጣቶች የቀረቡባቸው ክሦች ቦሳሶ ከተማ ውስጥ ባለሥልጣናትን ገድላችኋል የሚል ቢሆንም ልጆቹ እንደአዋቂ ለመዳኘት ለሚያበቃ አካለ መጠን ያላደረሱ እንደነበሩ፣ የሕግ ባለሙያ እንዲያነጋግሩ ዕድል እንዳልተሰጣቸውና አጥፍታችኋል የተባሉትን በግድ እንዲያምኑ መደረጋቸውን አምነስቲ ኢንተርናሽናል አመልክቷል፡፡

ልጆቹ የተባለውን ፈፅመናል ያሉት ድብደባ፣ መደፈር፣ የኤሌክትሪክ ንዝረት፣ ብልቶቻቸውን በሲጋራ መጥበስን የመሳሰሉ የማሰቃያ አድራጎቶች ከተፈፀሙባቸው በኋላ መሆኑን የቤተሰቦቻቸውን እማኝነት የጠቀሰው የአምነስቲ ሪፖርት አስታውቋል፡፡

ይህንን የሥቃይ አድራጎት ፈፅመዋል የሚል አቤቱታ የቀረበባቸው ሰዎች ጉዳይ በነፃ አካል እንዲመረመርና አጥፊዎች በተጠያቂነት እንዲያዙ የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምሥራቅ አፍሪካ፣ የአፍሪካ ቀንድና የታላላቅ ኃይቆች አካባቢ ጉዳዮችጽ ምክትል ዳይሬክተር ሚሼል ካጋሪ አሳስበዋል፡፡

የፑንትላንድ ወታደራዊ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ኃላፊ ሳላህ ሊፍ ግን ችሎቱ በግዳጅ እንደማያሳምን ገልፀው የተገደሉት ሰዎችም ዕድሜ በአዋቂነት የሚያስመድባቸው አይደለም የተባለውን አስተባብለዋል፡፡

XS
SM
MD
LG