በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

ዶ/ር መረራ ጉዲና

ዶ/ር መረራ ጉዲና በዋስ እንዲፈቱ ጠበቆቻቸው ያቀረቡት ጥያቄ በሕግ በተደነገጉ ልዩ ሁኔታዎች መሠረት ውድቅ ይደረግልኝ ሲል ፌደራል ዓቃቤ ሕግ አመልክቷል፡፡

ዶ/ር መረራ ጉዲና በዋስ እንዲፈቱ ጠበቆቻቸው ያቀረቡት ጥያቄ በሕግ በተደነገጉ ልዩ ሁኔታዎች መሠረት ውድቅ ይደረግልኝ ሲል ፌደራል ዓቃቤ ሕግ አመልክቷል፡፡ ፍርድ ቤቱ ጉዳዮን መርምሮ ብይን ለመስጠት ለነገ መጋቢት 1/2009 ዓ.ም. ቀጥሯል፡፡

ዓቃቤ ሕግ ዛሬ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት ባቀረበው የፁሑፍ አቤቱታ በባለፈው ሣምንት ዶ/ር መረራ ጉዲና በዋስ ተፈትተው ጉዳያቸውን በውጭ ሆነው እንዲከታተሉ ጠበቆቻቸው ያቀረቡትን ጥያቄ ተቃውመ፡፡

ዓቃቤ ሕግ በፃፈው በዚህ የተቃውሞ ማመልከቻ በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት የተያዙ ሰዎች በዋስትና የመፈታት መብት ቢኖራቸውም በሕግ በተደነገጉ ልዩ ሁኔታዎች ፍርድ ቤት ዋስትና ላለመቀበል ይችላል ሲል ይንደረደራል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

ኢሕአዴግና ሃያ አንድ ሀገር አቀፍ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ቅድመ ድርድር የአሠራር ረቂቅ ደንብ ላይ ውይይት

ኢሕአዴግና ሃያ አንድ ሀገር አቀፍ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በቅድመ ድርድር ነጥቦች ላይ የሚያደርጉትን ውይይት ዛሬ ቀጥለዋል፡፡

ኢሕአዴግና ሃያ አንድ ሀገር አቀፍ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በቅድመ ድርድር ነጥቦች ላይ የሚያደርጉትን ውይይት ዛሬ ቀጥለዋል፡፡

በድርድሩ በሚሳተፉት ፓርቲዎች አወካከልና በአደራዳሪዎች አመራረጥ ላይ ዛሬ የተወያዩት ተሳታፊዎቹ፣ የመጨረሻ እልባት ለመስጠት ለፊታችን ቅዳሜ ሣምንት ሌላ ቀጠሮ ይዘዋል፡፡

ኢሕአዴግና ሃያ አንድ ሀገር አቀፍ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ቅድመ ድርድር የአሠራር ረቂቅ ደንብ ላይ ውይይት
ኢሕአዴግና ሃያ አንድ ሀገር አቀፍ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ቅድመ ድርድር የአሠራር ረቂቅ ደንብ ላይ ውይይት

ገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግና ሃያ አንዱ ሀገር አቀፍ ተቃዋሚ ፓርቲዎች እየተወያዩ ያሉት የፖለቲካ ፓርቲዎች የክርክርና የድርድር የአሠራር ረቂቅ ደንብ በሚባለው ሰነድ በሰፈሩ ነጥቦች ላይ ነው፡፡

ዛሬ ውይይት ከተደረገባቸው መካከል በዚሁ ሰነድ ቁጥር /8/ ላይ የሰፈረው የድርድርና የክርክር አመራር የሚለው ይገኝበታል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም

ዩናይትድ ስቴትስ በልማትና በሰብዓዊ ዕርዳታ መልክ ለአፍሪካ አምባገነኖች በየዓመቱ የምትሰጠው በቢሊዮኖች ዶላሮች የሚገመት የገንዘብ ዕርዳታ በሙሰኞች ስለሚባክን መቆም አለበት ሲሉ በካሊፎርኒያ ስቴት ዩኒቨርስቲ ሳንበርናንዲኖ የፖለቲካ ሳይንስ መምህርና የሕግ ባለሞያ የሆኑት ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማሪያም ለፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ደብዳቤ ፅፈዋል።

ከግብር ከፋይ አሜሪካውያን እየተሰበሰበ የሚላከው ገንዘብ ለታቀዱ ፕሮጀክቶች ማስፈፀሚያነት ስለማይውል መቆም አለበት ብለዋል፣ ደብዳቤውን ለፕሬዚዳንት ትራምፕ የላኩት ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም በተለይ ኢትዮጵያን አስመልክቶ በፃፉት ደብዳቤ፡፡

በፃፉት ደብዳቤ ይዘትና ዓላማ ዙሪያ፣ የፕሮግራሙ አዘጋጅና አቅራቢ ሰሎሞን ክፍሌ ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያምን አነጋግሯቸዋል።

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG