በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

ethiopia map

ገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግና ሃያ አንዱ ሀገር አቀፍ ፓርቲዎች ሊያካሂዱት ባቀዱት ድርድር እና ክርክር ዓላማ ላይ ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል፡፡

ገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግና ሃያ አንዱ ሀገር አቀፍ ፓርቲዎች ሊያካሂዱት ባቀዱት ድርድር እና ክርክር ዓላማ ላይ ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል፡፡ ባልተቋጩ ሌሎች ነጥቦች ላይ ለመወያየትም ለመጭው የካቲት 30 ቀጠሮ ይዘዋል፡፡

ገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግና ሃያ አንድ ሀገር አቀፍ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ለድርድር የሚያደርጉትን ዝግጅት ቀጥለዋል፡፡ የፖለቲካ ፓርቲዎች የክርክርና የድርድር የአሠራር ረቂቅ ደንብ በሚባለው ሰነድ የሰፈሩትን ነጥቦች እየተመለከቱ ነው፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

ዶ/ር መረራ በማዕከላዊ ለመቆየት ጠየቁ

  • መለስካቸው አምሃ
ዶ/ር መረራ ጉዲና

ዶ/ር መረራ ጉዲና በዋስ እንዲፈቱና ጉዳያቸውን በውጭ ሆነው እንዲከታተሉ ጠበቆቻቸው አመለከቱ፡፡ ዓቃቤ ሕግ ተከሣሽ ባቀረቡት የዋስ ጥያቄ ላይ አስተያየቱን በፁሑፍ እንዲሰጥ ፍርድ ቤቱ አዝዟል፡፡

ዶ/ር መረራ ጉዲና በዋስ እንዲፈቱና ጉዳያቸውን በውጭ ሆነው እንዲከታተሉ ጠበቆቻቸው አመለከቱ፡፡ ዓቃቤ ሕግ ተከሣሽ ባቀረቡት የዋስ ጥያቄ ላይ አስተያየቱን በፁሑፍ እንዲሰጥ ፍርድ ቤቱ አዝዟል፡፡ ከዶ/ር መረራ ጋር ተከሰው ያልቀረቡ ተከሳሾች፣ በጋዜጣ እንዲጠሩ ታዝዟል፡፡ ፍርድ ቤቱ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አስራ ዘጠነኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ ዶ/ር መረራ ጉዲና እንደቀረቡ ችሎቱን በመሰየሙ ሂደት ላይ፣ የሌሎች ተከሳሽ ስም ማለትም ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ፣ ጃዋር መሃመድ፣ ኢሳት ወይንም የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን፣ ኦሮሞ ሚዲያ ኔት ወርክ ተጠርተው በስፍራው አለመኖቸው ተረጋግጧል፡፡ በመቀጠልም ዓቃቤ ሕግ ካቀረበው የክስ ማመልከቻ ላይ ዶ/ር መረራ ጉዲናን የሚመለክተውን ክፍል ፍ/ቤቱ ለተከሳሽ አንብቧል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG