በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜና

በሕይወት የተረፈው ሕፃን እዩጼል ባየ በአለርት ሆስፒታል ተኝቶ

እናቱና ወንድሙ ሕይወታቸው አልፎ መቀበራቸውን ያላወቀ የሰባት ዓመት ታዳጊ አነጋግረነዋል

በሌላ በኩል በዕለቱ ከተደረመሰ በኋላ ተፈልገው ከወጡት ውስጥ በአለርት ሆስፒታል የምትገኝና ባለቤቷን እና ሁለት ልጆቿን ያጣች እናት ጠይቀናል።

በአዲሰ አበባ ከተማ "ቆሼ" ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ቅዳሜ ዕለት በደረሰው አደጋ የሟቾች ቁጥር 113 መድረሱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ማምሻውን አስታውቋል።

ስዩም በየነ ይባላል ሰባት ቤተሰቦቹን አጥቷል በዛሬ ዕለት ለለቅሶ በተቀመጠበት ተገኝቶ ነው የተነሳው። የአንድ ወንድሙን አስክሬን በመጠበቅ ላይ ናቸው።

የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ሚንስትር ዶ/ር ነገሪ ከዚህ አደጋ በህይወት ተርፈው በተለያየ ቦታ የሚገኙ ሰዎችን ለመርዳት ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ እንደሆነና በዘላቂነት መልሶ እንዲቋቋሙ እንደሚደረግ ገልፀውልናል።

ስዩም በየነ ይባላል፡ የ17 ዓመት ወጣትና የ10ኛ ክፍል ተማሪ ነው። ቆሼ እየተባለ በሚተራው ቦታ ተወልዶ ማደጉን ይናገራል። የሚኖሩበት ቤት መካከለኛ የሚባል እንደሆነና በግቢያቸው ውስጥም ተከራዮች እንደነበሩ ይናገራል።ዩም ቅዳሜ ምሽት በቤታቸው ውስጥ የደረሰውን አደጋ ሲያስረዳ፤ በእነርሱ ቤት ውስጥ አራስ የወንድሙን ሚስት ሊጠይቁ የመጡ አክስቱና ስድስት ቤተሰቦቹ በአጠቃላይ በደጋው ሕይወታቸውን አጥተዋል። በግቢያቸው ውስጥ ከነበሩ ተከራዮችም ዐስር ሰዎች በአደጋው ሕይወታቸው ተፍቷል። በአጠቃላይ ከእነርሱ ግቢ ውስጥ 17 ሰው ሞቷል።

የእርሱ የወንድም ልጅ እና የተወሰኑት የተከራይ አስክሬን እየተፈለገ እንደሆነ ነግሮናል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ሚንስትር ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃል ፍለጋው እንደቀጠለና የሟቾች ቁጥር 113 መድረሱን ገልፀዋል።

በሌላ በኩል ከደረሰ በኋላ ለተጎዱት ሰዎች ፈጣን ርብርብ አልተደረገም በዚህም ምክኒያት ሊተርፉ ይችሉ የነበሩ ሰዎች ሕይወት አልፏል የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች አነጋግረናል።

ጽዮን ግርማ ያጠናቀረችውን ዘገባ ዝርዝር ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

ጠ/ሚ ኃይለማሪያም ደሳለኝ

የቆይታ ጊዜው ከአንድ ወር በኋላ የሚጠናቀቀው የአስቸኳይ ጊዜ ዓዋጅ በከፊል ሊራዘም እንደሚችል ጠ/ሚ ኃይለማሪያም ደሳለኝ አስታወቁ፡፡

የቆይታ ጊዜው ከአንድ ወር በኋላ የሚጠናቀቀው የአስቸኳይ ጊዜ ዓዋጅ በከፊል ሊራዘም እንደሚችል ጠ/ሚ ኃይለማሪያም ደሳለኝ አስታወቁ፡፡

በዓዋጁ የተጠቀሱ አብዛኛዎቹ ክልከላዎች፣ ትናንትና ተነስተዋል፡፡ የሀገሪቱ የፀጥታ አካላት በአንድ ዕዝ ተቀናጅተው እንዲሰሩ የሚጠይቁ ክስተቶች ግን መሉ በሙሉ አልተወገዱም ብለዋል - ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

በበተደረገው የሕዝብ አስተያያት ጥናት፣ በጥናቱ ከተሳተፉት ሰማኒያ ሁለት ከመቶው የአስቸኳይ ጊዜ ዓዋጅ "መሉ በሙሉ ወይንም በከፊል እንዲቀጥል" የሚል አስተያየት እንዳለው መረጋገጡን ነው ጠ/ሚኒስትሩ ለፓርላማ አባላት የገለፁት፡፡ አንዳንድ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችም በጠ/ሚኒስትሩ ማብራሪያ ላይ የየራሳቸውን አስተያየት ሰጥተዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

በሌላም በኩል ከኤርትራ በየቀኑ ሁለት መቶ የሚሆን ሰው ወደ ኢትዮጵያ እንደሚሰደድና ከመካከላቸውም አምስት ከመቶ የሚሆኑት የሃገሪቱ ወታደሮች የነበሩ መሆናቸውን የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዛሬ እንደገለፁበት ዓይነት ቀደም ሲል ከኢትዮጵያ ለተሰማ መግለጫ የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ የማነ ገብረመስቀል ሰጥተውት በነበረ ምላሽ ለኤርትራዊያኑ መውጣት ሰበቡ “ኢትዮጵያ ነች” ብለዋል፡፡

“ኤርትራ ውስጥ የፖለቲካ ማሳደድ የለም” ያሉት የሃገሪቱ የማስታወቂያ ሚኒስትር ሰዎች የሚወጡት ጨቋኝ መንግሥት ስላለ፣ ወይም በተሣሣቱ የምጣኔ-ኃብት ፖሊሲዎች፣ ወይም ለኑሮ የማይመች ሁኔታ በመኖሩ ሳይሆን “በጦርነትና ከኢትዮጵያ በሚመጣው የጦርነት ሥጋት ምክንያት ነው” ብለዋል፡፡

በመሆኑም ለኢትዮጵያ ግዙፍ ድጋፍ ይሰጣሉ ያሏቸው የአውሮፓ መንግሥታት ጫናቸውን “ኢትዮጵያ ሰላም እንድትሠጠን ለማድረግ ማሳደር አለባቸው፤ እንደ ሕዝብ፣ እንደሃገር በሰላም የመኖር መብት አለን” ብለው ነበር፡፡

የቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ

የቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ የመጨረሻ ሁለት ምስክሮቹን ዛሬ አሰማ፡፡

የቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ የመጨረሻ ሁለት ምስክሮቹን ዛሬ አሰማ፡፡

ምስክሮቹ ተከሳሽ የፈፀማቸው ድርጊቶች፣ ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል መርሆችን ያልጣሱ መሆናቸውን ለፍርድ ቤቱ አስረዱ፡፡ ቀሪ የተከሳሽ የድምፅ ከምስል ማስረጃዎች ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ተሟልተው እንዲቀርቡ አዞ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

ሁለቱ የአቶ ዮናታን ተስፋዬ የመጨረሻ ምስክሮች ዶ/ር መረራ ጉዲናና አቶ እስክንድር ነጋ በተለያዩ ምክንያቶች የፍርድ ቤት ትዛዝ ሳይከበር ቀርቶ ብዙ ተደጋጋሚ ቀጠሮዎች እየተሰጡ ተሟልተው ሳይቀርቡ ቆይተዋል፡፡

ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ ሁለቱም ምስክሮች ተሟልተው ቀርበዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

“ጳጉሜ” የኢትዮጵያውያን መዝናኛ ማዕከል በሎስ አንጀለስ ካሊፎርኒያ ተሸላሚዎች

“ጳጉሜ” የኢትዮጵያውያን መዝናኛ ማዕከል በሎስ አንጀለስ ካሊፎርኒያ ውስጥ ከተመሰረተ አንድ ዓመቱ ነው።

“ጳጉሜ” የኢትዮጵያውያን መዝናኛ ማዕከል በሎስ አንጀለስ ካሊፎርኒያ ውስጥ ከተመሰረተ አንድ ዓመቱ ነው።

እሑድ መጋቢት ሦስት ቀን ባዘጋጀው የዕውቅናና የማክበሪያ ቀን፣ ለሦስት ኢትዮጵያውያን ሽልማት ሰጥቶ አክብሯቸዋል።

“ጳጉሜ” የኢትዮጵያውያን መዝናኛ ማዕከል በሎስ አንጀለስ ካሊፎርኒያ ተሸላሚዎች
“ጳጉሜ” የኢትዮጵያውያን መዝናኛ ማዕከል በሎስ አንጀለስ ካሊፎርኒያ ተሸላሚዎች

እነዚህ የአክብሮት ቀን የተዘጋጀላቸውና ሽልማት ያገኙ ኢትዮጵያውያን እነማን ናቸው? የአመራረጡ መስፈርትስ ምን ነበር?

አዲሱ አበበ ሌሎች ጥያቄዎችንም አንስቶ የማዕከሉን ዳይሬክተር ዳንኤል አርጋውን አነጋግሮ ለዛሬ ኢትዮጵያውያን በአሜሪካ ፕሮግራሙ አዘጋጅቶታል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

የሚ ጌታቸው(በስተግራ)፡ ተክለሚካኤል አበበ(መሀል)እና ፍፁም አቻምየለህ(በስተቀኝ)

“በተለያዩ ሁኔታ በፍርድ ቤት ሂደቶች አልፈው ጉዳያቸው ሳይሳካላቸው ቀርቶ ነገር ግን ወንጀል ስለሌላቸው ሊሆን ይችላል ከአገር ያልተባረሩ፤ በዓመት ወይ በስድስት ወር አንዴ ወደ ኢሚግራሽን መሥሪያ ቤት እየፈረሙ በሰላም የመሚኖሩ .. ለእነኚህና ለሌሎች አሁን አሳሳቢ ሁኔታ እየተፈጠረ ነው።” የሚ ጌታቸው በካሊፎኒያ የአሜሪካ የሕግ-ጠበቆች ማኅበር የሳንታክላራ ቫሊ ሊቀመንበር።

በብዙ ሚልዮን የሚቆጠሩ በዩናይትድ ስቴትስ የሚኖሩ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸውንና ሌሎችን ያሳሰበ ርዕሰ ጉዳይ ነው።

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ባሳለፍነው ሳምንት መገባደጂያ ያወጡትን አዲሱን ፕሬዝዳንታዊ ማዘዣ ጨምሮ በዩናይትድ ስቴትስ የኢሚግሬሽን ፖሊሲ ዙሪያ እየመጡ ያሉና “ይመጡ ይሆናል” የተባሉ ለውጦችና አንድምታ በጥልቀትና በቅርበት ለማየት የሚጥር ከሕግ ባለሞያዎች ጋር የተካሄደ ውይይት ነው።

ተወያዮች:- የሚ ጌታቸው በካሊፎኒያ ክፍለ ግዛት በሳንሆዜ የአሜሪካ የሕግ-ጠበቆች ማኅበር የሳንታክላራ ቫሊ ሊቀመንበር ናቸው። በስደተኞች ጉዳይ ተሟጋችነትም ይታወቃሉ።

አቶ ፍጹም አቻምየለህ በዋሽንግተን ዲሲና ቨርጂኒያ በጥብቅና ሥራ የተሰማሩና በስደተኞች ሕግ ዙሪያ ለረዥም ጊዜ ያገለገሉ ናቸው።

አቶ ተክለሚካኤል አበበ ደግሞ በካናዳ ቶሮንቶ በጥብቅና ሥራ የተሰማሩ ናቸው። የውይይቱን የመጀመሪያ ክፍል ከዚህ ያድምጡ።

XS
SM
MD
LG