በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

ዛሬ ሚያዝያ 23 ወይም ሜይ 1 ዓለም አቀፍ የወዛደሮች ቀን፤ የብዙ አገሮች ሠራተኞች ያከብሩታል።

ዛሬ ሚያዝያ 23 ወይም ሜይ 1 ዓለም አቀፍ የወዛደሮች ቀን፤ የብዙ አገሮች ሠራተኞች ያከብሩታል።

ከሰሐራ በስተደቡብ ባሉ የአፍሪካ ሀገሮች ውስጥ የሚገኙ ሠራተኞች፣ ያለ ምንም የሥራ ውል፣ ያለ ምንም የሥራ ወይም ያገልግልሎት ዋስትና አግባብነት በሌለው ሁኔታ ነው የሚሠሩት ይላል ዓለማቀፉ የሥራ ድርጅት - አይኤልኦ።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

ባህር ዳር

ከትናንት በስቲያ ቅዳሜ ምሽት በባህር ዳር መስቀል አደባባይ በሚገኘው ሚሊኒዬም የወጣቶች ስፖርት ማዕከል ውስጥ ፍንዳታ ደርሶ የሁለት ሰው ሕይወት ማጥፋቱን ቢያንስ አምስት ሠዎች መቁሰላቸውን ከአካባቢው ያነጋገርናቸው ምንጮች ገልፀውታል፡፡

ከትናንት በስቲያ ቅዳሜ ምሽት በባህር ዳር መስቀል አደባባይ በሚገኘው ሚሊኒዬም የወጣቶች ስፖርት ማዕከል ውስጥ ፍንዳታ ደርሶ የሁለት ሰው ሕይወት ማጥፋቱን ቢያንስ አምስት ሠዎች መቁሰላቸውን ከአካባቢው ያነጋገርናቸው ምንጮች ገልፀውታል፡፡

ፍንዳታው የደረሠው ታዋቂ አርቲስቶች በተገኙበት የሙዚቃ ዝግጅት ላይ እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡ ሰለተገደሉትና ሰለቆሰሉት ሠዎች ማንነትና ቁጥር ለማጣራት ጥረት ተደርጓል፡፡

ወደ አማራ ክልል የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ንግሡ ጥላሁን ያደረግነው ተደጋጋሚ የስልክ ጥሪ አልተሳካም፡፡ ጥረታችንን እንቀጥላለን፡፡

ከባህር ዳር ያነጋገሩን ግለሰብ ለደኅንነታቸው ስለሰጉ በጠየቁን መሠረት ድምፃቸውን ቀይረናል፡፡ በኮንሰርቱ ላይ የነበሩትን አርቲስቶች ስም ዝርዝር በመጥቀስ ይጀምራሉ፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

ሳምንታዊ ስፖርት

  • ሰሎሞን ክፍሌ

የቱርክ ኢስታንቡል ግማሽ ማራቶን የሴቶችን ኬንያ የወንዶቹን ታንዛኒያ አሸንፈዋል፡፡

የቱርክ ኢስታንቡል ግማሽ ማራቶን የሴቶችን ኬንያ የወንዶቹን ታንዛኒያ አሸንፈዋል፡፡

በወንዶቹ ኢትዮጵያ የሁለተኝነቱን ሥፍራ ወስዳለች፡፡ በመስክ ቴኒስ ራፋኤል ናዳል አሥረኛው የባርሴሎና ኦፕን ድል ተቀዳጅቷል፡፡

በእግር ኳስ የኢትዮጵያና የአውሮፓ ፕሪሚየም ሊግ ጨዋታዎችን እናያለን፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG