በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

የዩጋንዳዪቱ ተመራማሪ በዋስ ተለቀቁ

  • ትዝታ በላቸው

የዩጋንዳውን ፕሬዚዳንት ዮዌሪ መሴቬኒን "ፌስ ቡክ ላይ ሰድበዋል" በሚል ባለፈው ወር ታስረው የነበሩት የዩኒቨርሲቲ ተመራማሪ ዶክተር ስቴላ ኛንዚ ዛሬ በዋስ ተለቅቀዋል፡፡

የዩጋንዳውን ፕሬዚዳንት ዮዌሪ መሴቬኒን "ፌስ ቡክ ላይ ሰድበዋል" በሚል ባለፈው ወር ታስረው የነበሩት የዩኒቨርሲቲ ተመራማሪ ዶክተር ስቴላ ኛንዚ ዛሬ በዋስ ተለቅቀዋል፡፡

ዶክተር ኛንዚ ዛሬ ወደ ችሎት ሲገቡ እጅግ የተጎሣቆለ ገፅታ ይታይባቸው እንደነበረ ተዘግቧል፡፡

ወትሮ ንቁ፣ ተገዳዳሪና ተናጋሪ የነበሩት ኛንዚ በሦስት ሴት የወኅኒ ዘቦች ተደጋግፈው ነበር ዳኛ ፊት የቀረቡት፡፡ ዳኛው ጄምስ ኢሬሚዬ ውሣኔአቸውን ከማሰማታቸው በፊት እረፍት እንደተወጣ ኛንዚ ተዝለፍልፈው ወድቀዋል፡፡

ለማንኛውም ሰዉም ከእረፍት ተጠራ፤ ዳኛውም ውሣኔአቸውን አሰሙ፡፡

"በተሰጠኝ ሥልጣን መሠረት ተጠርጣሪዋ በአሥር ሚሊዮን ሽልንግ ዋስ እንዲፈቱ ወስኛለሁ፡፡" አሉ ዳኛው፡፡

ኛንዚ ለዛሬው የዋስ መብት መጠበቅ ከመድረሳቸው በፊት ለአራት ሣምንታት እሥር ላይ ቆይተዋል፡፡

«ኢንተርኔትን ያለአግባብ በመጠቀም» እና «ጎጂ ንግግሮችን በኢንተርኔት ማውጣት» የሚል ነበር የተሰማባቸው ክሥ፡፡ ኛንዚ መሴቪኒን «መንታ ቂጥ» ሲሉ ፌስቡክ ላይ ፅፈውባቸዋል ተብሏል፡፡ /ችሎት ፊት የቀረበ የክሥ ጭብጥ በመሆኑ ነው ቃሉን በግልፅ ለመጥራት የተገደድነው፤ በእኛ በኩል ይቅርታ እንጠይቃለን፡፡/

ይህ ኢንተርኔት ላይ የወጣ ፅሁፍ ፕሬዚዳንቱ ገቢያቸው አነስተኛ የሆነ ቤተሰቦች አባላት ለሆኑ ልጃገረዶች የወር አበባ ንፅህና መጠበቂያ አቅርቦቶችን በነፃ ለማዳረስ ቀደም ሲል ገብተውት የነበረውን ቃል እንዲጠብቁ ለማስገደድ ስቴላ ኛንዚ የከፈቱት ዘመቻ አካል ነው፡፡

በችሎቱ ፊት ስለ ኛንዚ የተሟገቱት የሰብዓዊ መብቶች ጉዳዮች ጠበቃው ኒኮላስ ኦፓዮ ደንበኛቸው የደም ግፊትና የወባ ችግሮች እንዳሉባቸው ገልፀዋል፡፡

"ፍርድ ቤቱ በመጨረሻም ቢሆን ስቴላን በዋስ በመልቀቁ ደስ ብሎናል፤ ባለሥልጣናቱ የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ ጥሰው ዶክተር ኛንዚን እንደገና እንዳያስሩና እንዳያውሉም እንፀልያለን፡፡ አሁን ነፃ በመሆናቸው ለችሎት ስለሚሰጡት መልስም በተገቢው ሁኔታ መወያየት እንችላለን» ብለዋል ጠበቃቸው፡፡

ዳኛው ውሣኔአቸውን ከማሰማታቸው በፊት የተናገሩት የመንግሥቱ አቃቤ ሕግ ጆናታን ሙዋጋኛ ለተከሣሿ የዋስትና መብት ቢጠበቅላቸው እንደማይቃወሙ ገልፀዋል፡፡ "አሁን ተከሣሿ እንደታመመች ተነግሮናል፡፡ ክቡርነትዎ ይህቺ በዋስ የተለቀቀች ተከሣሽ ካሁን በኋላ በኢንተርኔት የሰደበችውንም ሰው ሆነ የቤተሰቡን አባላት እንደገና እንዳትሰድብ እንዲያሳስብልኝ እጠይቃለሁ» ብለዋል፡፡

አምነስቲ ኢንተርናሽናል የሚባለው የሰብዓዊ መብቶች ዓለምአቀፍ ተሟጋች ቡድን በኛንዚ ላይ የተመሠረተውን ክሥ «አስገራሚና ሃሣብን በመግለፅ ነፃነት ላይ የተጣለ ስድብ» ነው ብሎታል፡፡ ክሡ ሙሉ በሙሉ እንዲሠረዝም ጠይቋል አምነስቲ፡፡

የኛንዚ ጉዳይ ለፊታችን ግንቦት 17 ተቀጥሯል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ የፌዴራል ምርመራ ቢሮ /ኤፍቢአይ/ ዳይሬክተሩን ጄምስ ኮሜይን ለማባረር የወሰኑት በራሣቸው ቃላት "መሥራቤቱን በተሳካ ሁኔታ ለመምራት ባለመቻላቸው" እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ የፌዴራል ምርመራ ቢሮ /ኤፍቢአይ/ ዳይሬክተሩን ጄምስ ኮሜይን ለማባረር የወሰኑት በራሣቸው ቃላት “መሥራቤቱን በተሳካ ሁኔታ ለመምራት ባለመቻላቸው” እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ትራምፕ ይሔንን የዋሺንግተንን የፖለቲካ መንደር ሁሉ ያስደነገጠ የትናንት ምሽት ድንገተኛ እርምጃቸውን ለኮሜ በድብዳቤ ያሳወቋቸው መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ትራምፕ ለውሣኔያቸውም መሠረት የሆኗቸው ጠቅላይ አቃቤ ሕጉ ጄፍ ሴሼንስ እና ምክትላቸው ሮድ ራዥንስቲን በቀድሞዋ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሄላሪ ክሊንተን የኢሜል አጠቃቀም የተያዘውን ምርመራ በሚገባ መምራት ባለመቻላቸው ከሥልጣናቸው እንዲባረሩ በተናጠል ያቀረቡላቸው ደብዳቤዎች መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

አፍሪካውያን ፍልሠተኞች

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ከፍተኛ ብዛት ያላቸው አፍሪካውያን ሕገወጥ በሆነ መንገድ ወደ አውሮፓ ለመሻገር ሊብያ ጠረፍ ሲጋቡ ቆይተዋል።

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ከፍተኛ ብዛት ያላቸው አፍሪካውያን ሕገወጥ በሆነ መንገድ ወደ አውሮፓ ለመሻገር ሊብያ ጠረፍ ሲጋቡ ቆይተዋል።

አስተማማኝነት በሌላቸው ጀልባዎች በሜዲትራንያን ባህር ለመጓዝ ሲሞክሩ የአውሮፓ ሕብረት ወይም መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ደርሰው እስከሚያተርፏቸው ጊዜ ድረስ ባሕሩ ላይ ሲንሣፈፉ ከቆዩ በኋላ በመከራ ኢጣልያ ይገባሉ።

በአሁኑ ወቅት ግን ኢጣልያ ከሠሃረ በመለስ ካሉት የአፍሪካ ሀገሮች የፈለሱ አፍሪካውያን በባሕሩ እንዳይደርሱ ለማድረግ እየሞከረች ነው።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ዲሞክራሲ በተግባር

  • ሰሎሞን ክፍሌ
ማሪን ሎ ፔን

በአውሮፓ ኅብረት ህልውና ላይ ጎጂ ለውጥ ሊያመጣ ይችላል የሚል ስጋት በብዙዎች ዘንድ አሳድሮ የነበረው የፈረንሳይ ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ ውጤት በቀኝ አክራሪው ብሄርተኛ ፓርቲ ዕጩ ተወዳዳሪ ማሪን ሎ ፔን መሸነፍ ተወግዷል።

በአውሮፓ ኅብረት ህልውና ላይ ጎጂ ለውጥ ሊያመጣ ይችላል የሚል ስጋት በብዙዎች ዘንድ አሳድሮ የነበረው የፈረንሳይ ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ ውጤት በቀኝ አክራሪው ብሄርተኛ ፓርቲ ዕጩ ተወዳዳሪ ማሪን ሎ ፔን መሸነፍ ተወግዷል።

ሎ ፔን ፈረንሳይን ከአውሮፓ ኅብረት አባልነቷ የማስወጣት ፍላጎት ያላቸው ሲሆኑ በስደተኞች ላይም ጥሩ አመለካከት የላቸውም።

በምርጫው ያሸነፉት ኢማኑኤል ማክሮን ከናፖሊዮን ቦናፓርት ወዲህ ለፈረንሣይ በዕድሜያቸው እጅግ ወጣት የሆኑ የመጀመሪያው ፕሬዚዳንት ናቸው። ፈረንሳይን አንድ ለማድረግ በአውሮፓ ኅብረት አባልነታቸው ለመቀጠልና በዩሮ መገበያየታቸውን ለመቀጠል ቃል ገብተዋል።

የቀኝ አክራሪ ብሄርተኛ ፓርቲዎች ፈረንሳይን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ሃገሮች በተካሄዱ ምርጫዎች ሽንፈት እየገጠማቸው ነው። ሁኔታው ባጠቃላይ ለዓለም በተለይ ግን ለአፍሪካ ምን አንድምታ ይኖረዋል?

የምሽቱ “ዲሞክራሲ በተግባር” ፕሮግራም ባጭሩ ይመለከተዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን የሩስያ አቻቸው ሰርጌይ ላቭሮቭን ዋሺንግተን ላይ ዛሬ - ረቡዕ ቢሯቸው ተቀብለው አነጋግረዋቸዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን የሩስያ አቻቸው ሰርጌይ ላቭሮቭን ዋሺንግተን ላይ ዛሬ - ረቡዕ ቢሯቸው ተቀብለው አነጋግረዋቸዋል።

የሁለቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ውይይት በአመዛኙ ያተኮረው በሶሪያና በዩክሬይን ላይ ሲሆን ጉዳዮቹን በተመለከተ በሁለቱ ሃገሮች መካከል ያሉ ልዩነቶች እንደተጠበቁ መሆናቸው ተገልጿል።

የሩስያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ላቭሮቭ ዋሺንግተንን ሲጎበኙ ባለፉት ዓመታት ሦስት ዓመታት ይህ የመጀመሪያ ጊዜያቸው ነው።

ሁለቱ ሚኒስትሮች በመቀጠል አርክቲክ ካውንስል በሚባለው የአርክቲክ አካባቢ መንግሥታትና ህዝቦች ጉዳዮች ላይ በሚመካከረው ኅብረ መንግሥታዊ ስብስብ ጉባዔ ላይ ለመገኘት ወደ አላስካ ይጓዛሉ።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ዶናልድ ትራምፕ የዩናይትድ ስቴትስ 45ኛ ፕሬዚዳንት ሆነው ከተመረጡ ስድሥት ወራት ሆኗል።

ዶናልድ ትራምፕ የዩናይትድ ስቴትስ 45ኛ ፕሬዚዳንት ሆነው ከተመረጡ ስድሥት ወራት ሆኗል።

ትራምፕ ለፕሬዚዳንትነት የተመረጡት በአሜሪካ ታሪክ ከፍተኛ ክፍፍል ከታየባቸው የምርጫ ሂደቶች አንዱ በሆነው ነው።

ትራምፕ የተወዳደሩትም የፖለቲካ ትርምስ በመፍጠር ዘዴ ነው። ይሁንና እስካሁን ባለው ጊዜ በፕሬዚዳንትነት ዐብይ ሊባል የሚችል ሥራ ሲያከናውኑ አልታየም።

በቀድሞው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ አስተዳደር ወቅት ለሥምንት ዓመታት ያህል የዋይት ሃውስ አስተዳደርን ተቆጣጥረው የቆዩት ዲሞክራቶች በበኩላቸው አዲሱ ሚናቸው ምን እንደሚሆን እያሠላሰሉ ናቸው።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

XS
SM
MD
LG