በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

አፍሪካዊ የግጭቶች አፈታት ዘዴዎች ዓለምቀፍ ዓውደ ጥናት በመቀሌ

አፍሪካዊ የግጭቶች አፈታት ዘዴዎች ላይ የሚወያይ ዓለምቀፍ ዓውደ ጥናት ዛሬ በመቀሌ ፕላኔት ሆቴል ውስጥ በመካሄድ ላይ ነው፡፡

አፍሪካዊ የግጭቶች አፈታት ዘዴዎች ላይ የሚወያይ ዓለምቀፍ ዓውደ ጥናት ዛሬ በመቀሌ ፕላኔት ሆቴል ውስጥ በመካሄድ ላይ ነው፡፡

ዓውደ ጥናቱን በመቀለ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ሕዝብ ጥናቶች ተቋም ነው እየተመራ ያለው የተቋሙ ዳይሬክተር ዶክተር ክንፈ አብርሃ ይባላሉ፤ ግርማይ ገብሩ የዓውደ ጥናቱ ዓላማና ይዘት በሚመለከት ጠይቋቸው ዶ/ር ክንፈ በሚሰጡት መልስ ይጀምራሉ፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የፌዴራሉን ምርመራ ቢሮ /ኤፍቢአይ/ን ዳይሬክተር ጄምስ ኮሚ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የፌዴራሉን ምርመራ ቢሮ /ኤፍቢአይ/ን ዳይሬክተር ጄምስ ኮሚን ከሥራ ኃላፊነት ለማባረር የወሰዱትን የውሳኔ እርምጃ “ትክክል ነው” ሲሉ እየሟገቱ ናቸው።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የፌዴራሉን ምርመራ ቢሮ /ኤፍቢአይ/ን ዳይሬክተር ጄምስ ኮሚን ከሥራ ኃላፊነት ለማባረር የወሰዱትን የውሳኔ እርምጃ “ትክክል ነው” ሲሉ እየሟገቱ ናቸው።

ፕሬዚዳንቱ የወሰዱት እርምጃ ዋሺንግተን ውስጥ የፖለቲካ ቁጣ አቀጣጥሏል።

ፕሬዚዳንቱና የአስተዳደራቸውን ውሳኔ ትክክለኛነት በመግለፅ ቢከራከሩም ተቃዋሚ ዲሞክራቶች ባለፈው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የሚስተር ትራምፕ የምረጡኝ ዘመቻ ከሩስያ ጋር ተመሳጥሮ ሊሆን ይችላል፤ በሚለው ዙሪያ የሚካሄደውን ምርመራ የሚመራ ልዩ አቃቤ ሕግ እንዲሾም እየጠየቁ ነው።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ኢሕአዴግና ሀገር አቀፍ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ቅድመ ድርድር

ከገዥው ፓርቲና ከሀገር አቀፍ ፓርቲዎች ለድርድር የቀረቡ አጀንዳዎችን የሚያጠናቅረው የአጀንዳ የአደራጅና የሚዲያና የኮሙዩኒኬሽን ኮሚቴ ዛሬ ሥራውን ጀምሯል፡፡

ከገዥው ፓርቲና ከሀገር አቀፍ ፓርቲዎች ለድርድር የቀረቡ አጀንዳዎችን የሚያጠናቅረው የአጀንዳ የአደራጅና የሚዲያና የኮሙዩኒኬሽን ኮሚቴ ዛሬ ሥራውን ጀምሯል፡፡ ድርድሩ ሊጀመር የሚችለው ፓርቲዎቹ በተደራጁት አጀንዳዎች ላይ ከሥምምነት ከደረሱ በኋላ መሆኑን ተገልጿል፡፡

በተቃዋሚ ፓርቲዎች ከቀረቡት አጀንዳዎች መካከል የፖለቲካና የሕሊና እሥረኞች መፈታትና የፀረ ሽብር ሕጉ መሻሻል እንደሚገኝበት የመኢአድ ምክትል ፕሬዚዳንት ለአሜሪካ ድምፅ አስረድተዋል፡፡

በገዥው ኢህአዴግና በሀገር አቀፍ ፓርቲዎች መካከል የሚደረገው ድርድር በሚመራበት ሠነድ ላይ ከሥምምነት በመደረሱ አሁን ትኩረቱ በአጀንዳዋች ላይ ሆኗል፡፡ ኢህአዴግና ተቃዋሚዎቹ በምን በምን ጉዳዮች ላይ እንደሚደራደሩ ገና አልተወሠነም፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Migrants are detained at Abosetta base in Tripoli, Libya, May 10, 2017.

አንድ የሊብያ የባሕር ጠረፍ ጥበቃ መርከብ ትላንት ከ350 በላይ የሚሆኑ ፍልሰተኞችን ባህር ላይ አግኝቶ መልሶቸዋል። ከጀርመን የመድህን ጀልባ ጋር ሊጋጭ የሚችልበት ሁኔታ ተፈጥሮ የነበረ ሲሆን ነገር ግን እስካሁን የደረሰ ጉዳት ካለ አልተገለፀም።

አንድ የሊብያ የባሕር ጠረፍ ጥበቃ መርከብ ትላንት ከ350 በላይ የሚሆኑ ፍልሰተኞችን ባህር ላይ አግኝቶ መልሶቸዋል። ከጀርመን የመድህን ጀልባ ጋር ሊጋጭ የሚችልበት ሁኔታ ተፈጥሮ የነበረ ሲሆን ነገር ግን እስካሁን የደረሰ ጉዳት ካለ አልተገለፀም።

“ሳብራታ” ከተባለችው የጠረፍ ከተማ የተመለሱት ስደተኞች ወደ ትሪፖሊ ተወስደዋል። የሊብያ የባሕር ኃይል ቃል አቀባይ እንደሚለው ስደተኞቹ አንድ በእንጨት የተሠራ ጀልባ ላይ ተፋፍገው ነበር የተገኙት።

የሊብያ የባሕር ጠረፍ ጥበቃ መርከብ ወደነሱ ስትጠጋ አንድ የጀርመን የመድህን ጀልባ ደርሶ ከሊብያው መርከብ ጋር ሊጋጭ ተቃርቦ እንደነበር ቃል አቀባዩ ተናግሯል።

የባሕር ጥበቃ የተባለው የጀርመን የመድኅን ቡድን ፍልሠተኞቹን ወደ ሊብያ መመለሱ ለ”ደኅንነታቸው አደገኛ ነው” በሚል ሳይሆን አልቀረም ከሊብያው መርከብ ጋር የተፋጠጠው ተብሏል፡፡

XS
SM
MD
LG